Get Mystery Box with random crypto!

ተዋሕዶን የነካ የለውም በረካ። '…ባለሜንጫው ጃዋርን እመለስበታለሁ። አሁን በባለ ገጀራው በላይ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተዋሕዶን የነካ የለውም በረካ።

"…ባለሜንጫው ጃዋርን እመለስበታለሁ። አሁን በባለ ገጀራው በላይ መኮንን ላይ ልቀጥል። በዘመነ ወያኔ ፓርላማ ባልገቡት የቅንጅት አባላት ምትክ ተመርጦ የወያኔ ፓርላማ አባል የነበረ። በኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች ዳኛ ሆኖ ዐማሮችን ደም እንባ ያስለቀሰ ሃይማኖትም እምነትም የለሽ ሰው ነበር።

"…ከወያኔ ጋር የኦህዴድ አባል ሆኖ ድጅኖ በመሆን ኢትዮጵያን የማፍረስ ፕሮጀክቱን ያፋጠነ፣ ከዘመነ ነውጥ በኋላ ደግሞ ከዋናው ፀረ ኢትዮጵያው ፈንጄ ከባለ ሜንጫው ጃዋር መሀመድ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በቅድሚያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ማፍረስ የሚለውን የጠላት ዕቅድ ለመተግበርም የተነሣ። በኦሮሞ ምድር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ያስፋቀ፣ ቅዱስ ሲኖዶስን የተፈታተነ፣ በኦሮሚያ ሺዎችን በሃይማኖታቸው ያስገደለ፣ ደማቸውንም ያስፈሰሰ አረመኔ ነበር።

"…በመስቀል በዓል ላይ የኢሬቻን በዓል የደረበ፣ ደብረዘይት ወርዶ በቢሾፍቱ ሃይቅ የከፍት ደም የተቀባ፣ ሃይማኖቱን ያዋረደ፣ ያረከሰ፣ መቅደሱን ለማቆሸሽ በብዙ የጣረ፣ በኦሮሞነቱ ተጠቅሞ ለሴት ልጁ ባመጣው ምስኪን ደሀ ወንድ በኩል በግፍ የዘረፈውን ገንዘብ ያከማቸ፣ ሆቴሎች የከፈተ፣ ቪላ ቤቶች የገነባ፣ ለነውሩ ጥግ የሌለው ባለ ጊዜ ነበር። ከኦሮሞ እስላሞች በሚጎርፍለት ገንዘብ ተዋሕዶን ዱላ አበዛባት።

"…መሸ ነጋ፣ ሁለተኛውም ቀን ሆነ። የጌታ መልአክ የበላይን ጎኑን ነካው። በላይ መኮንን ቀልቡም፣ ውቃቢውም ተገፈፈ። ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹም ተላልፎ ተሰጠ፣ ተረኛ ነኝ፣ መብቴ ነው ብሎ ሐበሻን ዘርፎ ወደ አፍሪካውያን ዘረፋ የዞረውን ሰው ፈጣሪ በ6 ሚልዮን ዶላር ማጭበርበር አዋረደው፣ የበላይን ቅስሙንም፣ ጅስሙንም ሰበረው።

"…አዛኜን አንዳቸውም አይተርፉም። ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል።” ኢሳ 45፥16