2022-09-24 13:06:26
ከላይኛው የቀጠለ…
ለመደገፍ እምብዛም አጋዥ ለመሆን ፈቃደኞች አይደሉም። በሀገር ማኩረፍ ልክም ተገቢም ባይሆን ነገር ግን ደግሞ የወያኔን ሕገ መንግሥት ታቅፎ ወያኔን እዋጋለሁ ለሚል አገዛዝ ምን ተብሎ ይደገፋል። እኔ በዳያስጶራውም አልፈርድበትም።
"…ብድርም፣ እርዳታም ያጣው የሰባኪው የዐቢይ አሕመድ መንግሥት አሁንም በሰፊው የብር ህትመቱ ላይ ቀጥሏል። ብር ሲታተም ደግሞ ብር ወደ ወረቀትነት ክብር ይወርዳል። ብርን ያስከበረው እንደወረቀትም እንዳይቆጠር፣ ዋጋና ክብር እንዲኖረው ያደረገው እኮ ኢኮኖሚው በሚፈቅደው መልኩ ሥራ ላይ መዋሉ ነው እንጂ ሲጠርርብህ ሩጠህ ብር ማተሙ እኮ አይደለም። ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ”የብር የመግዛት አቅም አንሷል የምንለው በጥቁር ገበያ እና በባንኮች የብር ምንዛሬ መካከል የሰፋ ልዩነት ሲታይ ነው። ይህ የሚያሳየው ደግሞ በገበያ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትና አቅርቦት ከፍተኛ አለመመጣጠን ስለሚታይበት ነው” በማለት ያስረዳሉ።
"…ለዚህ ነው አንድ ዶላር አንድ መቶ ብር፣ አንድ የኩዌት ዲናር ደግሞ ሦስት መቶ ስምንት ብር እየተመነዘረ የሚገኘው። የፓውንድ፣ የዩሮ ምንዛሪ ስንት እንደሆነ አላወቅኩም። ይሄ ከባድ አደጋ ነው። ብር መታተሙን የምታውቁት ከንቲባ ወሮ አዳነች አቤቤ በየዕለቱ በየደረሰችበት ሥፍራ ሁሉ፣ የእናቷ ቆሎ ይመስል ከመንግሥት ካዝና እየዘገነች በየዕለቱ ሰጠሁ፣ ለገስኩ የምትለውን ሚልዮን ብሮች ማየቱ በቂ ምስክር ነው። የድግስ ስሟ ተቀይሮም "ማዕድ ማጋራት" የሚል የዳቦ ስም ተሰጥቷታል። የትኛውም የብልጽግና ስብሰባ "ካለ ማዕድ ማጋራት" ማከናወን አይቻልም። የራበው ካድሬ በሙሉ ካልበላ እንዴት ይሰብሰብ ብላችሁ ነው። የሆድ ጥያቄ ሚኒስትሮቹም ዘንድ በኃይለኛው አለ ማለት ነው። አዲስ አበባ ነዳጅ አታፈልቅም፣ ወርቅ አታመርትም ነገር ግን በዘመነ ታከለ ኡማና በዘመነ አዳነች አበቤ የከተማ አስተዳደሩ በዓለም ላይ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ የማያልቅ ሚልዮን ብሮችን ሲበትንና የሌለ ለጋስ ሲሆን ይታያል። አይገርምላችሁም…?
