Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398.62K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 271

2022-09-04 12:38:44
ስለ ጦርነቱ አዲስ መረጃ…!!

"…ደመሰስናቸው" ነው የሚለት ሁለቱም። በሺዎች የሚቆጠሩ የፋሺስቱ አቢይ አሕመድን ወታደሮች በዚህ ግንባር፣ በዚያኛው ዐውደ ውጊያ ይህን ያህል ደመሰስን፣ ይህን ያህል ማረክን ይላሉ የህወሓት ልሣኖችና አክቲቪስቶች። ደመሰስን ነው የሚሉት። ደመሰስን።

"…ደርብ ይላል የዚህኛው ወገን ደግሞ። ደርቤ ውቃው ይላል። በዚህና በዚያ ቦታ በድሮን በተደረገ የአየር ድብደባ የህወሓት የጦር መሳሪያ ማስቀመጫ መጋዘን፣ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተደመሰሰ፣ በዚህና በዚያ የህወሓት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንደሆኑ የተገመቱ ሰዎች የተሰበሰቡበት ቤት በድሮን ተደበደበ፣ በዚህና በዚያ ግንባር ደመሰስን፣ ተደመሰሱ ነው የሚሉት።

"…በዚህ ግርግር መሃል አበው "ግርግር ለሌባ ያመቻል" እንዲሉ ዐቢይ አሕመድ የቤት ዕቃ ሁሉ አውጥቶ የገዢ ያለህ እያለ ነው። ወያኔ ድሮ ዘርፋ ባስቀመጠችው፣ ከሰሜን ዕዝ ገፋ በከዘነችው፣ እንደ እባብ እየተሽሎከሎኩ በአውሮጵላን ወስደው ያራገፉላትም መሣሪያ አላት። በዚያ ላይ በየግንባሩ ትተውላት የሚሸሹትን ትጠቀምበታለች። ዐቢይ ግን ካልገዛ ከየት ያመጣዋል?

"…አንድ ጥይት ሲተኮስ ዶላር ነው የሚተኮሰው፣ አንድ ታንክ ሲቃጠል፣ አንድ ኦራል ሲወድም፣ አንድ ክላሽ ሲማረክ ዶላር ነው የሚከስረው። የሚተኮሰው፣ የሚቃጠለው፣ የሚማረከው ዶላር ነው። ሃገር ደግሞ ዶላር ከየት ታምጣ? ዳያስጶራውን እንዳይለምን ባለፈው አባሳጭቶታል፣ ሃገርቤት ሰው ደክርቷል። ችግር ነው። በደኅና በሰላሙ ጊዜ ጉራው ሃገር ይያዝልኝ የሚለው ችግኝ አቢይ አህመድ አሁን በጭንቁ ቀን ተደብቋል። ትንፍሽ አይላትም። የሟች ወታደር ችግር የለም። በሽ ነው። አሁንም ሌላዙር የሟች ማስታወቂያ ወጥቷል። እናም ስለጦርነቱ አዲስ መረጃ ያለኝ ይሄው ነው። እርስ በእርስ እየተደማሰስን ነው የሚሉት።

"…እየተደማሰሳችሁ…!!
57.5K viewsedited  09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 07:58:38
"…ሰቆጣ ሰላም አድራለች…!!

"…ሰላም ነው ማለት በዚህ ዘመን ትርጓሜው በህወሓት አለመያዝ እና አለመወረር ከሆነ የዋግኽምራዋ ሰቆጣ ሰላም አድራለች። የሸሸው እና የተበታተነው መከላከያም ተመልሷል። የሰቆጣ ከተማን ዙሪያም ከቦ ይዟል። ሽሽት፣ ስደት ጀምሮ ከነበረው ህዝብም ገሚሱ የተወሰነው ከመንገድ እየተመለሰ ነው። ከህዝቡ ቀድመው የሸሹት አመራሮች ግን እስከአሁን ድረስ የት እንደደረሱ አልታወቀም።

"…አሁን ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የከባድ መሣሪያ ተኩስ አየተሰማነው። እስከአሁን ያለው መረጃ ይሄው ነው።
74.4K viewsedited  04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 22:34:05 የሸዋፋኖ አሁናዊ መረጃ…!!

