Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398.62K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 266

2022-09-14 19:05:16
እዚህ ጋር ደግሞ ሌላ ትኩሳት…!!

"…አሁንም ማረፍ እፈልጋለሁ። ነገር ግን አንዳንድ ዋይታዎች፣ የድረሱልን ድምጾች ግን አያሳርፉም። አያስተኙም። መደበቂያም ያሳጣሉ። ሰሚ ኖረም አልኖረ ግን ለታሪክ መቀመጡ በራሱ አንድ ሌላ ታሪክ ነውና ይሄን የድረሱልን ጥሪ መልእክት ለማስተላለፍ ተገድጃለሁ።

"…ይኸውልህ ዘመዴ ከወጨጫ ማርያም ጀምሮ… ቆርኬ ቀበሌ እስከ ወለቴ ዲያስጶራ የሚባለው ለሚ ደብረይድራስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ድረስ የሚገኙ በብሔር የዐማራ፣ የጉራጌ እና የዶርዜ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ለማፍረስ የኤክስ ምልክት ተደርጎባቸዋል።

"…በቶሎ እንዲቋጭ የማይፈለገውን የሰሜኑን ጦርነት እንደ 120 ድራማ እያሟዘዙ የሰዉን ዓይንና ጆሮ በዚያ ሰቅዞ በመያዝ እነርሱ ከስር ከስር ጽዳቱን ከዳር ሃገር ወደ መሃል ሃገር አስጠግተውታል። የኦሮሚያ ልዩኃይል፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይላትም በቤቶቹ ፈረሳ ወቅት የሚያለቅስ፣ ጮክ ብሎ የሚጮህ ካለ አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት በተጠንቀቅ መቆማቸውም ተነገሯል። …በሉ እንግዲህ ዐማራ፣ ጉራጌና ዶርዜዎች እንደተለመደው ዋይ ዋይ ለማለትም ተዘጋጁ…!!

"…እግዚአብሔር ይሁናችሁ…!!
229.5K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 12:15:55 Zemedkun Bekele (ዘመዴ) pinned a photo
09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 11:27:59
"…እግዚአብሔር ይመስገን። እኔና ቤተሰቤ እጅግ በጣም ሰላም ነን። የቀረው የተለመደው የእኔ ወደ ሚዲያውና ወደ ቴሌግራም ቻናሌ መመለስ እና መጨቃጨቅ፣ መጯጯህ ብቻ ነው። እርሱ ደግሞ በቅርቡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እመለስበታለሁ።

"…ከጷጉሜ 5 ምሽት ወዲህ ከስልክም፣ ከኢንተርኔትም ራሴን ለመጀመሪያ ጊዜ አርቄ አግልዬም ስለነበር በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ላይ ምን እየተከሰተ እንደነበር ምንም ዓይነት መረጃ አልነበረኝም። የባለቤቴን ስልክ የሚያውቁ ጥቂት ወዳጆቼ በባለቤቴ በኩል ደጋግመው መወትወታቸው ምቾት ያልሰጣት ባለቤቴ "አለሁ ብለህ ገላግለኝ" ስላለችኝ ነው ዛሬ ብቅ ማለቴ።

"…የመልእክት ሰንዱቆቼንም ዛሬ ገና ነበር የከፈትኳቸው። እናም ካንገበገበኝ ነገር አንዱ "ዘመዴ፣ ከበውናል፣ ሰዉ ሁሉ ስለ ሰሜኑ ጦርነት ነው ትኩረቱ፣ ሊጨፈጭፉን ነው፣ መልእክቱን አድረስልን፣ ንገርልን የሚል መልእክት ከወለጋ አስቀምጠውልኝ እኔ ግን ከኢንተርኔቱ ዓለም ተቆራርጬ ስለነበር መልእክታቸውን ሳላነበው፣ ሳላደርስላቸውም ቀርቼ አሁን መልእክታቸውን ሳነብ፣ ስመለከት ከተከበቡቱ "ከ40" በላይ የሚሆኑቱ መታረዳቸውን በመስማቴ ከልብ አዝኛለሁ። ይሄ እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው።

"…የወዳጅ የጓደኞቼን የሁላችሁንም መልእክቶች በሙሉ አንብቤአለሁ። ከጠዋት ጀምሮ እሱኑ ነበር ሳነብ ያረፈድኩት። የአንዳችሁም መልእክት አላለፈኝም። ስለ መልካም ምኞታችሁ በሙሉ እጅግ አድርጌ አመሰግናላሁ። በጤናዬ በኩል ግን እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው ፍፁም ደኅና ነኝ። በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሚዲያ ሥራዬም እንደምመለስም ተስፋ አደርጋለሁ። የመምሬ ቄሱንም ቤት መግዛት አለብኝ እኮ። እሱ ነገርም አልተቋጨም። ከስልክ ራቅ ማለቱ ግን ጥቅሙ ለራሴ ነው። ለማንኛውም ቸር ያገናኘን። በያላችሁበትም ሰላም ሁኑ።

