Get Mystery Box with random crypto!

ትንቢቱን ከኤምሬትስ እንጀምር…! '…ልዕለ ኃያሏ አማሪካ እና እንግሊዝ እስራኤልም አለችበት ይባላ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ትንቢቱን ከኤምሬትስ እንጀምር…!

"…ልዕለ ኃያሏ አማሪካ እና እንግሊዝ እስራኤልም አለችበት ይባላል የጦር መሣሪያና ደላር እያፈሰሱ በጣሊያን ድልድይነት በዚህ በኤምሬትሱ ሼክ በኩል የእኛኑ መሃይም ሀ ገደሉን ይዘው ኢትዮጵያን የማውደም ተልእኮም ሰጥተው እያንቀሳቀሱት ነው የሚሉ መተርጉማን አሉ።

"…በአረብ ኤምሬትስ በኩል በመጣ ዶላር ምድሪቱ ረከሰች። በአረብ ኤምሬትስ በኩል በመጣ ድሮንና እና ቦንብ ትግሬና ዐማራ ወደሙ ገዳማት፣ አድባራት ፈረሱ። ካህናት፣ መነኮሳት፣ ምእመናን እንደ ቅጠል ረገፉ፣ ተጨፈጨፉም። የኢትዮጵያ መሠረተ ልማት ወደመ። የንጹሐን ደም እንደጎርፍ ፈሰሰ። የኤምሬቱ ንጉሥ የንጉሥ ሰለሞንን የጣት ቀለበት ፍለጋ ገዳማትን አሰሰ። እስራኤል ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ ማሰነች። ምዕራባውያን ታቦትን የሚያጣጥል፣ የሚያራክስ ሃይማኖት በገፍ አስፋፉ። የኢትዮጵያን ምድር አህዛብ አስጨነቁ።

• ትንቢት…

"…የተባበሩት አረብ ኤምሬት ትጠፋለች። ሐበሻን አትንኩ የሚለውን የነቢያቸውን ቃል ተላልፈዋልና እርሷን ጨምሮ ኢትዮጵያን የነኩ ዓረቦችም ሆኑ ምዕራባውያንም ይጠፋሉ። መፈራታቸውን፣ መከበራቸውንም ያጣሉ። ግርማ ሞገስ ውበታቸው ሁሉ ይረግፋል፣ ይገፈፋልም። ክብራቸውንም ያጣሉ።

"…ኢትዮጵያ ድሮን የላትም። ቦንብም አታመርትም። የኢትዮጵያ ድሮኗ አውቶሚክ ቦንቧም ጸሎቷ ነው። አዎ ዱባይ ትፈርሳለች፣ ትግማማለች፣ ትጠነባለች። የወልቃይትን ለም መሬት እንደጓጓችም ትቀራለች። መሰረቷ ሁሉ ይናወጣል። ድሪቶአም፣ ቡቱቱአም፣ ጨርቃም ትሆናለች። ፎቅ ሕንጻዎቿ በሙሉ ዱቄት፣ ዐመድ ይሆናሉ። ትወድማለች በል በል አለኝ። ቀኝ ትከሻዬንም ሸከከኝ ያልኳችሁና ከዚህ በፊት በተለብዥንም የነገርኳችሁ ሁሉ ይፈጸማል። ኢትዮጵያን የነካ የለውም በረካ። አራት ነጥብ።

• ይሄ የእኔ ትንቢት ነው። የእናንተን ቀጥሉ።