"…የቀረው ቀርቶ፣ ሌላውን ሳንቆጥር በትናንቱ የቅዱስ ጊዮርጊስና፣ የኢትዮጵያ ቡና የቅሪላ ማልፋት መርሀ ግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደ ሌሎቹ የክብር እንግዶች ጨዋታውን ተከታትለው ዝም ብለው አልወጡም። ለሁለቱ ክለቦች 10 ሚልየን ብር ለግሰው፣ አስጨብጭበው ነው የወጡት። ገና እነ መድህን፣ ባንክ፣ መቻል፣ ሌሎቹም የአዲስ አበባ ክለቦች ልገሳውን ይጠብቃሉ ማለት ነው። እነ ኤልፓም ዝም አይሉም። ይሄ ነው እንግዲህ ሃገር መምራት። አስቂኝም፣ አሳዛኝም የሚያደርገው። ወታደሩ ባዶ ሆዱን ይሰዋል፣ አካሉ ይጎድላል ለፊርማ በሚልዮን የሚቆጠር ብር ተቀብሎ ቅሪላ ለሚያለፋ ጎረምሳ 20 ሚልዮን ብር ዘግና ትሰጣለች። ትንሽ እንኳ እኮ አይሸክካትም።
"…በዚሁ ከቀጠልን ብር ወረቀት ይሆናል። ክብሩን ያጣል። ነዳጅ ለመግዛት አቅም ያንሳል። ነዳጅ ከሌለ ደግሞ ምንም አይኖርም። ለግብርና ግብአት፣ ለጤና፣ ለመሠረተ ልማት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማስገባት ያቅታል። 120 ሚልዮን ህዝብ መመገብ ያቅታል። አምራቹ ገበሬ ከሞተ፣ ከተፈናቀለ፣ ከተሰደደ ህንፃው ምግብ አይሆንም። ድንጋይ አትበላም። እርስ በራስህ ትበላላታለህ እንጂ። ለዐማራ ያላመረተውን እህል ይሰፍርበት ዘንድ ጣሳ እያደልክ ለኦሮሞ ትራክተርና የውኃ መሳቢያ ሞተር ስላደልክ ይሄን ክፉ ዘመን አትሻገረውም። ነገሩ ከባድ ነው። ቆም ብሎ ማሰብ፣ ካድሬን አስወግዶ ባለሙያ መመደብና ከዚህ ጭንቅ የሚወጣበትን መፍትሄ ለማምጣት ሥራ መጀመር ይሻላል ባይ ነኝ።
"…ትናንት ቢጨንቀው የኢትዮጵያ መንግሥት የፌደራር መንግሥት የሴት ሚኒስትሮች የእርሻ ማሳ ጎበኙ የሚል ዜና ይዞ ወጥቶ ሲያሯሩጥ አየሁ። https://www.facebook.com/123960474361367/posts/pfbid02XitfwWo2UQqm7YG9jFoC8qw5UVGxbJgCgzZii1772GQKCDnoP6eutzrz83vTyNXWl/ ወለጋ እኮ ምርት የለም። ሰሜን ጎንደር፣ ዋግኽምራ፣ ሰሜን ወሎ ምርት የለም። እዚህ ደብረዘይት እና አሩሲ ላይ ድሮም ጥንትም የነበረ የኖረ እርሻ እየጎበኙ፣ ፎቶም እየተነሡ ራስን ማታለል ሞኝነት ነው። ሴት ሚኒስትሮቹ እርሻውን ስለጎበኙ እኮ ምርቱ አይጨምርም። እንደው ቢጨንቅ፣ ግራ ቢገባቸው እኮ ነው።
"…በኢትዮጵያ የሥራ መነሻ ደሞዝ 2,500 ነው ይባላል። የቤት ኪራይ መነሻ ዋጋ ደግሞ 4,500 ነው። ተመልከቱ ሁለት ልጅ ያለው አይደለም አንድ ብቻውን የሚኖር ወንደላጤ እንኳ እንዴት ነው ኑሮን የሚዘልቀው? የምግብ ዋጋ ስንት ነው? ዳቦ እንኳ በአቅሟ ስንት ነው የገባችው? ህክምናን ትታችሁ የትራንስፖርት፣ የልጆች ወጪ ሲጨመርበት ደግሞ አስቡት። ብዙ የመንግሥት ሠራተኞች ምሳ መብላት እንዳቆሙ እየሰማን እኮ ነው። ባዶ ሆዱን አንጀቱን ቋጥሮ የመጣው ሰውዬ ያለ ጉቦ፣ የለ እጅ መንሻ አልሠራም ቢል ምን ትፈርዱበታላችሁ? ነገርየው ከባድ ነው።