• ሻሎም…!  ሰላም…!
235.9K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 21:36:09
አለን ለማለት ያህል…

"…በዘመን ውስጥ የምንለወጥ እንጂ ዘመን የሚለወጥብን አይሁን።" እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም በጤና አሸጋገረን አሸጋገራችሁ።"

"…ተወዳጆች ሆይ ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።" መክ 3፥1 እናም አምላካችን ሆይ፣ ስለ እናትህ ብለህ፣ ስለ ቅዱሳን መላእክቱ፣ ስለ ቅዱሳን ነቢያት፣ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ስለ ቅዱሳን ሰማእታቱ ብለህ …"መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይበለን።" መዝ 90:15።

"…እንደተነገረንም እንደተስፋው ቃል 2015 ዓም የኢትዮጵያ ትንሣኤዋን ብሥራት የምንሰማበት ዘመን አድርግልን። መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይበለን።" መዝ 90:15። አሜን…!!

•… ታዲያ ነገ በድሮው በበግ ዋጋ የገዛችሁትን ዶሮ እናንተ ሰብሰብ ብላችሁ ስትበሉ፣ ስትጠጡ፣ ምራቁን እያዝረበረበ በመጎምጀት ከበራፍ ከደጃፋችሁ ላይ የቆመ እንዳለ እና እንደሌለ አስተውሉ። መልካም ዓውደ ዓመት። ምሕረት ለኢትዮጵያ…!!

"…ማስታወሻ፦ ደነኅና ነኝ። እግዚአብሔር ይመስገን። ተሽሎኛል። ስልክ ለምትደውሉልኝ ስልካችሁን የማልመልሰው ማውራት ስለማልችል ነው። ለመልእክቶቻችሁም ምላሽ የማልሰጠው ከስልኩ አካባቢ ራቅ ስላልኩ ነው። ይቅርታ…!!
69.1K viewsedited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 22:05:41
"…እንደ ከዚህ ቀደሙ፣ እንደ ልማዴ በሜዳ በመንደሩ እንደ ልቤ እየፈነጨሁ እንዳልበጠረቅ ክፉኛ ስላመመኝ ፍሬን ለመያዝ ተገድጃለሁ። ሆኖም ግን እነ ሰበር ዜናዎች፣ እነ መቀሌ ራቱ፣ እነ ደሴ ቁርሱን ሁለቱንም በጥራቆች በተወሰነ መልኩ በልካቸው ይበጠረቁ ዘንድ የበኩሌን አስተዋፅኦ በማድረግ እንዲያቀዘቅዙ ለማድረግ ጥሬአለሁ።

"…መሬት ላይ ያለው ሃቅ ሌላ ነው። አዲስ አበባ የሚደሰኮረው ሌላ ነው። ከሁለቱም ወገን እንደቅጠል ረግፏል። ከዚያ ደግሞ ስለ ሰላም ሲባል ተብሎ ወያኔ ከራያ እንደተዘፈዘፈች የተኩስ አቁም ስምምነት ይፈረማል። ያኔ ዛሬ ስለ ሰላም የሚያቅራሩት ይኮነኑ እና የጦርነት ነጋሪት ጎሳሚዎቹ እነ ጋሽ ደርቤ በተራቸው የሰላም ሐዋርያ ሆነው ይከሰታሉ። ዐቢይ ህወሓት እንድትጠፋበት አይፈልግም። በእሷ ሰበብ ኢትዮጵያን እጁ ላይ ማሟሟት ነው የሚፈልገው።

• እንደምታዩት ጦርነት አውዳሚ ነው። ጦርነቱ ዐማራን የማውደም ባይሆን ኖሮ በደሌ ከተማ ለመግባት 27 ኪሎ ሜትር ለቀረው ኦነግም ላይ ይዘመት ነበር። ማርያምን ባያመኝ ኖሮማ አሳይህ ነበር።

• እውነት ብቻ…!!
94.2K viewsedited  19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 18:35:49
ዳቦን ተቆጣጥረዋል…!!

