2022-09-24 13:05:49
"…ትናንት ከሰዓት በኋላ ላይ በሃገረ ኩዌት በሥራ ላይ ያለች አንዲት አብሮአደግ እህቴ ትደውልልኛለች። የተለመደውን የቤተሰብ ጉዳይ አወጋን። ሴቷ ፌስቡክም፣ ቴሌግራምም የምትከታተል አይደለችም። ለሃገሪቱም የፖለቲካ ጉዳይ ባዳ ናት። ሲጀመርም መስማትም፣ ማየትም የማትፈልግ ዳተኛም፣ ቸልተኛም እህት ናት።
"…እንዲያና እንዲህ እያልን ስለ አንዳንድ ጉዳዮች ስናወጋ ቆየን። የሚገርመው ነገር ግን ይህቺ የምላችሁ እህት አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ስላለው ጦርነት እንኳ የምታውቀው አንዳች ነገር የለም። እንደ አዲስ ነው የምትጠይቀኝ። ቆይቶ ግን እየፈነጠዘች እንዲህ አለችኝ። "…ይኸውልህ ዘመዴ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ በዝግጅት ላይ ነኝ። የሚገርምህ ትናንት የኩዌት ዲናር ዘርዝሬ ወደ ኢትዮጵያ ልኬ ነበር። አንዱ የኩዌት ዲናር በኢትዮጵያ በስንት እንደሚመነዘር ታውቃለህ? አለችኝ። አላውቅም አልኳት። አንዱ ዲናር በ308 የኢትዮጵያ ብር አለችኝ። እና አንቺ ስንት ላክሽ አልኳት? 300 ዲናር አለችኝ። ትፈነጥዛለች አይገልፀውም።
"…300 ዲናርን በ308 የኢትዮጵያ ብር አባዛሁት። የመጣልኝ ድምር 92,400 ብር ሆነ። ነገር ዓለሙ ለማይገባት እህቴ በ300 ዲናር 92 ሺ ብር ማግኘቷ ቢያስደስታትም ሃገር ግን ወዴት እያመራች፣ የብር የመግዛት አቅም እንዴት በአፍጢሙ እየተደፋ፣ በአናቱ እየተፈጠፈጠ እየመጣ እንደሆነ አልሀገባትም። እንዲያው ሰሞኑን ሊጨምር ይችላል ስለተባልኩ ይዤዋለሁ ሁላ አለችኝ። በመጠኑ እየሆነ ያለውን ነገር ነግሬያት፣ አደጋው ለሃገር ከባድ እንደሆነ ነግሬያት፣ በፈንጠዝያዋ ላይ ውኃ ቸልሼባት ተለያየን። እንግዲህ ጓደኞቼ ነገርየው በዚሁ ከቀጠለ በቅርቡ አንድ የኩዌት ዲናር በ5 መቶ ወይም በ1ሺ የኢትዮጵያ ብር መመንዘሩ አይቀርም ማለት ነው። ዶላር፣ ፓውንድና ዩሮም እንደዚያው።
"…አሁን ስለ ጦርነቱ መጻፍ ፍረጃው ከባድ ነው። በዚያ በኩል ፀረ ህዝበ ትግራይ ያስብላል። ያስፈርጃል። በእኛ በኩል ደግሞ ተማረከ፣ ደመሰስን፣ ወቀጥነው የሚል ሃረግ ካልተጨመረበት በቀር ጁንታ፣ የወያኔ ተላላኪ ተብሎ ያሰድባል። እንደመፍትሄ የያዝኩት በዚህ መንገድ የጀመሩት ይቀጥሉበት። እነ ደርቤ ይዘግቡት። እኔ ግን በተቻለ መጠን የጦርነቱ ጉዳት በሃገርና በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳትና ውድመት በስሱ እየዳሰስኩ እሱ ነገር ላይ ባተኩር ይሻለኛል ብዬ ምርጫዬን አስተካክያለሁ። የከፋ ነገር ሲመጣ፣ ውሸት ሲበዛ ግን የደረሰኝን መረጃ ይፋ አላደርግም ማለት አይደለም።
