Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398.62K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 268

2022-09-06 22:23:09
"…አንዳንድ ማዳሞች ደግሞ አሉ እንዲህ እንደ ልጅ፣ እንደ እህት የሚቆጥሩ፣ የሚያቀርቡ፣ የሚያጽናኑ። ሁሏም ማዳም ክፉ ናት ማለት አይደለም። እንዲያውም ከዓረቦቹ ማዳሞች የኢትዮጵያ ማዳሞች አይከፉም ብላችሁ ነው?

"…ሠራተኛዋ የሠራችውን ዶሮ ወጥ የማያስቀምሱ፣ እንጀራ ቆጥረው፣ መሶብና ድስት ቆልፈው የሚሄዱ፣ ብርጭቆ ሰበርሽ ብለው ደሞዝ የሚቆርጡ፣ ማሽን እንጂ ሰው የማይመስሏቸው አሉ የኢትዮጵያ ማዳሞች። ሲወጡ ሲገቡ ልጆች በእርግጫ፣ ባል በጡጫ፣ ሚስት በመውቀጫ የሚነርቷቸው አሉ እኮ በኢትዮጵያም። ዋሸሁ እንዴ?

ማዕተብሽን ግን እንዳትበጥሺ…!!
27.5K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 22:11:59
አሁን ደግሞ ከማዳም ኩሽና ከዓረቢያ ምድር በቃል ሳይሆን በተግባር ክርስትናን የሚኖሩ ባለ ማዕተብ እህቶቼን እንገልጣለን። የእኔ የማዳም ቅመሞች መሬት ናቸው ሁሉን ቻይ፣ የዐረብን ምድር ፀሐይ፣ የፀሐይዋንም ሙቀት፣ የማዳምን ኩሽና ሁለተኛ እሳት፣ የማዳምን እሳት የሆነ ምላስ፣ ይሄን ሁሉ ነው ታግሰው ችለው የሚኖሩት። በዚያ ላይ የቤተሰብ ናፍቆት፣ ሞላ አልሞላ ሰቀቀን፣ እንቅልፍ ማጣት፣ እረፍት አልባ ኑሮ፣ ይሄን ሁሉ ነው የምትችለው የእኔ ባለማዕተቧ የዓረቢያ ምድሯ አብሪ ኮከብ።

"…በዐረብ ፊት መስቀል አድርጎ በፅናት መኖር ከዚህ በላይ ሰማዕትነት የለም። በሉ የማዳም ቅመሞች ያላችሁበትን ሃገርና ማዕተባችሁን ላኩልኝማ አንድ ሁለት ዙር የእናንተን ለጥፌ ነው የዛሬውን መርሃ ግብሬን የምቋጨው።

ማዕተቤንማ አልበጥስም…!!
30.0K views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 22:01:51
ባለማዕተቡ የጢያራ ሹፌር…!

"…አቤት ግርማ ሞገስ፣ አቤት ውበት፣ አቡነዘበሰማያት፣ ጸሎተማርያም እየደገመ፣ መዝሙር እየዘመረ መብረር ነው። አቤት መታደል በእመቤቴ።

ማዕተብክንማ እንዳትበጥስ ወንድምዓለሜ…!!
31.7K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 21:43:33
እግር ኳስ ተጫዋችም ሁን ብቻ የፈለከውን ሁን። ማዕተብክን ግን እንዳትበጥስ።

የዛሬው ቀን ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርቶታል። እስከዚያው ማዕተቤን አልበጥስም እያልን እንዘምር።
36.2K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 23:45:19
ሸርቤዎቹ ማኮን ተቆጣጥረዋል… !!