"…የሆነው ይሄነው። የሸዋሮቢቱ ከንቲባ ይገደላል። ከምሽቱ 3 ሰዓት ጠጥቶ ሰክሮ ወደቤቱ ሊገባ ሲል ይገደላል። ከመገደሉ በፊት ሰውየው ከግርማ የጂብጥላ መመሪያ እየተቀበለ የሸዋ ፋኖ ላይ ይደነፋ፣ ዐቢይ አሕመድን በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰደባችሁ ብሎ በጅምላ ያስረሸነ ሰው ነበር። እንዲያም ሆኖ የሸዋ ሮቢት የብልጽግና ኃላፊዎች ከሁለት ተከፍለው መጨቃጨቅ ከጀመሩ እንደሰነበቱ ይነገራል። አንዱ ወደ ኦሮሞ ብልጽግና የሚያደላ ሲሆን ሌላው ደግሞ ብአዴን እንሁን ባይ ነው። ሟቹ ከንቲባ ወላዋይ ነው አሉ። እናም ከመገደሉ በፊት የፖለቲካ ክፍሉ እንደሚገደል መረጃው እንደደረሰው መነገሩ ተሰምቷል። ከዚያ ተገደለ።

"…የከንቲባው መገደል ለእነግርማ የጅብጥላና ታደሰ ገብረጻዲቅ ሰርግና ምላሽ ሆነላቸው። ፈነጠዙ። አሁን ነው የሸዋ ፋኖን መምታት፣ አሁን ነው የሸዋ ፋኖን መበተን ብለው አሰቡ። በዚያውም ለኦነግ ሸኔ መንገድ ለመጥረግ፣ በዚያውም የዐማራ ልዩ ኃይልና ፋኖና ሚኒሻውን እርስ በእርስ ለማገዳደል ቋመጡ። ቋመጡናም የዐማራ ልዩኃይልን ወደ ሸዋሮቢት ላኩት።

"…የሸዋ ፋኖም በግድያው ስለሌበት በከተማው ነበረ። የዐማራ ልዩ ኃይሎች ወደ ከተማዋ እንደገቡ በቀጥታ ወደ ፋኖ አለቆች ቤት አመሩ። በቀን 27/12/2014 ዓ,ም በየፋኖዎቹ ቤት የደረሰው የዐማራ ልዩ ኃይል ተኩስ ከፈተ። ቦንብ ሁላ መወርወር ጀመረ። ከወያኔና ከኦነግ ጋር የሚዋጋ እንጂ ወንድሞቹ ጋር የሚዋጋ አይመስልም ነው የሚሉት ታዛቢዎች። ፋኖዎቹ ዱብ ዕዳ ነው የሆኑባቸው። እንዳይተኩሱ የራሳቸው የዐማራ ኃይል ነው። ዝም እንዳይሉ ጨካኝ ወታደር ነው የመጣባቸው። እንደምንም ለመከላከል ሞከሩ። ነገር ግን ሌሎች ወደ ጫካ ቢያመልጡም ጥቂቶች ግን ቆስለው ታፈኑ። የታፈኑ ፋኖዎችም የሚከተሉት ናቸው።

1፦ ፋኖ ታደለ ወርቁ
2፦ ፋኖ ዮሐንስ
3፦ ፋኖ እንዳለ አረጋሃኝ
4፦ ፋኖ አማኑኤል ሲሆኑ፤ ፋኖ ታደለ ወርቁ በቦንብ ሦስት ቦታ ተመትቶ ከሸዋ ሮቢት ሪፈር ቢባልም የግርማ የሺጥላና የታደሰ ገብረጻዲቅ ህክምና አያስፈልገውም ቀላል ቁስል ነው ብለው ደብረ ብርሃን 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዲታሠር መደረጉ ተነግሯል። ፋኖ ዮሐንስ ወገቡ ላይ በጥይት ተመትቶ ደብረ ብርሃን ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛል።

