Get Mystery Box with random crypto!

'…እግዚአብሔር ይመስገን። እኔና ቤተሰቤ እጅግ በጣም ሰላም ነን። የቀረው የተለመደው የእኔ ወደ ሚ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እግዚአብሔር ይመስገን። እኔና ቤተሰቤ እጅግ በጣም ሰላም ነን። የቀረው የተለመደው የእኔ ወደ ሚዲያውና ወደ ቴሌግራም ቻናሌ መመለስ እና መጨቃጨቅ፣ መጯጯህ ብቻ ነው። እርሱ ደግሞ በቅርቡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እመለስበታለሁ።

"…ከጷጉሜ 5 ምሽት ወዲህ ከስልክም፣ ከኢንተርኔትም ራሴን ለመጀመሪያ ጊዜ አርቄ አግልዬም ስለነበር በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ላይ ምን እየተከሰተ እንደነበር ምንም ዓይነት መረጃ አልነበረኝም። የባለቤቴን ስልክ የሚያውቁ ጥቂት ወዳጆቼ በባለቤቴ በኩል ደጋግመው መወትወታቸው ምቾት ያልሰጣት ባለቤቴ "አለሁ ብለህ ገላግለኝ" ስላለችኝ ነው ዛሬ ብቅ ማለቴ።

"…የመልእክት ሰንዱቆቼንም ዛሬ ገና ነበር የከፈትኳቸው። እናም ካንገበገበኝ ነገር አንዱ "ዘመዴ፣ ከበውናል፣ ሰዉ ሁሉ ስለ ሰሜኑ ጦርነት ነው ትኩረቱ፣ ሊጨፈጭፉን ነው፣ መልእክቱን አድረስልን፣ ንገርልን የሚል መልእክት ከወለጋ አስቀምጠውልኝ እኔ ግን ከኢንተርኔቱ ዓለም ተቆራርጬ ስለነበር መልእክታቸውን ሳላነበው፣ ሳላደርስላቸውም ቀርቼ አሁን መልእክታቸውን ሳነብ፣ ስመለከት ከተከበቡቱ "ከ40" በላይ የሚሆኑቱ መታረዳቸውን በመስማቴ ከልብ አዝኛለሁ። ይሄ እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው።

"…የወዳጅ የጓደኞቼን የሁላችሁንም መልእክቶች በሙሉ አንብቤአለሁ። ከጠዋት ጀምሮ እሱኑ ነበር ሳነብ ያረፈድኩት። የአንዳችሁም መልእክት አላለፈኝም። ስለ መልካም ምኞታችሁ በሙሉ እጅግ አድርጌ አመሰግናላሁ። በጤናዬ በኩል ግን እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው ፍፁም ደኅና ነኝ። በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሚዲያ ሥራዬም እንደምመለስም ተስፋ አደርጋለሁ። የመምሬ ቄሱንም ቤት መግዛት አለብኝ እኮ። እሱ ነገርም አልተቋጨም። ከስልክ ራቅ ማለቱ ግን ጥቅሙ ለራሴ ነው። ለማንኛውም ቸር ያገናኘን። በያላችሁበትም ሰላም ሁኑ።

• ሻሎም…!  ሰላም…!