Get Mystery Box with random crypto!

ዋግ ኽምራ የጦር ውሎ…!! '…ንጋት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ህወሓት ወደ ዋግ ኽምራ ሰቆጣ ለመግባ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዋግ ኽምራ የጦር ውሎ…!!

"…ንጋት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ህወሓት ወደ ዋግ ኽምራ ሰቆጣ ለመግባት ከሰቆጣ ፋጥዝጊ ከሚባል ተራራ ላይ ሁና ወደ ዝቋላ ወረዳ ቀዳሚት ቀበሌ ከባድ መድፍ በመተኮስ የተለመደ ትንኮሳዋን ትጀምራለች። ነገር ግን እንደ ቆቦው ግንባር በርግጎ የሚሸሽ፣ የሚፈረጥጥ፣ የማይናበብ የኢትዮጵያ ሠራዊት በዚህኛው ግንባር አልገጠማትም። እንዲያውም አጸፋውን አከበዱባት።

"…በውጊያው ያ ድሮ ኢትዮጵያ በምታውቀው፣ መሸነፍ፣ መበርገግ፣ መሮጥ በማያውቀው ጀግና ስንለው በኩራት ደረታችንን ነፍተን በምንመሰክርለት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዎትና ጀግኖቹ በዐማራ ልዩ ኃይል፣ በዐማራ ፋኖ እና በዐማራ ሚኒሻዎች ጽኑ ተጋድሎ ህወሓትን በመመከት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ውጊያው መቆየቱም ተነግሯል። ከ10ሰአት በኋላ ግን በሰቆጣ የከባድ መሣሪያ ድምፅ አልተሰማም።

"…ህወሓት በ3 አቅጣጫዎች ነበር መድፍ ስትተኩስ የዋለችው። 1ኛ ወደ ዝቋላ ቀዳሚት ቀበሌ። 2ኛ አበርገሌ ወረዳ፣ 3ኛ ፃግብጂ ወረዳ። የፃግብጅ ድልድዩን ሰብረውት የነበረ ቢሆንም ያ ድሮ የምናውቀው መመኪያችን የምንለው፣ የሃገር ኩራት የሃገር መከላከያ ሰራዊታችን ጊዜያዊ ድልድይ በአስቸኳይ በመሥራት ጥራሪን ተሻግሮ ወደ ኮረም መስመርም አልፏል። ገስግሷልም።

"…ጥምር ጦሩ ማታ አበርገሌ ጠዋት መቀሌ ነው የምገኘው እያለ ሲሆን ወደ ኮረም ከገሰገሰና ኮረም ከገባ ግን ወልድያን እይዛለሁ ብሎ በወጥመድ ውስጥ የተቀረቀረው የህወሓት ሰራዊት የመማረክ ዕድል ካልገጠመው በቀር ለወሬ ነጋሪም መትረፉን እንጃ ነው የሚሉት የመረጃ ምንጮቼ። በአፋር በኩል ደግሞ መቀሌ 50 ኪሎሜትር ነው የሚርቀው።

"…ይህ የእኔ የዘመዴ መረጃ ነው።

• ድል ለኢትዮጵያ ሠራዊት…!!
• ለዐማራ ልዩ ኃይል…!!
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!!