"…አሁን እነ ግርማ የሺጥላ ፋኖው ከኦነግ ጋር የሚዋጋበትን የጦር መሳሪያ በድንገት ደርሰው ዘርፈውበታል። የተወሰዱ ንብረቶችም አንድ ድሽቃ፣ አንድ መትረየስ፣ ሁለት ጥቁር ክላሽ፣ ሦስት ቦንብ፣  7000 የመትረየስ ጥይት፣ 3000 የክላሽ ጥይት ወስደውባቸዋል። ልብበሉ ወያኔ ሞላሌ በደረሰች ጊዜ የመሃልሜዳ ህዝብ ከመሃልሜዳ ከተማ ሸሽቶ ሲሄድ ሲሰደድ የግርማ የጂብጥላ ወንድምና ከ4ሴቶች የሚወልዳቸው ልጆቹ ወያኔን ተቀብለው ያስተናገዱ ናቸው። ወያኔ እንደወጣች ግርማ የጂብጥላ ወንድሞቹን የመሃል ሜዳ የጸጥታውና አስተዳዳሪ አድርጎ ሹሟቸዋል። ይሄን ያዙልኝ።

"…እናም ዛሬ በቀን 28/12/201 ግርማ የሺጥላ የዐማራ ልዩ ኃይልንና የፌደራል ፖሊስን አንድ ላይ አቀናጅቶ ወደ ራሳ መስመር ልኳቸው ነበር። የራሳ ፋኖና ገበሬ ተዉ ወንድማማቾች ነን አንዋጋ ብለዋቸውም ነበር። ልዩ ኃይሉ ግን እምቢ ብሎ ከራሳዎች ጋር ጦርነት የከፈተ ሲሆን በጦርነቱም ሁለት ከልዩ ኃይል ሲሰዉ አንድ ከፋኖ ቆስሏል። ከፋኖ የቆሰለው ባዩ የሚባል የፋኖ አባል እንደሆነ አረጋግጫለሁ።

"…በቀጣይ ምንድነው የሚሆነው?

"…ከሸዋሮቢቱ ድንገተኛ የእነ ግርማ የጅብጥላ ወረራ በኋላ በቀጥታ የራሳ ፋኖና ገበሬ፣ የአባያጥር ፋኖና ገበሬ፣ የሸዋሮቢት ፋኖዎች ወደ ጫካ ገብተዋል። ወደ ጫካ የገቡት በሙሉ በዛሬው ዕለት ትግሬ ነው ለሚባለው ለሸዋው አስተዳዳሪ ሽምግልና ልከዋል። የታሰሩት ፋኖዎችና የተዘረፍነው መሣሪያ በአስቸኳይ ይመለስልን በማለት ነበር የላኩት። አይተ ታደሰም እሳት ለብሰው፣ እሳት ጎርሰው 'በሸዋ የታጠቀ ፋኖ አያስፈልግም፣ ገና ሁሉንም እንደመስሳቸዋለን ብለው" ሽማግሌዎቹን መመለሳቸው ተነግሯል።

"…እናንተ ምን አሰባችሁ? ብያቸው ነበር?

"…ሸኔ ከሚገድለን፣ ህወሓት ከምትገድለን እዚሁ ከብአዴን ጋር ተቷክሰን በክብር መሞትን መርጠናል። ሙሉ ሸዋ በቀጣይ ቀናት የሚሆነውን አብረን መጠበቅ ነው። ብለውኛል። ይሄን እያወራን ሳለም አንድ የበጃጅ ሹፌርን የዐማራ ልዩኃይል ልብስ የለበሱት የግርማ የጅብጥላ ሰራዊቶች ተኩሰው መትተውታል። ይሙት ይትረፍ አልታወቀም። የቀረውን እንዲሁ እየተከታተልኩ አሳውቃችኋለሁ።

"…ምነው ሸዋ…!!
86.2K views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:42:03
"…ከመተኛታችሁ በፊት…!!

