Get Mystery Box with random crypto!

'…አንድ የኩዌት ዲናር እየተመነዘረ ያለበትን የኢትዮጵያ ብር ስሰማ የጻፍኩት ማስታወሻ ነው። የብር | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አንድ የኩዌት ዲናር እየተመነዘረ ያለበትን የኢትዮጵያ ብር ስሰማ የጻፍኩት ማስታወሻ ነው። የብር የመግዛት አቅም በአፍጢሙ እየተደፋ መሆኑን በማየቴና ቀጥሎ ከባድ የሆነ ታይቶ የማይታወቅ የኢኮኖሚ ቀውስ እንዳይገጥመን በመስጋት እንደ ዜጋ በጊዜ ወደ መፍትሄ ብናመራ ብዬ የጫጫርኳት ጦማር ናት። በዚህ መልኩ መወትወቴን ደግሞ እቀጥላለሁ።

"…ያልቸገራችሁ፣ አገዛዙም የተመቻችሁ የብልፅግና ካድሬዎች ግን ቢቻል ጮጋ ብላችሁ እለፉት። ከተቻለም ሃሳብ ስጡበት። አልያ ግን ስድብ እሳደባለሁ፣ ነውሬን እተፋዋለሁ ብላችሁ ፔጄ ላይ በአፋችሁ ለመፀዳዳት ብትመጡ እቀስፋችኋለሁ። ሰምታችኋል። ይሄ የመወያያ መድረክ ነው። የአስተያየት መስጫውን ሰንዱቅ እንደሌሎች አልቆልፈውም። ሁሉም ሰው ይተንፍስ። ይወያይ። ስድብ ግን ካካ ነው። እፉ ነው።

"…ቆይቼ አንብባችሁ ስትጨርሱ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። በጨዋ ደንብ እንወያይ። ተመስግናችኋል።



http://t.me/ZemedkunBekeleZ