Get Mystery Box with random crypto!

ደሞዝህ ነው ተቀበል። '…አባ ገዳይ ጎበና ሆላ ልጁን ፎሌ ጎበናን የኦነግ ሸኔ አባልና ወታደራዊ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ደሞዝህ ነው ተቀበል።

"…አባ ገዳይ ጎበና ሆላ ልጁን ፎሌ ጎበናን የኦነግ ሸኔ አባልና ወታደራዊ አመራር አድርጎ፣ በኦሮሚያ ክልልም አዝምቶ፣ ዐማራንና ኦርቶዶክሳውያን እያዘረፈ፣ እያስገደለ፣ እያሳገተ፣ እሱ ግን እንደ ሃይማኖት አባት ባላየ፣ ባልሰማ አባ ገዳ ሆኖ በጨዋ ደንብ ስለሰላም እያወራ ሲቦተልክ የሚውል ሰው ነበርእሱ ግን በልጁ በኩል የሰው ነፍስ እያስቀጠፈ ለደጋ አጋዘን፣ ለደብረዘይት አህዮች የኦሮሞን "ውኃ ሲጠየቅ እርጎ ነው የሚሰጠው" ተረት እየተረተ የርህራሄ የሚያሳያቸው አባገዳይ ነበር። ውሎ አድሮ ቆይቶ የንጹሐን ደም ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ደረሰ። ከሥላሴም መንበር ዘንድ ደርሶ ጮኸ። እግዚአብሔርም ፈረደ።

• መሸ፣ ነጋ፣ እቡይ አህመድ በነገሠ፣ የአባገዳይ ጎበና ልጅ ዐማራን ማገት፣ መግደል እና ደም ማፍሰስ በጀመረም በ6ተኛው ዓመት በራሱ በኦሮሙማው ኃይል ፀረ ዐማራው፣ ፀረ ኦርቶዶክሱ የአባ ገዳይ ጎበና ልጅ በዚያው በኦሮሚያ ተገደለ። አባገዳይ ጎበናም አለቀሰ። አነባም። ሌሎች ቤት የገባው ኀዘን መከራም በአባገዳዩ በቤቱ ገባ። ይሄንንም ቢቢሲ የተሰኘው መከራ ጠማቂ ድርጅት ዘገበው።

"…የሌሎቹም ይቀጥላል። ደም ያፈሰሱት፣ የዘረፉት በሙሉ የኀዘን ድንኳንም በሁላቸውም ቤት ሰተት ብሎ ይገባል። አሁንም ገብቷል። እየገባም ነው። በኢትዮጵያም በኦሮሚያም ንፁሐን ብቻ እንዳለቀሱ አይቀሩም። ንጹሐን ያዩት ጭንቀት መከራም በሁሉም ጓዳ ይገባል። እንቅልፍም ታጣላችሁ። ትዋረዳላችሁም። ትራባላችሁ፣ ዘራችሁም እህል ይለምናል። ለምኖም ያጣል። በፈሰሰው የንጹሐን ደም የበቀለውን እህል የበላ ሁሉ በነቀርሳ ህመም ይሰቃያል። መንምኖ፣ ማቅቆም ይሞታል።

"…ቆይቼ እመለሳለሁ።