Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398.62K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 272

2022-09-02 18:12:23
…ገባ ገባ በሉማ ልንጀምረው ነው።





• https://rumble.com/v1id8z5--ethiobeteseb-.html

"…ትናንት በዕለተ ሐሙስ መርሀ ግብራችን የጀመርነውንና ለዛሬ በይደር ያቆየነውን መርሀ ግብር በ" የእኛ ቤተሰብ ሚዲያ በኩል እናቀርብላችኋለን። ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው ከሃገረ ማርያም (ሜሪላንድ አማሪካ) እኔም ዘመዳችሁም ከሀገረ ጀርመን ከራየን ወንዝ ማዶ ሆነን እንጠብቃችኋለን።

• የስደተኛው ካህን ጉዳይ ከምን ደረሰ…? ምላሽ ይኖረኛል።
• የታሠሩትም ተፈተዋል። እሱንም እንመለከታለን።

• በተረፈ ዩቲዩብም፣ ፌስቡክም ከማንኛውም መድረክ ቢያገሉኝም የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሰዎች ፦

https://donorbox.org/zemedemedia

https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። የሚቀረው ከእነ ዩቲዩብ የሚገኘው ገንዘብ ነው። እናንተ አምስትም አስርም አቅማችሁ የሚፈቅደውን በዚህ ከለገሳችሁ ኤት አባቱ ዩቲዩብ። እጅ መስጠትማ የለም።

… ሻሎም !  ሰላም !
89.0K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 16:48:07
ጦርነቱ አስከፊ ነው።

"…ይሄን አይቶ ተመልክቶ በዚህ እንደማዘን፣ ይሄማ የካቻምና ነው። ይሄ የዓምና፣ ይሄማ 6 ወር አለፈው ብሎ ፎቶውን ያውቀው ይመስል ኢንተርኔት ካለበት ሆኖ ይሟገታል። እሱ አይዘምትም። የዘመቱት ህጻናት ፎቶውን ካዩት ከውጊያ ያፈግፍጉ እና እንሸነፍ ይሆን ብሎ ይጨነቃል። ይሰጋል። እሱ ልጆቹን አሜሪካና አውሮጳ አስቀምጦ እያስተማረ የራበውን የደሃ ልጅ ወዲ ጀጋኑ እያለ እየፎከረ ያስጨርሳል።

"…የትግሬን ህጻን ከአራስ እስከ ጉልምስናው ድረስ፦

ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ ፍፅም ወይከ የለን
መስመር'ዩ ሓይልና _ህዝቢ'ዩ ሓይልና
ወይከ ኣይንሳዓርን።
     ንከበብ በዛብእ መሬት ይፅበበና
     ኣብ ሥጋና ይቀርቀር ኣስናን ፀላእትና
     ሥጋና ንእሞራ ደምና ውሕጅ ይኹን
     አዕፅምትና ይዳቀቕ ሕሩጭ ኮይኑ ይበተን
     መስመር'ዩ ሓይልና_ ህዝቢ'ዩ ሓይልና ወይከ ኣንሳዓርን።

"…እያስባለ እያዘመረ፣ ሥጋዬን ጅብ ይብላው፣ አጥንቴ ይከስከስ፣ ደሜ ወንዝ ይሁን ብሎ እያዘመረ ይኸው የትግሬ ህጻናትና ወጣቶች ደም እንዲህ በከንቱ ፈሰሰ። እየፈሰሰ ነው።

"…ሄዶ ሄዶ ጦርነቱ በተኩስ አቁም ሰበብ መቆሙ አይቀርም። ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊን በጦርነት አያሸንፈውም። እልቂቱ ይበዛል፣ ቂምና ቁርሾ ይተከላል እንጂ አሸናፊ የለውም። እናም ከውጭ ያላችሁ ፉከራውን ትታችሁ ህወሓትን አደብ አስገዟት። ፉከራ ሞት አይቀንስም።

"…ህወሓትና ልጆቿ እነ ብአዴንና ኦህዴድ ከእናታቸው መታረቃቸው አይቀርም። የሞተ ተጎዳ እንጂ መታረቃቸው አይቀርም። እናም ቆም ብላችሁ አስቡ። ለደብረ ጽዮንና ለጌታቸው አሠፋ ተብሎ ፍጥረት አይለቅ።

"…ኧረ ተመከሩ…!!
91.1K views13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 16:06:00
"…ከፋኖ ጦር ይሸሽ የነበረውን የህወሓት ጦር የተከዜ ወንዝ ወስዶታል ተብሏል። ችግሩ መጥፎነቱም አሁን በሱዳን የሚገኙት ደግሞ አስከሬኑን ለቅመው እነ CNNን እና እነ BBCን ጠርተው "…ፋኖና መከላከያው የትግራይን ዘር እያጠፋ ነው" እንዳይሉ ነው። እሱ ደግሞ አይቀርም። ኧረ ተዉ ተረጋጉ…!!

"…እየጎረፋችሁ…!!

"…ደጋግሜ ተናግሬአለሁ… ለጊዜው የምጠቀመው፣ ሃሳቤንም የምገልፀው፣ መልእክቶቼንም የማስተላልፈው በዚህ የቴሌግራም ቻናሌ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ አንድም ፌስቡክ የማልጠቀም መሆኔም በግልጽ ይታወቅልኝ። ተናግሬአለሁ። ከአጭበርባሪዎች ተጠበቁ።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ

https://t.me/zemede_Discussion
88.2K viewsedited  13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 14:57:10
ወይ እናት ኦሮጲያ…!!