"…ለምሳሌ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን ጉዳይ እዚህ ላይ ላንሣ። የአሩሲዋ እመቤት ከንቲባ አዳነች አበቤ ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ክራይ ድጎማ አድርጋለች። ይሄ ድጎማ ግን የአዲስ አበባን ፖሊስን ለይታ ተወችው። አሁን ፖሊስ ነፍሴ ችግር ላይ ነው። የአዲስ አበባ ፖሊስ የሆነ ሰው መልቀቂያ ከተከለከለ 5 ዓመት አለፈው። መልቀቅ አይችልም። በዚህ ባለው ደሞዝ ደግሞ መኖር ከብዶታል። በተለይ አባላቱ ላይ የከፋ ነው ተብሏል። ሁሌ እስታንድ ባይ ብለው ያለ እረፍት ነው የሚያሠሩት። በእንዲህ ዓይነት ሰቀቀን መኖር ከጀመሩ ድፍን ሁለት ዓመት እንዳለፋቸው ይናገራሉ። መኖር አቃተን፣ ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ነው የሚሉት። ቢያንስ መልቀቂያ የሚከለክል ሕግ በሌለበት ሃገር መልቀቂያ ተከልክለን እየተሰቃየን ነው ያለነው ነው የሚሉት። የአዲስ አበባ ፖሊስ ሆነው የመብት ጥያቄ የሚያነሡ በሙሉ ታፔላ ተለጥፎባቸው ይታሰራሉ። ይሄ አደጋ አለው።
"…ፖሊስ እየራበው አይሠራም። የሚሠርቅ፣ የሚዘርፍ ቡድን የቋቁማል። ከዚያ በሬህን ከሠረቀህ ጋር ለፍለጋ ስትሯሯጥ ትኖራለህ። በትግሬዎች መታሰር የከበሩ መርማሪ ፖሊሶች፣ የጣቢያ ኃላፊዎች የትየለሌ ናቸው ይባላል። ትግሬዎቹ ገንዘብ አላቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ስንቱን ምስኪን ጁንታ ነህ ብለው አስረው በአፅሙ አስቀርተውታል። ብር ሲጠርራቸው ትግሬ እየፈለጉ ልናስርህ ነው ብለው ስንቱን ትግሬ ባዶ ኪሱን አስቀርተውታል። እናም ፖሊስ ራበኝ ሲል አደጋ አለው። የዛሬውን የኢቢሲ ዘገባ ተመልከቱ። በኦሮሚያ ታርጋ መዝረፍ ቀላል ነው። https://www.facebook.com/541629952535552/posts/pfbid0zcQtRbfmBkRdt497aG6uQag45VQ5mmYXzpZCiP7KBTy3xo5QAqj9ALuBA334zkHil/
"…በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በደብረ ታቦር፣ በወልድያ፣ በደሴ፣ በአዲስ አበባ የተከማቸው ቁስለኛ ወታደርም እየቆየ ሲሄድ አደጋ መፍጠሩ አይቀርም። የመድኃኒት ወጪውም ከባድ ነው። ቤተሰብም ደሞዝ ይጠብቃል። የጡረታ ገንዘብም ይፈልጋል። እናም ሌላ አድቫንቴጅ እያሰቡ፣ ሰሜኑን በማድቀቅ ሽባ የሆነች ኢትዮጵያን እንዳሻን እንገዛለን ብሎ የሌለ የሴራ መንገድ ከመከተል ጦርነቱን በጊዜ አጠቃልሎ የተረጋጋ ኢኮኖሚና ሃገር ወደመፍጠሩ መሄዱ ይበጃል ባይ ነኝ።
"…ቆይቼ ደግሞ እመለሳለሁ።
12.9K viewsedited 10:06