"…የዐቢይ አሕመድ እና የሽመልስ አብዲሳ ፕላንB የሆኑት የዐማራ ማጽጃ ማሽኖቹ በዛሬው ዕለት ቡኖ በደሌ ዞን ማኮ ወረዳን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራቸው ተረጋግጧል። ይህ የምታዩት ፎቶ ሹርቤዎቹ በአልጌ ወረዳ ሳቺ ቀበሌን አልፈው ወደ መኮ ሲገቡ ተነሥተው የለቀቁት ፎቶ ነው።

"…ሹርቤዎቹ ከመኮ ወደ ዴጋ ከተማ ጉዞ የጀመሩ ሲሆን ዴጋ ከመኮ በ18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። ሰሞኑን ብቻ በወለጋ የዘር ማጽዳቱን ሥራ በተሳካ ሁኔታ እየፈጸመ ያለው የዐቢይ ሽመልሱ ኦነግ ሸኔ ፊቱን ወደ ኢሊባቦር ዞን በማዞር የዐማራን ዘር እንደቆሻሻ እያጸዳው ይገኛል። ያውም ተቆጭ፣ ገልማጭ፣ አፍጣጭ ሳይኖርበት ማለት ነው።

"…አልጌ ወረዳ ሳቺ ቀበሌ፣ በበደሌ ዞን ዶረኒ፣ የዶረኒን ቀበሌዎች በአጠቃላይ ይዘዋል። ወረቦም በእነሱ ቁጥጥር ስር ነው። ዛሬ መኮ ከተማ የገቡት እስከ ምሽት ድረስ የመንግሥት የአስተዳደር መኪኖችን ሲያቃጥሉ የዋሉ ሲሆን፣ ሲንቄ ባንክ አስቀድሞ ገንዘብ በማሸሹ ምክንያት ምንም ገንዘብ ሲያጡ ሙሉ በሙሉ በእሳት እንዳወደሙት ተነግሯል። እንደ ንግድ ባንክ፣ ኦሮሚያ ባንክ እና አዋሽ ባንክ ብር ሳያስቀምጥላቸው በመሄዱ ምክንያት ነው የሲንቄ ባንክ የተቃጠለው ተብሏል።

"…መከላከያ በቦታው የለም። የኦሮሚያ ልዩ ኃይ ጥቂት ለመታኮስ ሞክሮ ነበር አፈግፍጓል። ህዝቡ ተሰዷል። የአስተዳደር ሓላፈዎቹ ከሳምንት በፊት ከዐማራው ላይ መሳሪያ ሲገፉ ከርመው፣ የገፈፉትን መሳሪያ በወረዳው መጋዘን ከዝነው፣ ዛሬ ሸኔዎቹ ሲገቡ ተተኳሽም፣ መተኮሻውንም በገፍ ተከማችቶ ተረክበውታል። የኦህዴድ ሓላፊዎች ወደ መቱ፣ በደሌ፣ ጅማና አዲስ አበባ ሸሽተዋል። የሞት ዜና እስከአሁን አልተሰማም።

"…የነገ ሰው ይበለን። በጠዋት አንድ መርዶ አረዳችኋለሁ እስከዚያው ደኅና እደሩልኝ።

"…
40.1K views20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 22:24:24
"…ቅዱስነታቸው ወደ ቅድስት ሃገር ጉዞ መጀመራቸው ተሰምቷል።

"…ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሃገረ አማሪካ ሲከታተሉ የቆዩትን ህክምና በሚገባ አጠናቀው ዛሬ በሙሉ ጤንነት ወደ ቅድስት ሃገራቸው ኢትዮጵያና ወደ መንበራቸው ጉዞ ጀምረዋል። መልካም ጉዞ… ይፍቱኝ ይባርኩኝ አባቴ…!!

“… በእግዚአብሔር ዘንድ ተክለ ሃይማኖት ክቡር ነው፤ ዘወትርም መንፈስ ቅዱስ በመቃብሩ ላይ ይረባል። በተክለ ሃይማኖት ወምበር የተቀመጠ ተክለ ሃይማኖት ነው። ”ገድለ ተክለ ሃይማኖት ም61 ቁ9 ገጽ 204። እናም ቅዱስ አባቴ ሆይ ከመናፍቅ… ከተከፋይ ካድሬ… እና ከአክራሪ ነውጠኛው ፀረ ተዋሕዶ አህዛብ ጋርማ ተደርቤ በመቆም ነውረኛ አልሆንም። እንደ ዳንኤል ክብረት፣ እንደ ስዩም ተሾመ እና እንደ ብርሃኑ ነጋ ካልሲ አጣቢው ናትናኤልማ ለባለጊዜዎች ተቀጥሬ ዲዳ ለመሆን በቅዱሱ ላይ አፌን አልከፍትም።

