Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398.62K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 267

2022-09-09 13:59:04
"…በኢትዮጵያውያኑ እሬቻዋን የበላችው ፋሽስቷ ኢጣሊያ እንኳ እንዲህ አላደረገችም። አሁን ይሄ የተፈጸመው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ቢባል ማን ያምናል። ይሄን ስታይ ግብፅ ራሷ አትደነግጥምን? የሳዑዲን ባንዲራ እንደግል አዳኙ የሚቀበል ትውልድ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲያይ በቀን በብርሃን የሚነስረው ትውልድ ኢትዮጵያ ውስጥ ያውም ኦሮሚያ ተብዬው ክልል ውስጥ ብቻ ነው ያለው። የሆነው ሆኖ ለተወሰነች ሰከንድ ዊኒጥ ዊኒጥ ይባል እንደሁ እንጂ ኢትዮጵያንም የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማዋንም ማጥፋት አይቻልም። ለጊዜው አሁን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ክብሩን ያጣው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብቻ ነው። እርሱም የጊዜው ጊዜ ሲደርስ ይስተካከላል። ይኸው ነው።

• ኢትዮጵያ…
99.3K viewsedited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 11:20:46
"…ሰው እንዴት ይህችን ከመሰለች ውብ የነፃነት ጮራ ከሆነች ሰንደቅ ዓላማ ጋር ይላተማል…?

• እ ም ጷ …!!
92.4K viewsedited  08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 10:43:47
በነገራችን መሃል…!!

"…የመንግሥት አክቲቪስቶች ስለሚያወሩት ተያዘ ተለቀቀ ጉዳይ እኔንም ግራ እየገባኝ ነው። በራያ ግንባር ውጊያው እንደቀጠለ ነው። የሚሞተውና የሚቆስለው ስፍር ቁጥር የለውም። ውጊያው ያለው የአላውሀ ወንዝን ተሻግሮ በጉብየና በበላጎ ተራራወች ላይ ነው። ይህ የአላውሀ ወንዝ በላይኛው በኩል ያለው ተራራው በመከላከያ የተያዘ ተራራ ነው።

"…አላማጣ ደረስን፣ መቀሌ ልንገባ ነው የሚሉት ከየት አምጥተው እንደሆነ አልገባኝም። የራያው ግንባር ልክ እንደ ጎንደር እና እንደ ሰቆጣው ግንባር በወታደራዊ ዲሲፒሊን እየተመራ አይደለም። የራያ ህዝብ ሞት ቀለቡ ከሆነና በመንግሥት ከተረሳ ቆየ። የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በራያ በኩል ለምን ወደፊት መግፋት እንደማይፈልግ እሱና የሚያመልከው አጋንንቱ ናቸው የሚያውቁት።

"…እውነት ብቻ…!!
92.6K viewsedited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 09:00:35
ተጀምሯል…!!

"…ዛሬ ጳጉሜን ፬ ቀን ስለ ሰንደቅ ዓላማችን እና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስናወሳ እና ስናወድስ የምንውልበት ዕለት ነው።

"…አንዳንዶች ሊነሥራቸው ይችላል። አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ዓላማ ሲያዩ ሊያማቸው ይችላል። ሆኖም ግን ምንም ልንረዳቸው አንችልም።

"…እናንተም ደብራችሁን፣ ያሳደገቻችሁን ቤተ ክርስቲያን፣ አጥቢያችሁን አስተዋውቁን። እኔ ብዙም አልተሻለኝም ነገር ግን ከትናንቱ ዛሬ በጎ ነኝና በየመሃሉ ብቅ ማለቴ አይቀርም።

"…በሉ ጀምሩ…!!
94.8K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 22:11:44
ጳጒሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን፦ በማለት ስናከብር እንውላለን። ፌስቡክም፣ ቴሌግራምም በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ ዓላማችን እና በዋሻ፣ በጭቃ፣ በእምነበረድ ስለተሠራችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስናወጋ እንውላለን። በአጥቢያችሁ፣ ያሰደጋችሁ ደብረረና ገዳምም ታስተዋውቁናላችሁ። የሚነስረው ይንሰረው እንጂ ነገማ ፌስቡክም፣ ቴሌግራምምም በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ ዓላማችን ነው የምናጥለቀልቀው።