"…ከመኝታ በፊት በሰሜን ሸዋ ከትናን ጀምሮ ዛሬም የቀጠለውን በግርማ የጂብጥላ ትእዛዝ በፋኖና በዐማራ ልዩ ኃይል መካከል እየተካሄደ ስላለው ጦርነት አሁናዊ መረጃ ልነግራችሁ ነኝና ጠብቁኝ።

"…ቆስለው ሆስፒታል ስለገቡ ፋኖዎች፣ ቆስለው ህክምና ተከልክለው ዘብጥያ ከነደማቸው ደብረ ብርሃን ስለገቡ ፋኖዎች፣ በጥይት በውጊያው ላይ ስለተገደሉት የዐማራ ልዩ ኃይሎች፣ ፋኖው ስለተወሰደበት መሣሪያ አይነት፣ እና ግርማ የሺጥላና ታደሰ ገብረ ጻዲቅ በቀጣይ ስላቀዱት ዕቅድ እጥር ምጥን ያለች መረጃ ጀባ እላችኋለሁ። ጠብቁኝ።
85.6K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 20:36:18
• በዋግ ኽምራ መሬት ላይ ያለው ሃቅ

ዛሬ ጠዋት

"…የዋግ ኽምራዋ ሰቆጣ በአሁን ሰዓት ጭንቅ ላይ ናት። ተደምስሰው ሸሽተዋል ተብለው የነበሩት የህውሀት ኃይሎች እንደገና ተመልሰው ወደ ትያ ከዳነምህረት ተጠግተዋል። መከላከያ ወደኋላ ሁኖ በአየር እደበደበ ነበር። 

ከሰዓት በኋላ

"…ህወሓቶች ከሰቆጣ 17 ኪሎ ሜትር ርቀት ነበር የነበሩት። ወታደሩም ጥሩ በሚባል አቋም ላይ ነበር የነበረው። ህዝቡም ከዚህ በፊት የዛሬ ዓመት ለአዲስ ዓመት በዓል ሊያከብር ከብት አርዶ፣ ጠላ ጠምቆ ቅዱስ ዮሐንስ በዓልን ሊያከብር ሲል ጦርነቱ ፈንድቶ ህወሓት ስትገባ ጥሎ መሸሹን በማስታወስ ዘንድሮም የአምናው ነገር ይገጥመን ይሆን ብሎ በስጋት ላይ ነበር።  

አሁን ምሽት

"…ዱቄት ተብሎ ተበትኗል ተብሎ የተነገረለት የህውሓት ኃይሎች ከሰቆጣ 7 ኪሎ ሜትር ላይ ደርሰዋል። ወለህ ማርያም አካባቢ ነው እየተዋጉ ያሉት። በመረዋ የመጣው የእኛ ኃይልም ሰቆጣን ከቦ የነበረው ኃይል ማለት ነው አሁን ሰቆጣን ለቆ እየወጣ ነው። ህዝቡም አብሮት ከከተማዋ እየወጣ ነው። በላሊበላ በኩል የመጣው የእኛ ኃይልም አስከተማ ላይ እየተራገፈ ነው። ትናንት ወደ አበርገሌ ወርዶ የነበረው መከላከያም ዛሬ ምን ሰምቶ ምንታዞ እንደሆነ አይታወቅም ልክ ድል እንዳደረገ ነገር ሆ እያለ ተመልሶ እየመጣ ነው። የዋግ ህዝብም እንዲህ እያለ ነው። ደሀው የዋግ ህዝብ አዋጥቶ ያዘጋጀላቸውን ምግብ እንኳ ሳይበሉ ከዱን። የዋሁ የሰቆጣ ህዝብ ለ3ተኛ ጊዜ ተከዳ። መከላከያ አሁን ዕቃውን ሸክፎ እየወጣ ነው።

• ትናንትና ሠራዊቱ መቀሌ መግባት የለበትም የተባለውን አስታውሱ። ጦርነቱ ዐማራ ክልል መቆየት አለበት። ኦሮሚያ እስክትለማ ዐማራና ትግሬ ይጨፋጨፍ ይዳማ። የቀረውን ነገ ጠዋት መረጃው ከደረሰኝ እነግራችኋለሁ። እስከዚያው…