• ቅዱስ አባታችን ሆይ እኔ ዘመዴ… እኔ ቆቱው የሐረርጌው መራታ ዛሬም፣ ነገም፣ ተነገም ወዲያ ከጎንዎ ነኝ። ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጆችዎም በሙሉ ከእርስዎ ጎን ናቸው። ይህ ደግሞ የማይታበል ቃላችን ነው።

• መልካም መንገድ… ይፍቱን ይባርኩን።
16.4K viewsedited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 21:57:59
ይሄ ደግሞ ምን ልሁን ነው የሚለው?

"…የሰሜን ወሎ የሃገረ ስብከቱ የብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ካሜራ ማን ነው። ሙሉ ስሙ ብርሃን በላይ ይባላል። እኔን ነው እንግዲህ በዐማራ ስም የምነግድ የሚያደርገኝ። ጉድ እኩ ነው።  እኔ ግን እሱ ደሞዝ አጥቶ በተራበ ጊዜ በብፁዕነታቸው ትእዛዝ በሚልዮን የሚቆጠር ብር ለምኜ የደረስኩለት ሰው ነኝ።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid021Q3yzfo96Ukixg4nnwRhT5ao2jFUtJ2JQe66nJKqucH5N1eVHqnjrB3ZJJJPxTZil&id=100018096012195

"…ዘመድኩን በቀለ አማራው በውስጥ ችግር እንዲጫረስ አበክሮ እየሠራ ነው። ኹሉም ከመሬት ተነስቶ የዕለት እንጀራ መቁረሻ ያደረገው ሕዝብ #አማራ አላለኝም። እንኳንም ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤርሚያስ እንዲህ ያላሉኝ።

"…በነገራችን ላይ ካሜራማናቸው ከወረፈኝ አይቀር እግረ መንገዴን አንዲት ጥያቄ ልጠይቅ። በዚህኛው ዙር የዋግ ኽምራው ብፁዕ አቡነ በርናባስ እና ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ አሜሪካና ካናዳ ከከተሙ ቆዩ። ምነው በሰላም ነው…? …ወደ ቀደመው ሐዋርያዊ ተግባር ቢመለሱ መልካም ይመስለኛል። አሜሪካና ካናዳ ይደረስበታል። ካሜራማኑ ጨዋታውን ስላመጣው ነው እኔም በዚያው ወደ ጥያቄ የገባሁት። (ብፁዕ አቡነ በርናባስ ሰሞኑን ወደ ሃገርቤት መመለሳቸውን አሁን ሰምቻለሁ)

"…አይ የካሜራ ማን ነገር… !! ቀጥል እኔም እቀጥላለሁ። ሲርብህ ደግሞ እለምንልሃለሁ። ለማኝ አይደለሁ…? የወሎ ኅብረት ጉዳይ ግን ነጭ ነጯን ሳይፈልግ አልቀረም። አይመስላችሁም?
25.7K views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 19:37:50
የዋግኽምራ የሰቆጣ መረጃ…!!

"…በወለህ መርያም በትናንቱ ወጊያ ብዙ ሰው ሞቷል። ለማስታወስ ያህል የዋግ ሰው ሙሉውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ነው። ይሰመርበት።

"…እንደ መረጃ ምንጮቼ አገላለጽ ከሆነ የህወሓት ኃይሎች ዛሮታን፣ ትያ ኪደነምህረት፣ ወለህ ማወርያም፣ ሀመሲትን ተቆጣጥረው የነበር ሲሆን፣ የላሊበላን ዋናውን መንገድ ለ3ቀናት ያህልም ዘግተው ነበር ተብሏል። ጥምር ጦሩ ከአስከተማ፣ ውረምሽን፣  የጉርባቅንና የቤላን ተራራ በመጠቀም በሰቆጣ አቅጣጫ ባብና ሥላሴን በውቅር በታሊኩ አድርጎ ገብቶ የጠላትን ኃይል በልዩ ሁኔታ መደምሰሱ ተነግሯል።