እኔም እስከ ነገ ከጥልቁ እንቅልፌ ሳልነቃ አልቀርም። ነቃ ብዬ ነው የምጠብቃችሁ።

"…እየተዘጋጃችሁ…!!
99.5K views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 18:20:43 በ2013 ዓም የዛሬ ሁለት ዓመት እንዲህ ብዬ ጽፌ ነበር እስቲ መልሳችሁ አንብቧት። ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ።

~ጷጉሜን ፫

የፊደል ገበታ ቀን።
  *~★★~*

~ የፊደል ገበታ ያለበት ፎቶ ብቻ ዛሬ ፌስቡክን ተቆጣጥሮት እንዲውል እናድርገው። ማኅበራዊ ሚዲያውን በእሱ እናጥለቅልቀው። 

ETHIOPIA | ~ ዛሬ ደግሞ ጳጉሜን 3 ነው። በዚያ ላይ ዓመታዊው የቅዱስ ሩፋኤል ክብረ በዓል ነው። እናም የፊደል ገበታ ቀናችንን ሞቅ ደመቅ አድርገን እያከበርን በዚያውም የቅዱስ ሩፋኤልን በዓል ሰብሰብ ብለን ስንዘክር፣ ስንዘምርም እንውላለን።

•••
የኢትዮጵያ ጌጥ፣ የሀበሻ ሁሉ መኩሪያ ነው ሀ ሁ የፊደል ገበታችን። የኢትዮጵያውያንም። የኤርትራውያንም መኩሪያ ነው የፊደል ገበታችን። ክብርና ምስጋና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይድረሳትና ልጆቿ አበው ብራና ፍቀው፣ ቀለም በጥብጠው፣ አእምሮአቸውን ተጠቅመው ይኸው እኛንም በዓለም ላይ የራሳቸው ፊደል ካላቸው ሀገራት በቀዳሚ ተርታ ላይ እንድንመደብ አደርገው አስቀመጠውናል። ያለ ድጋፍ በራሱ የሚቆም ፊደል ባለቤቶች አድርገው አንደኛ አደረጉን። ክብር ለአባቶቻችን።

•••
ፊደላችን የቀደመ የኢትዮጵያዊነታችንም ሆነ የኦርቶዶክሳዊ ማንነታችን መገለጫችን ነው። የቀደሙቱ አባቶቻችን ፊደልን ፈጥረው፣ አሳድገው፣ አበልጽገውም፣ አስፋፍተው ኢትዮጵያን ሞላዋን አጥለቅልቀዋትም ነው ለእኛ ያስረከቡን። ሀበሻ ሆኖ በኢትዮጵያ ፊደል የማይጠቀምና የማይኮራ ሰው የለም። ሀበሻ ሆኖ በአማርኛና በግዕዝ ፊደላት የሚሸማቀቅ፣ የሚያፍር፣ ካለ እሱ ሶዬ ወይ የባንዳ የልጅ ልጅ ነው ወይም ደግሞ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ የጠላት ቅጥረኛ ነው። እኛ ግን በፊደላችን እንኮራለን። ከፍከፍም እንለን።

•••
ብዙዎች የፊደል ገበታችንን አሳምረው ይጠቀሙበታል። የአማርኛ ቋንቋን ለመቃወም ራሱ እሱኑ የአማርኛ ቋንቋ አሳምረው የሚጠቀሙ ጥቂቶች አይደሉም። የትግሬው ህወሓትም፣ የኦሮሞው ኦነግም ሁሉ እንዲሰማቸው ሲያለቃቅሱ የሚውሉት በሚጠሉት የአማርኛ ቋንቋ ነው። እየጠሉት የፊደል ገበታውን የሚጠቀሙ ሰዎች ደግሞ በጣም ያስቁኛል ያሳዝኑኛልም።… ቆንጅዬ የዐማራ ሚስት በአማርኛ ጀንጅኖ፣ አማላጅ በአማርኛ ልኮ አግብቶ ትዳር መሥርቶ፣ ዐማራዋን ቆንጆ ሚስቱን እሷን ታቅፎ እየተኛ፣ ቆንጅዬ ቆንጅዬ ልጆችን አከታትሎ በላይ በላዪ አስወልዶ እየኖረ ሲነጋለት ጠዋት ሚድያ ላይ ቀርቦ ዐማራንና አማርኛን ሲሳደብ፣ ሲራገም የሚውል ስንትና ስንት ዓይነት ሰው አለ መሰላችሁ።

