Get Mystery Box with random crypto!

ሸርቤዎቹ ማኮን ተቆጣጥረዋል… !! '…የዐቢይ አሕመድ እና የሽመልስ አብዲሳ ፕላንB የሆኑት የዐ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሸርቤዎቹ ማኮን ተቆጣጥረዋል… !!

"…የዐቢይ አሕመድ እና የሽመልስ አብዲሳ ፕላንB የሆኑት የዐማራ ማጽጃ ማሽኖቹ በዛሬው ዕለት ቡኖ በደሌ ዞን ማኮ ወረዳን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራቸው ተረጋግጧል። ይህ የምታዩት ፎቶ ሹርቤዎቹ በአልጌ ወረዳ ሳቺ ቀበሌን አልፈው ወደ መኮ ሲገቡ ተነሥተው የለቀቁት ፎቶ ነው።

"…ሹርቤዎቹ ከመኮ ወደ ዴጋ ከተማ ጉዞ የጀመሩ ሲሆን ዴጋ ከመኮ በ18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። ሰሞኑን ብቻ በወለጋ የዘር ማጽዳቱን ሥራ በተሳካ ሁኔታ እየፈጸመ ያለው የዐቢይ ሽመልሱ ኦነግ ሸኔ ፊቱን ወደ ኢሊባቦር ዞን በማዞር የዐማራን ዘር እንደቆሻሻ እያጸዳው ይገኛል። ያውም ተቆጭ፣ ገልማጭ፣ አፍጣጭ ሳይኖርበት ማለት ነው።

"…አልጌ ወረዳ ሳቺ ቀበሌ፣ በበደሌ ዞን ዶረኒ፣ የዶረኒን ቀበሌዎች በአጠቃላይ ይዘዋል። ወረቦም በእነሱ ቁጥጥር ስር ነው። ዛሬ መኮ ከተማ የገቡት እስከ ምሽት ድረስ የመንግሥት የአስተዳደር መኪኖችን ሲያቃጥሉ የዋሉ ሲሆን፣ ሲንቄ ባንክ አስቀድሞ ገንዘብ በማሸሹ ምክንያት ምንም ገንዘብ ሲያጡ ሙሉ በሙሉ በእሳት እንዳወደሙት ተነግሯል። እንደ ንግድ ባንክ፣ ኦሮሚያ ባንክ እና አዋሽ ባንክ ብር ሳያስቀምጥላቸው በመሄዱ ምክንያት ነው የሲንቄ ባንክ የተቃጠለው ተብሏል።

"…መከላከያ በቦታው የለም። የኦሮሚያ ልዩ ኃይ ጥቂት ለመታኮስ ሞክሮ ነበር አፈግፍጓል። ህዝቡ ተሰዷል። የአስተዳደር ሓላፈዎቹ ከሳምንት በፊት ከዐማራው ላይ መሳሪያ ሲገፉ ከርመው፣ የገፈፉትን መሳሪያ በወረዳው መጋዘን ከዝነው፣ ዛሬ ሸኔዎቹ ሲገቡ ተተኳሽም፣ መተኮሻውንም በገፍ ተከማችቶ ተረክበውታል። የኦህዴድ ሓላፊዎች ወደ መቱ፣ በደሌ፣ ጅማና አዲስ አበባ ሸሽተዋል። የሞት ዜና እስከአሁን አልተሰማም።

"…የነገ ሰው ይበለን። በጠዋት አንድ መርዶ አረዳችኋለሁ እስከዚያው ደኅና እደሩልኝ።

"…