"ዐማራና ትግሬ እየተጨፋጨፋችሁ…!
90.2K viewsedited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 20:13:33
"…ስለ ሰቆጣ አሁናዊ ሁኔታ መረጃ ልሰጣችሁ ፈልጌ ነበር። እኔ የሚደርሰኝ መረጃ የታመነ ነው። ከመሬት ላይ ያለውን ሃቅ ነው። እነ ጋሽ ደርቤ፣ እነ ጋሽ በለው፣ እነ ሰበር ዜናዎች የሚያወሩት ደግሞ ድል በድል የሆነ ዜና ነው። ዝም ልበል እንዴ ብዬ ስለ ጦርነቱ መጻፍ አቁሜ ነበር። ነገር ግን ፈጣጣ ውሸቱ ስለበዛ ያሉትን ይበሉ እውነታውን ላፈነዳው ነኝ።

"…እህሳ ምን ትላላችሁ? ወይስ ይቅርብኝ። እንዳማረብኝ ዝም ልበል? እ?
86.8K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 18:01:35
ዶግ ዐመድ…!!

"…ወያኔ መጥታ ትምህርት ቤቱን ትዘርፋለች። የገደለቻቸውን ዜጎች ዐማሮች በጅምላ ትቀብርበታለች። ከዚያ ዐቢይ አሕመድ ያዛል፣ አብርሃ በላይና፣ ይልማ መርዳሳ፣ ብርሃኑ ጁላ ሆነው አየር ልከው፣ ድሮንም አሰማርተው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቱን ዶግ ዐመድ ያደርጉታል። ወዲያው ለናትናኤል መኮንን በሰበር ዜና መልክ እንዲሠራው ይልኩለታል። በመጨረሻም ናቲ ሆዬ እና ሌሎች ሆያሆዬዎች ሰበር ዜና ብለው በራያቆቦ አየር ሃይላችን የራያ ቆቦ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤትን ዐወደሙ ሲሉ ዐማራው ነፍሴ፣ ሃገር ወዳዱ ወገኔ እልልታውን ያቀልጠዋል። ጮቤም ይረግጣል።

"…ይቆይና ብአዴን ሪፖርት ያቀርባል። ይሄን ያህል ትምህርት ቤት፣ ይሄን ያህል ጤና ጣቢያ ወደመብን ይልሃል። በማርያም በአላህ ብር አዋጡልኝ ብለው አኩፋዳቸውን ይዘው በልመና ያደነቁርልሃል።

"…አሁንም ለማስታወስ ያህል ጦርነቱ እየተካሄደ የሚገኘው ዐማራ ክልል ውስጥ ነው። እየወደመ ያለው ዐማራው ነው። እየተሰደደ ያለው ዐማራው ነው። እየተፈናቀለ ያለው ዐማራው ነው። የቆሰለው ወታደር እየታከመ ያለው በዐማራው በጀት ነው። ለወታደሩ ስንቅ እያቀበለ ያለው ዐማራው ነው። እየደቀቀ ያለው ዐማራው ነው። ኦሮሚያ እስክትለማ ትግሬና ዐማራ ይድማ።

"…እየወደማችሁ…!!
93.5K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 13:49:45
በመቱ እንዲህ እየሆነ ነው

• ተቀበል…!

"…በኦሮሚያ ክልል፣ ኢሉባቦር ዞን ዶረኒ ወረዳ ወረቦ ቀበሌ ኦነግ ሸኔ ገብቶ ዐማራ የሆነውን ሁሉ እያፈናቀለው፣ እየዘረፈው፣ እየገደለውና ከትናንት ጀምሮ ደግሞ የዐማራን ሴቶች በሙሉ አስገዳጅ የወሲብ አገልግሎት ለታጣቂው ሸኔ እንዲሰጡ በማስገደድ እየደፈሩ ነው ተብሏል።

"…ከሳምንት በፊት የኦሮሚያ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከላይ ከኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ቢሮ የወጣ ትእዛዝ ነው በሚል ሕጋዊ የጦር መሣሪያ የተባለን በሙሉ ከህዝቡ ላይ ገፈፉ፣ ገፈፉና ህዝቡን ባዶ እጁን አስቀሩት። ከሳምንት በኋላ የኦሮሚያ ፖሊስና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እየጨፈሩ ለቀው ወጡ። እነሱ እንደወጡ የእነሱን እግር ተከትለው ባለጉድሩዎቹ፣ ባለ ሹርባዎቹ ተግተልትለው ገቡ።

