Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ…!! '…ዛሬ በደመራው በዓል ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሰንበት ተማሪዎ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ…!!

"…ዛሬ በደመራው በዓል ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሰንበት ተማሪዎች ከምር አሰለቀሱኝ። ብቻዬን ነው መርዶ እንደሰማ ሰው ስቅስቅ ብዬ እንዳለቀስ ያደረጉኝ። የደስታ ልቅሶ። የደስታ እንባ። አባቴም እናቴም ሞተው በዚህ መጠን አላለቀስኩም። ከምር ተባረኩልኝ። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተዋሕዶ አምላክ ብድራቱን ይክፈላችሁ።

"…ልዕልት ዕሌኒ ቅዱስ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ቆፍራ እንዳወጣችው ነው እናንተም ዛሬ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከተቀበረበት ሥፍራ አውጥታችሁ በኦነጉ የኢትዮጵያ ሚንስትር በቀጄላ ፊት ያውለበለባችሁት። የብልጽግናው መንግሥት የኦሮሙማ ወታደሮች ህዝቡን በሃገሩ ሰንደቅ ዓላማ እንዳያጌጥ ቢያደርጉትም፣ ቲሸርት ሳይቀር አውልቅ ብለው ቢያስጨንቁትም። ከዐውደ ምህረቱ ላይ ሰንደቋን እንዳትታይ ቢያደርጓትም እናንተ ግን በጥብዓት ገለጣችኋት። በቀጄላ መርዳሳ፣ በቅርቡ በዐቢይ አህመድ ሚስት በጎንደሬዋ ዝናሽ ታያቸው ጎትጓችነት ጴንጤ በሆነችውና ከጥብቅ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰቦች በተገኘችው በአዳነች አበቤ ፊት ለፊት ኢትዮጵያን ገለጣችኋት።

"…ኡፍፍፍ እንዴት ብዬ ደስታዬን ልግለጠው? ቃላቶች ሁላ ሽባ ሆኑብኝ። ከኃጢአት የራቀ ረጅም የአገልግሎት ዘመን ይስጣችሁ። ዕድሜ፣ ጤና፣ ሃብቱን አንዱም ሳይጎድል እግዚአብሔር ይስጣችሁ። ሰላማዊቷ ተዋሕዶም የደመራ በዓሏን በመላው ኢትዮጵያ በሰላም ማክበሯን እንደቀጠለች ነው።

"…አዛኜን እውነቴን ነው ኢትዮጵያማ ትነሣለች።