•••
ለምሳሌ ተመልከት እነ ጃዋር መሀመድ ሀብታምና ታዋቂ የሆኑት አማርኛን አቀላጥፈው በመናገራቸው ነው። መለስ ዜናዊ የሚጠላትን ሃገር ቀጥቅጦ የገዛው በአማርኛ እያወራ ነው። ያውም በሚያፈዝ፣ በሚያደነግዝ ምላሱ ቋንቋውን እየቀሸረ። እነ ጃዋር በአማርኛ ቅኔ ይዘርፋሉ። እነ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋቢሳ፣ እነ ግርማ ጉተማ፣ እነ ፀጋዬ አራርሳ ዐማራንና አማርኛን እየጠሉ፣ እየተጸየፉ አማርኛን ከዐማራው በላይ አቀላጥፈው የሚናገሩ ናቸው። በዚህም ደግሞ ተጠቀሙ እንጂ አልተጎዱም። ነገር ግን ሰዎቹ በተፈጥሮአቸው ምቀኞች ስለሆኑ፣ የበታቸኝነት ስለሚያጠቃቸው የኦሮሞው ህዝብ አማርኛን አውቆና ተምሮ በመላ ሀገሪቱ ተዘዋውሮ በፈለገው የሥራ መስክ ተቀጥሮ እንዳይበላ በካቴና ጭምር አስረውታል። እነሱ ግን እንዳሻቸው ሆነው ይኖራሉ።

… አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ከኦሮሚያ ውጪ በመላ ኢትዮጵያ ተዟዙሮ በፈለገበት ሥፍራ ተቀጥሮ ሥራ መሥራት እንዳይችል አድርጎ ነው የትግሬው ገዢ አይተ መለስ ዜናዊ ጠፍሮ ያሰረው። ኦሮሞ በላቲን ቋንቋ እየጻፈ፣ እያወራ፣ እዚያው ክልሉ ውስጥ ታጥሮ እንዲቀመጥ ነው ያደረገው። በምትኩ የትግሬ ልጆች አማርኛ ኤ እያመጡ የኦሮሞ አስተዳዳሪ ሊቀመንበር ሁሉ እንዲሆኑ ነው ያደረጋቸው። እግዚአብሔር ይይለት።

•••
ተወደደም ተጠላም አማርኛ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ የሥራ ቋንቋ ይሆናል። እኛም ላቲንን ለላቲኖቹ እንመልስና በራሳችን ቋንቋ እንጠቀም። ክብር ለሚገባው ለኢትዮጵያው የፊደል ገበታ መጀመሪያ ራሳችን ክብርን እንስጥ።

ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ
ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ
ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ
ኀ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ
ኘ ኙ ኚ ኛ ኜ ኝ ኞ
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ
ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ
ወ ው ዊ ዋ ዌ ው ዎ
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ
ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ
ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ
ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ
ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ
ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ
ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ
ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ
ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ

•••
ይሄ ነው የእኔ ፊደል። ያልተሠረቀ፣ ያልተበረዘ። የማንነቴ መገለጫ። ወዳጄ የሰው ወርቅ እኮ አያደምቅ ነው ከነ ተረቱ። መኩራትስ በራስ ነው። ማን እንደራስ ወርቅ? ክብር ለአባቶቻችን። ከብር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን።

•••
¶ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።

•••
" እኔ ግን እላለሁ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።

"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን !
                                                
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "

• ይህንንም ራሴው እኔ ዘመዴ በእጄ ጻፍኩት። +4915215070996 ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው። 

•••

ሻሎም !   ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጷጉሜን 3/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
101.0K viewsedited  15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 23:11:33
ጳጒሜን ፪ የክብረ ክህነት ቀን…!!

"…ነገ ጳጒሜን ፪ ደግሞ የክብረ ክብረ ክህነት ቀናችን ብለን ሰይመነዋል።  በነገው ዕለት ክበረ ክህነትን የምንገልጥበት፣ የምናወድስበት፣ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ስለ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ስናወሳ የምንውልበት ዕለት ነው። ከልደት እስከ ሞት ድረስ በእያንዳንዱ የህይወታችን ጉዞ ውስጥ ትልቁንና ወሳኙን ድርሻ ስሚይዙት፣ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፉ በእጃቸው ስለሚገኘው አባቶቻችን ካህናትን ነገ ቀኑን ሙሉ ከያለንበት ሆነን ስንደውልላቸው፣ ለበዓሉም ከመጬው አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫም ስናስተላልፍላቸው፣ አቅማችን የፈቀደውንም ለካህን የሚገባ ስጦታም ስናበረክትላቸው የምንውልበት ቀን ነው።