"…ሸኔ የተባሉት ኦነጎች ከታንክ በቀር ከባድም፣ ቀላልም መሳሪያ እስከአፍንጫቸው የታጠቁ ናቸው። አሁን ኦነጎቹ በኢልአባቦራ ዞን በዶረኒ ወረዳ በምትገኝ ወረቦ ከተማ ከገቡ ቀናትን አስቆጥረዋል። እስከ አሁን መዝረፍ፣ ማፈናቀል፣ መግደል ነበር፣ አሁን ደግሞ የዐማራ ሴቶች ለኦነግ ሠራዊት የወሲብ አገልግሎት ይስጡ ተብለው አንድ ሴት ለብዙ ኦነግ እንድትደፈር እየሆነ ነው ነው ያሉኝ የደወልኩላቸው ተፈናቃዮች።

"…በዚያም አለ በዚህ ታርጌቱ ዐማራን ማድቀቅ ነው። ዐማራን መስበር ነው። ትግሬም፣ ኦሮሞም ጠላቱ ያደረገው ዐማራን ነው። ዐማራ ግን ገራሚ ፍጥርት ነው። የማይሰበር፣ የማይደክም፣ የማይጠፋ፣ የማይዝል፣ የማይታክት፣ የማይሸነፍ፣ የማይንበጫበጭ፣ እጅ የማይሰጥ፣ አልሞት ባይ ተጋዳይ፣ ቂምበቀል የሌለው፣ ታጋሽ፣ እንደመሬት ሁሉን ቻይ፣ የማይጎብጥ፣ ደግሞም እንደጠላቱ ብዛት የማይጠፋ። አመስጋኝ፣ ይቅር ባይ። ግን ደግሞ ጀግና፣ እናቱ የወለደችው ጀግና። አቤት መታደል። ስቀናባቸው እኮ አትጠይቁኝ።

• ማርያምን እውነቴን ነው።
96.0K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 12:46:32
"…አሸባሪው ፋኖ…!!

"…አለ ነገር አለነገር ወለጋ አለ ነገር፣ ያለምክንያት OMN እንዲህ አይቀባጥር ነበር፣ አለ ነገር አለ ነገር፣ ለዐማራ የተደገሰ ድግስ፣ አለ ነገር አለ ነገር ነገርማ ባይኖር እንዲህ አይኮንም ነበር። አለ ነገር።

"…ያውም ፋኖ፣ ከዘብጥያ ወጥቶ፣ ድንበር ተሻግሮ፣ ኦሮሞን ሲያፈናቅል እግዚአብሔር ያሳያችሁ። ያመልክታችሁም። የሆነ ያሰቧት ነገርማ አለች። ከባድ ነገር፣ ኢንተር ሃምዌይ፣ ሩዋንዳን ሳያስቡማ አልቀረም። አለ ነገር፣ ነገርማ አለ።

"…ግርማ የጅብጥላ የሚባል የመሃል ሜዳ አለሌ አጫሽ ጠጪ ሰካራም የሚያሳድደው ፋኖ ከክልሉ ወጥቶ ያውም ሌላ ክልል ገብቶ ሲያሸብር ይታያችሁ። መንግሥት የሚቆጣጠረው፣ እንደፈለገ የሚያዘው የዐማራ ልዩ ኃይል ከመንግሥት ትእዛዝ አፈንግጦ ልክ እንደ ሸኔ ወመኔ ሆኖ ድንበር አልፎ ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ገብቶ ሲያሸብር ፈጣሪ ያሳያችሁ።

"…ኦነግ ነገ የሚያደርገውን ዛሬ ይኸው ነግሮሃል። ነገ ሊያጸዳህ ተዘጋጅቷል። አለ ነገር፣ የሆነ ነገር አለ። ያለ ነገር እንዲህማ አልጮሁም። አላጮሁትም።

"…እናንተስ ምን ትላላችሁ…?
91.8K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 21:55:14
ሸዋ… አዲስ አበባ… ኢትዮጵያ…!!
72.8K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