"…የዩክሬንና የሩሲያን ጦርነት ተመልከቱ። ዩክሬን ነዳለች፣ ፈርሳለች። ተቃጥላለች። ህዝቧ ተሰዷል። ነገር ግን ጦርነቱ ሊቆም አልቻለም። አሜሪካ እና የአውሮጳ ኅብረት ዩክሬንን ታይቶ በማይታወቅ በጀት እና የጦር መሣሪያ አቅርቦት ለአፍታም ያህል ስላልተለዩዋት ሃገሪቷ ብትዳሽቅም የስንቅና ትጥቅ አቅርቦቱ ስላለ በጥቂት ሰውም ቢሆን ጦርነቱ ቀጥሏል። በኢትዮጵያም እንደዚያው ነው። ህወሓት ላለፉት 50 ዓመታት አንድ ቀን አደጋ ይደርስብኛል በሚል እሳቤ በትግራይ የጦር መሣሪያ የመማምረት ያህል ስትቀብር ነው የኖረችው። በሩ ቢዘጋብኝ ተተኳሽ ላይኖረኝ ይችላል በሚል ትግራይን የጦር መሳሪያ ዲፖ አድርጋ ነው የቆየችው። የስንቅ ችግሯን ከነ ነዳጁ ምዕራባውያኑ እየቻሉት ውጊያው ቀጥሏል። ነዳጅና ስንቁ ሲያልቅ ደግሞ ጥቂት ፋታ ተወስዶ እረፍት ይደረግና ይገባበታል። እናም አዙሪቱ ይቀጥላል። ምንአልባት ተዋጊ ሲያልቅ ካልቆመ በቀር ህወሓት እያለች ጦርነቱ አይቆምም።
"…አቅም ያላት ሩሲያ እንኳ አሁን በቻይና፣ በኢራንና በኮርያ መረዳት ጀምራለች። የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ጦርነት በአጭሩ ካልተቋጨ ዳፋው ለዩክሬንና ለሩሲያ ብቻ አይደለም የሚተርፈው። ለመላው ዓለም እንጂ። አውሮጳም፣ አፍሪካም፣ በተለይ ነዳጅ እንጂ አንድ ቁና እህል ማምረት የማይችለው የዓረቡ ዓለም ከፍተኛ ድቀትና ውድቀት ትርምስም ይገጥመዋል።
"…እዚህ በምኖርበት ሃገር በጀርመን እንኳ ከፍተኛ ስጋት ነው ያለው። በሱፐርማርኬት ያልጨመረ ነገር የለም። መጪው ክረምት ነው ብርዱን ለማለፍ እንዴት እንደሚኮን ፈጣሪ ይወቀው ተብሏል። ሩሲያ ጋዝ ስላቋረጠች ስጋቱ ጨምሯል። ባለፈው ጊዜ አሜሪካ የህጻናት ወተት አጥታ ከአውሮጳ ሃገራት ለምና መውሰዷ ሲነገር ሰምቻለሁ። ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአውሮጳ ነዳጅ ተወዷል። ለዜና አያበቁትም እንጂ ህዝብ በመንግሥት ላይ ዘወትር ሰልፍ እንደወጣ ነው። በሆሊውድ መገኛዋ በሎሳንጀለስ ከተማ ኗሪው ነጩም ጥቁሩም ህዝብ እንደ ኢትዮጵያ ጎዳና ተዳዳሪ በላስቲክ ቤት በከተማ መሃል ተኮልኩሎ የ8 ደቂቃ ቪድዮ አይቼ ደንግጫለሁ። በኮቪድ የደቀቀው፣ ቀጥሎ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የሚንኮታኮተው ዓለም፣ ተጨማሪ የኢራን እስራኤል፣ የአሜሪካና የቻይና፣ የኮሪያና የአሜሪካ፣ የአውሮጳና የሩሲያ ጦርነት ሳይጨመርበት እንኳ የሚጠብቀው ከፍተኛ ዓለምአቀፍ የኢኮኖሚ ቀውስ ነው። የኒዩክለር ጦርነት ከተጨመረበት ደግሞ አስቡት። እጅጉኑ ይከፋል።