"…የነገ ሰው ይበለን። ነገ አባቶቻችን ምን ያህል እንደሚደሰቱ አትጠይቁኝ። ከምር ደውሉላቸው። ሰርፕራይዝ ነው የምትሉት አዎ ሰርፕራይዝ አድርጓቸው። አስደስቷቸው። ዘመዴ ነው የላከን በሏቸው። ከንስሀ አባቶቻችሁ የራቃችሁ በዚህ አጋጣሚ አግኟቸው። ለእኔም ፍጻሜዬን እንዲያሳምርልኝ " አክሊለ ገብርኤል" ብለው እንዲጸልዩልኝ ንገሩልኝ። በማርያም እንዳትረሱት።

"…ይሄ ቻሌንጅ የእኛ የባለ ማዕተቦቹ ነው። ሌሎቻችሁ አልደረስኩባችሁም። አልመጣሁባችሁም። እናም ገብታችሁ በቅናት መንፈስ አትዘባርቁብኝ። እምቢ ካልክ ቆምጬ ነው የምለቅህ። እቀስፍሃለሁ። ሰምተሃል።

የነገ ሰው ይበለን። ደኅና እደሩልኝ…!!
19.5K views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 22:55:05
የመጨረሻ…!!

የማዳም ቅመሞች፣ የብዙ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች የተስፋ ምንጮች ባለማዕተቦቹ እህቶቼ። ኑሩልኝ። በሰላም ለሃገራችሁ ያብቃችሁ። አሜን…!!

በመቀጠል ስለ ነገ ውሎአችን እናወጋለን። ነገም እንዲሁ ነው የምንውለው።
22.1K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 22:43:14
"…አየሃት የማዳምን ቅመም፣ የዓረቢያዋ ምድር ፀሐይ ባለማዕተቧን እህቴን…!! ማዕተቤንማ አልበጥስም። የትም፣ በምንም ምክንያት ማዕተቤን አልበጥስም።

"…አለች እንጂ ሁለት ፊልም ላይ ስትታይ አንጀሊና ጆሊ አንጀሊና ጆሊ የሚያጫውታት፣ አለች እንጂ የብልፅግና ካድሬ ስለሆነች ብቻ ማዕተቧን ለሆዷ በሆዷ ቀይሯ እምነቷን የምትቀይር። አለች እንጂ አያቷ የተወለዱበት አልጋ ላይ እየተኛች፣ በፊሊት ቆርቆሮ ጨው ቋጥራ፣ የአይጥ መናሃሪያ በሆነ ኮርኒስ ስር እየኖረች፣ በተውሶ ብታንቲ እየዘነጠች፣ ማዕተብ ሳስር አለርጂክ አለብኝ፣ ውበቴን ያጠፋዋል የምትል። ዘማናዊነትስ ማዕተብን ማጥበቅ ነው።

አየሻት የእኔን የማዳም ቅመም። የዐረቦቹን ሕግ ታከብራለች። እንጀራዋ ነውና። በማዕተቧ ግን ድርድር የለም። ማዕተቤንማ አልበጥስም።
23.8K viewsedited  19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 22:39:10
"…በነገራችን ላይ ይህችን ጳጒሜን አምስቷን ቀን በራሳችን መርሀ ግብር እንመራ ብዬ እንጂ ጮማ ጮማ የሆነ ወሬ አጥቼ አይደለም። ከሰሜን እስከ ምዕራብ ኢትዮጵያ ስላለው ጦርነት፣ ጥይት አልቆብኛል ብሎ ወደ በደሌ ስለሚፈረጥጠው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ በማይጸምሪ፣ በሰቆጣ፣ በራያ ስላለው የጦርነት ውሎ ቪድዮ ሁላ ነው ያለኝ። ግን ቀኑ ማዕተቤን የማጠብቅበት ቀን ነው። ዐማራ ላይ ሙጭጭ ብሎ በገገማው በጭፍን የዐቢይ አሕመድ መንግሥትን ሲያወድስ የሚውለው ፋሲል የእኔ ዓለም በዘመን ባንክ ስለሚገኘው ተቀማጭ ብሩ መረጃው ሳይደርሰኝ ቀርቶ አይደለም። ይደርሳል ብዬ ነው። እናንተ ዶላራችሁን ለመከላከያው ብላችሁ ላኩ እነ እንቶኔ ደግሞ ይቀረማመቱታል።

በሉ እሱን ሌላ ጊዜ እዘረግፈዋለሁ። አሁን ወደ ማዳም ቅመሞች እንሄዳለን።
23.6K views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