"…በጦርነቱ ንጹሐን የወለህና የቲያ ሰወች በብዛቱ ሞተዋል፣ ቆስለውማል፣ ህፃናት ጭምር ምንም የማውቁ ተጨፍጭፈዋል። የጠላት ኃይል ውጊያውን መቋቋም ሲያቅተው ወደተፈና ቃይ ካምፕ እና ወደ አርሶ አደሩ ቤት በመግባት እነሱን አሰመትተዋቸዋል። ከአንድ ቤተሰብ ከአምስት በላይ የሞተበትም አለ። ዛሬ የሞተውን ሬሳ ለማንሣትና በክብር ለማሳረፍ ወደ ቀብሩ ህዝቡ ተጠርቶ የነበረ ቢሆንም የተወሰኑ ተቆርጠው የቀሩ የህወሓት ኃይሎች ተኩስ ጀመሩ ተብሎ የወገን ኃይል ተመለሱ  ስላለ ለአስከሬን ለቀማ የተዘጋጀው ህዝብ ተመልሷል።

"…ከላይ የተጠቀሱት ቀበሌዎች በሙሉ ተዘርፈዋል። ልብስ እና ጫማ እያስወለቁ ነው የቀሟቸው። የመጠለያ ካምፕ ገብተው የተረዱትን እርዳታ ራሳቸው ተረጂዎቹን ጭምር እያሸከሙ የተወሰነ ቦታ አድርሱልን በማለት ግፍ ነው የሠሩባቸው። ወደፃግብጅ አቅጣጫ እክመፅርዋ ድረስ ሄደዋል። የመከላከያ ጄኔራሎቹ የብልፅግና አመራሮችን እንዴት ከህዝብ በፊት ትሻላችሁ? ብለው ስለሰደቧቸው ተጨንቀዋል። ቀድመው መሸሻቸውን ለማካካስ ሲሉ ሰርጎ ገብ ከ50 በላይ ያዝን በማለት ንፁሐንን ማሰቃየትም ጀምረዋል።

"…ውጊያውም ሞቱም ቀጥሏል…!!
53.8K viewsedited  16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 18:27:28
እንዲህ ነው እንዴ ነገሩ…?

"…እኔ እኮ ሰሞኑን እነ ሙጂብ አሚኖ በል፣ እነ ተስፋዬ ከበደ አሊ በል፣ እነ ቴዎድሮስ አያሌው በል፣ እነ ቶማስ ጃጀው በል፣ እነ ብሩክ አበጋዝ በል፣ እነ መንግሥቱ ዘገየ በል ከ እስከ በምሬ ወዳጆ ላይ ሲዘምቱ እንዴ ምን ሆነው ነው? ምን ነክቷቸው ነው ብዬ ግራ እየገባኝ ነበር።

"…ፋኖ ሃሰን ከረሙን እያወደሱ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖን እነ ምሬ ወዳጆን እና የቤተ ዐማራን ፋኖ ሲያጣጥሉ ሳይ እንዴ ምን ነክቷቸው ነው ብዬ መደመሜ አልቀረም። ምሬ ኦርቶዶክስ ቢሆንም ምክትሉ እስላም ነው። በወሎ ደግሞ እየወደመ ያሉት ሁለቱም ናቸው። እኔ እኮ ምን ሆነው ነው እነ ሙጂብ፣ እነ ብልፅግና ሃሰን ከሪሙ፣ ሃሰን ከሪሙ ብቻ የሚሉት እላለሁ። ለካስ ነገሩ ወዲህ ነው።