"…የዐቢይ ሽመልሱ ዐማራ ማጽጃ የግል ማሽን የሆነው ኦነግ ዛሬ በበደሌ ዞን ዳቦ ወረዳን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረዋል። የራሳቸውንም አስተዳደር እየሾሙ ወደ በደሌ ከተማ እየገሰገሱ መሆናቸው ተነግሯል። ከዳቦ በደሌ 27 ኪሎ ሜትር ብቻ ነው ርቀቱ።

"…በበደሌ ከተማ ሥራም እንቅስቃሴም በሙሉ ሙሉ በሙሉ መቆሙ ነው የሚነገረው። በበደሌ ዞን ጨዋቃ ወረዳም በእነሱ ቁጥጥር ስር ነው። ደጋ ወረዳም 3 ቀበሌ በእነሱ እጅ ነው። ነገ ደግሞ የት እንደሚደርሱ እነሱና መንግሥት ተብዬው ናቸው የሚያውቁት።

"…በራያ በኩል ወደፊት የሚገሰግሰው የጥምር ጦሩን ባለህበት ቁም እያለ ሙትና ቁስለኛ ሠራዊት እያፈራ ያለው የራያ ግንባሩ ጦር በጊዜ መላ ካልተበጀለት በቅርቡ የራያን ህዝብ ከምደረ ገፅ እንደሚያጠፉት ሊታወቅ ይገባል።

"…በሌላ በኩል በዐቢይ አህመዷ በልጻጊዋ ኢትዮጵያ በዛሬው የጷጒሜን ፬ቱ የአገልጋይነት ቀን ሦስት ሚንስትር መሥሪያ ቤቶች ከነ ሚንስትሮቻቸው የዲታ ልጆች መዝናኛ የሆነውን የእንጦጦ ፓርክ ሲያጸዱ ውለዋል። የዐቢይ የአገልጋይነት መንፈስ እኮ አንዴ አያግኛችሁ። በቃ እንዲህ ፓርክ ለፓርክ ሶፍትና የሃይላድ ፕላስቲክ ሲያስለቅምህ ነው የሚውለው።

"…ለማንኛውም እነዚህኞቹ እንደወያኔ አያሰጉም ካልተባለና በሰከንድ ውስጥ የሚጠፉ ናቸው ተብለወ ካልተናቁ በቀር በኦሮሚያም እየተፈናቀለ፣ እየፀዳም ያለው ዐማራው ነው።

• እውነት ብቻ…!!
98.0K views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 18:03:23
"…አንዳቸውም የዐቢይ አሕመድ አክቲቪስቶች ስለዚህኛው በኦሮሞ ስም ዐማራን ከኦሮሚያ ምድር እያጸዳ ስላለው ኃይል የሚተነፍስ የለም። በራያ ግንባር ወደፊት ሄዶ ማጥቃት አይፈቀድም። የራያ ገጠሩ እያለቀ ነው። ወያኔና ዐቢይ በጋራ ተባብረው እያጸዱት ነው። በወለጋና በኢሉአባቦር ደግሞ ይኸው እንደ ጉንዳን የሚርመሰመሰው ኃይል ዐማራውን እያጸዳው ነው። ለጊዜው ዓይኖች ሁሉ ወደ ሰሜን ስላተኮሩ በኦሮሚያ እየተፈጸመ ስላለው ነገር ማንም ጆሮ ሰጥቶ የሚያዳምጥ የለም።

• ድሮኗ እኮ የወገን ጦር አትነካም…
90.7K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 17:36:02
የመዓዛና የጎበዜ ክስ ታውቋል።

• ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ…

"…ሕገ መንግሥቱን እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የፈጠረችው እኮ ራሷ ወያኔ ናት። ጥብቅናው ለማነው? … በቃ ይሄን የወያኔ ሕገ መንግሥት መናድ አይቻልም ማለት ነው አይደል?

"…ዐቢይ ራሱ ወያኔ ነው…!!
88.8K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 16:47:15
በማይጠብሪ ግንባር።

"…ዛሬ ውጊያው ቡያ ማዶ አድጎባይ እና አድቀይህ፣ አቀብሰሎ ነው ያለው። ጥምር ጦሩ እስከአሁን በዚህ ግንባር ከህወሓት ጦር ያስለቀቃቸው ሥፍራዎች፦

• ጥሎባታ
• አባማር
• ማይልሃም
• መይቃንጫ
• ማይርጋብ
• ቡያ እና
• ምዝክር ኪዳነምህረት ናቸው። ሽሬ አክሱም የነ ናቲ ቀደዳ ነው። በዚህ ግንባር ያለው ወታደራዊ ዲሲፒሊን እጅግ አስደናቂ ነው። በሰማይም በምድርም ሁሉም ተናበው ነው የሚሠሩት። በሰቆጣ ግንባርም እንደዚያው። እንቆቅልሽ የሆነው የራያው ግንባር ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

• እውነት ብቻ…!!
89.1K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 15:09:31
"…መቀሌ አይደለም። በሂዊ የተፈጸመ። ወይ ደግሞ መቋዲሾም አይደለም። በአልሸባብ የተፈጸመ። እዚሁ ወለጋ ነው ነቀምቴ አካባቢ። ጣሊያን ራሷ ይሄን ብታይ በሳቅ ነው ጦሽ ብላ የምትፈነዳው። ባንዳ ሁላ… !!

• ኢትዮጵያ… !
98.4K viewsedited  12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