"…በኢትዮጵያም ጦርነቱ በዚሁ ከቀጠለ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ካልተቋጨ አደጋው ደግሞ ከአውሮጳም በእጅጉ የከፋ ነው። ህወሓት በጊዜ እንዲደመሰስ ደግሞ ምዕራባውያኑ አይፈልጉም። ልክ እንደ ዩክሬን ነው ሊረዱት የሚፈልጉት። አገዛዙ ደግሞ በአብዛኛው አፍቃሬ ህወሓት እና የህወሓት ዲቃላ ፍጡርም ስለሆነ ህወሓትን በአጭር ጊዜ ማሸነፍ አይፈልግም። አንዳኛ ሰሜኑ ኦርቶዶክስ በዚህ አጋጣሚ መመንመን፣ መድቀቅ፣ መውደም አለበት ከሚልም ሃይማኖታዊ ፍላጎትም የተነሣ ነው። ሁለቱ ህዝቦች ከደቀቁ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዳግም አይገቡም፣ መጪውን ክፍለዘመን በተረኝነት እኛ ብቻችንን እኛን የምትመስል ኢትዮጵያን ፈጥረን እየገዛን እንኖራለን ከሚል ዕሳቤም የተነሣ ጦርነቱን በጊዜ መቋጨት አይፈልጉም። ታዲያ ለጦርነቱ ወጪው ይቀጥላል። በብሔራዊ ባንክ የሚገኘው ተጠባባቂ የውጭ ምንዛሪም ተሟጦ ያልቃል። እንደ ቸገረው፣ እንደጠረረበት ግለሰብ መንግሥትም ከተገኘበት ልበደር ይላል። በዚህ ዘመን ደግሞ አበዳሪ የለም። ሁሉም ችግር ላይ ነው። ቆይቶ መንግሥት የቤት ዕቃ ልሽጥ ይላል። አየር መንገድ፣ ባንክ፣ ቴሌ ለመንግሥት የቤት ዕቃ ማለት ነው። እሱን ልሽጥ ይላል። ሽጦም የሚገዛው ቦንብ፣ ጥይትና ታንክ ስለሆነ መጨረሻ ላይ አጨብጭቦ ይቀራል። አያዋጣም።
"…አሁን ለጊዜው መከላከያ ሠራዊቱን፣ ጥምር ጦሩን የጎንደር፣ የጎጃም፣ እና የወሎ ህዝብ ወተት፣ እንጀራ፣ እርጎ፣ ዳቦ፣ ጠላና ጠጅ፣ ኮረፌም ጭምር ስንቅ እያቀበለው እየተዋጋ ነው። እስከመቼ የሚለው አይታወቅም። ለተዋጊው ኃይል ይድረስ አይድረስ ባላውቅም ኦሮሚያም ለበዓል ለጥምር ጦሩ ሰንጋ ልኬአለሁ ብሏል። መንግሥት ያቃተውን ስንቅ ማቅረብ ህዝቡ እስከመቼ ይችለዋል? የሚያዛልቅ አይደለም። በውጭ ያለው ዳያስጶራ ደግሞ የኢትዮጵያን ጦር በስንቅ እንዳያግዝ " ትዕቢተኛው፣ ሥጋ ለበሱ ሰይጣን፣ እግረ ደረቅ፣ ኮቴ መናናው፣ የብርሃን ልብስ ለብሶ የተገለጠው ዲያብሎሱ ዐቢይ አሕመድ አቦይ ስብሃትን የመሰለ አራጅ አሳራጅ በይፋ ፈትቶ ለቅቆ በዳያስጶራው ላይ ቀዝቃዛ በረዶ ውኃ ቸልሶበት ለጨጓራ በሽታ ዳርጓቸዋል። ዐቢይ ዳያስጶራውን ውሻ አድርጎ ነው ቅስሙን ሰብሮ የለቀቀው። በሰሜን ዕዝ ላይ ወንጀሉን ያቀነባበረ ዋነኛ ሰው ከነጀሌዎቹ በይፋ ለቅቆ ዳያስጶራውን እናንተ ገንዘብ ስንጠይቃችሁ አምጡ እንጂ ስለሌላው ሥራችን አይመለከታችሁም በማለት ኩም አድርጎ አንገታቸውን አስደፍቶ አዋርዶ ካባረራቸው በኋላ ዳያስጴ እንደ ድሮው የዐቢይን መንግሥት
12.4K views10:05