"…ለሃሰን ከሪሙ ስደውል ስልኬን የማያነሡት አሁን አይደል እንዴ የገባኝ። የወሎ ኅብረት ለካስ በዚህ ደረጃ ተደራጅቷል? እኔ መች ገብቶኝ። አያችሁት ይሄን ሰካራም ተንታኝ ተብዬ የወሎ ኅብረት ፈረስ የሆነ ሰውዬ እንዴት የምሥራቅ ዐማራን ፋኖ እና የቤተ ዐማራን ፋኖ ተጋድሎ እንደሚያኮስስ። ወሬያም።

"…እኔ እስከማውቀው ፋኖ አርበኛ ሃሰን ከሪሙን ከሸሹበት ተራራ አውርዶ፣ እሳቸውም ሁለት በሬ አርደው ተቀብለው፣ ልጆቻቸውንም ሰጥተውት ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር ጠላትን በጋራ እንደተፋለሙ ነው። ወሃቢዩና የኦሮሙማው ባለዛሮች ወሎን ክልል ማድረግ ስለሚፈልጉ ብቻ የልጆቹ ተጋድሎ ላይ በረዶ ባይቸልሱ መልካም ነው።

"…እኔ ደግሞ ሰው መስሎኝ በጨዋ ደንብ ማብራሪያ ልጠይቅ ተስፋዬ ከበደ አሊ ጋር በዚህ ስልክ ቁጥር መደወል። +251913043529 እናትህ…… ምንአባህ ታመጣለህ ብሎ ሲያጥረገርገኝ ጊዜና እኔን ብሎ የሀረርጌ ልጅ ብዬ ደንግጬ ስልኩን ዘጋሁት። እናንተንም እንዳይሰድባችሁ እንጂ ከፈለጋችሁ ደውሉለት።

"…እየተጥረገረጋችሁ…!!
62.5K views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 16:53:22
ጥንቃቄ ቢደረግ…!!

"…ለጥምር ጦሩ ስንቅ ማዘጋጀቱ ጥሩ ነው። መልካምም ነው። ነገር ግን በእንዲህ መልኩ የሚዘጋጅ ስንቅ ጥንቅር ብሎ ቢቀር ይሻላል።

"…ፈንገስ አለ። ኢቦላ አለ። ኮሮና አለ። ታይፈስ አለ። ታይፎይድ አለ። ውኃ የለች። ሳሙና ተወዷል። በኮንጎ ጫማ፣ ኧረ ይደብራል። በዚያ ላይ ሙጀሌ አለ። በዚያ ላይ ቁስል አይጠፋም። በዚያ ላይ መግል አለ። እና ይሄ እንዴት በዚህ መልክ ይዘጋጃል?

"…አዘገጃጀቱ ላይ ጥንቃቄ ይደረግ። በተረፈ በርቱ…!! እስላሞች ከጦርነቱ ታቅበው ዱአ ላይ ናቸው። ጴንጤ የጌታ ልጅ ነው አይዘምትም። ስንቁን እስላም፣ ጴንጤና የሆዳም ኦርቶዶክሱ ወገን የሆኑት ያዘጋጃሉ። ከዚያ ባለማዕተቡ ኦርቶዶክሱ ከዚህ ወታደር ሆኖ ከዚያ ወያኔ ሆኖ መጥቶ ይጨፋጨፋል። ማንተጎዳ? ማን ተጠቀመ? መልሱን ለእናንተው። ጴንጤና ኦሮሞ ሆኖ የሚዘምተው ደግሞ አጋጣሚውን ሲያገኝ እጁን አንከርፍፎ ይማረካል። ንግግሬ ትንሽ መረር ትላለች ግን መፍትሄው መዋጥ ብቻ ነው።

"…ምግቡን የምታዘጋጁ ግን ቢያንስ በእግራችሁ ላይ ፌስታል ነገር አሰር ብታደርጉ መልካም ነው። አገላለፄ እንደሚዘጋችሁ አውቃለሁ። ግን ያው የታወቀ በእኔ ቤት የተለመደ ነጭ ነጯን እንደወረደ ምክር ነው።

"…እግር እየታጠብን…!!
68.4K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