Get Mystery Box with random crypto!

ጳጒሜን ፪ የክብረ ክህነት ቀን…!! '…ነገ ጳጒሜን ፪ ደግሞ የክብረ ክብረ ክህነት ቀናችን ብለ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጳጒሜን ፪ የክብረ ክህነት ቀን…!!

"…ነገ ጳጒሜን ፪ ደግሞ የክብረ ክብረ ክህነት ቀናችን ብለን ሰይመነዋል።  በነገው ዕለት ክበረ ክህነትን የምንገልጥበት፣ የምናወድስበት፣ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ስለ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ስናወሳ የምንውልበት ዕለት ነው። ከልደት እስከ ሞት ድረስ በእያንዳንዱ የህይወታችን ጉዞ ውስጥ ትልቁንና ወሳኙን ድርሻ ስሚይዙት፣ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፉ በእጃቸው ስለሚገኘው አባቶቻችን ካህናትን ነገ ቀኑን ሙሉ ከያለንበት ሆነን ስንደውልላቸው፣ ለበዓሉም ከመጬው አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫም ስናስተላልፍላቸው፣ አቅማችን የፈቀደውንም ለካህን የሚገባ ስጦታም ስናበረክትላቸው የምንውልበት ቀን ነው።

"…የነገ ሰው ይበለን። ነገ አባቶቻችን ምን ያህል እንደሚደሰቱ አትጠይቁኝ። ከምር ደውሉላቸው። ሰርፕራይዝ ነው የምትሉት አዎ ሰርፕራይዝ አድርጓቸው። አስደስቷቸው። ዘመዴ ነው የላከን በሏቸው። ከንስሀ አባቶቻችሁ የራቃችሁ በዚህ አጋጣሚ አግኟቸው። ለእኔም ፍጻሜዬን እንዲያሳምርልኝ " አክሊለ ገብርኤል" ብለው እንዲጸልዩልኝ ንገሩልኝ። በማርያም እንዳትረሱት።

"…ይሄ ቻሌንጅ የእኛ የባለ ማዕተቦቹ ነው። ሌሎቻችሁ አልደረስኩባችሁም። አልመጣሁባችሁም። እናም ገብታችሁ በቅናት መንፈስ አትዘባርቁብኝ። እምቢ ካልክ ቆምጬ ነው የምለቅህ። እቀስፍሃለሁ። ሰምተሃል።

የነገ ሰው ይበለን። ደኅና እደሩልኝ…!!