"…በቃ ከሌላ ብሔር ሰው ጠፋ ማለት ነው…?

ጠቅላይ ጦር አዛዥ ........  (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ )
ኢታማዦር ሹም .............. (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ምክትል ኢ/ ሹ................ (#ዐማራ ብልፅግና ፓርቲ)
ምድር ጦር...................... (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ሰሜን ዕዝ ...................... (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ምዕራብ ዕዝ.....................(ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ደቡብ ዕዝ .......................(ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ምሥራቅ ደቡብ................. (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
አየር ሀይል ሓላፊ...............(ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ምክትል አየር ሀይል .......... (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ፌደራል ፖሊስ ................. (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ፖሊስ ኮሚሽን................. (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን .... (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ዐቃቤ ሕግ ..................... (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)
ጠቅላይ ፍርድ ቤት........... (ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ)

"…የታንኩ ይህን ይመስላል… የባንኩስ ምን ይመስል ይሆን?
91.2K viewsedited  11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 14:05:32
"…ምርኮን በተመለከተ… እዚህም እዚያም አለ። ሙትና ቁስለኛን በተመለከተ… እዚህም እዚያም አለ። ነገርየው ጦርነት እንጂ እግርኳስ አይደለም። ነፃ ትግልም አይደለም። በጦርነት ሞት፣ መቁሰልና እድለኛ ከሆን ቆስለህም ትማረካለህ።

"…ህወሓት የምትማርከው ፕሮፌሽናል ወታደር ነው። የእኛ መንግሥት ደግሞ የምታዩዋቸውን ህጻናትና እናቶች። በግምባር የነበረ ወታደር እንደነገረኝ ከሆነ ልጄን የሚመስል ህፃን እየከነፈ ሊወጋኝ ሲመጣ ልጄን የምገድል እየመሰለኝ የተጨነቅኩትን ጭንቀት እኔና ፈጣሪ ነን የምናውቀው እንዳለኝ አስታውሳለሁ።

"…ትቆረጣለህ፣ ተተኳሽ ያልቃል ከዚያ ትማረካለህ። በቃ የሆነው ይሄው ነው። ጦርነቱ ይቀጥላል። ከኋላ ደጀን ያለው እየተካ ይቀጥላል። በመጨረሻም ያለቀው አልቆ የጦሩ አዛዦች በማዕረግና በደሞዝ ይንበሻበሻሉ። የሞተው ይሞታል። አሞራና ጅብ ይበላዋል። የቆሰለም ወይ ይሞታል። ወይ ደግሞ ይተርፍና የጠፋ አይኑን፣ የተቆረጠና የተጎመደ እግሩን ይዞ ክብር አጥቶ እንደተንከራተተ ይኖራል። ጡረታ እንኳ የሌላቸው ዕልፍ ናቸው።

"…ጦርነቱ ሄዶ ሄዶ በሆነ ስምምነት ይቋጫል። ተኩስ አቁም ተብሎ ይፈራረማሉ። እስረኛ፣ ምርኮኛ ይለዋወጣሉ። የሆነ ቀን መቆሙ አይቀርም። እስከዚያው ግን ከሁለቱም ወገን ከእኛም ከእነሱ ከግንባር የሚለቀቁልንን የሙት፣ የቁስለኛ፣ የምርኮና የወገን የሬሳ ክምር እያየን እንጠብቃለን።

"…እየተማራከችሁ…!! እየማረካችሁም…!!
1.2K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:45:34 የከንቲባው ፍጻሜ…!!

• ቆይቼ የአስተያየት መስጫውን ሰንዱቅ እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው እያነበባችሁ ቆዩኝ።

"…በሰሜን ሸዋ በሸዋሮቢት ከተማ በትናንትናው ምሽት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ባልታወቁ ሰዎች ተመተው መገደላቸው ይታወሳል። ከአቶ ውብሸት በተጨማሪ የአቶ ውብሸት ባለቤትም የተመቱ ሲሆን ነገር ግን ለከፍተኛ ህክምና ወደ ደብረብርሃን ይሁን ወደ አዲስ አበባ ለጊዜው ወዳልታወቀ ሥፍራ ለህክምና መላካቸው እንጂ እስከአሁን የሞታቸው ዜና አልተሰማም።

"…የሸዋሮቢት ከተማ የተለየያዩ ከንቲባዎችን አስተናግዳ ታውቃለች። ከአቶ ውብሸት በፊት አቶ ቴዎድሮስ እና ወሮ ሉባባ የሚባሉ ሁለት ከንቲባዎችም ተሾመው ነበሩ። አቶ ቴዎድሮስ በፋኖዎች የፌስቡክ ገፅ ውስጥ ገብተው በኮመንት መስጫ ሳጥኑ ላይ " አንድ ሞርታር ይዞ መጎረር አይከብድም?" ብለው አስተያየት ከሰጡ በኋላ በደረሰባቸው ውግዘት ተደናግጠው ሥልጣን ለቀው አሁን ሰላማዊ ሰው ሆነው ብስክሌት እየነዱ በሰላም መኖር ከጀመሩ ሰነባብተዋል ነው የሚባለው። ወሮ ሉባባም በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩና በእድገት ወደ ዞን ያደጉ ሴት ከንቲባ ነበሩም ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች። ቀጥሎ የመጡት አቶ ውብሸት ነበሩ።

"…አቶ ውብሸት የተረከቡት የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ በጁንታው የደቀቀ፣ በኦነግ ሴቶቹ የተደፈሩባት፣ ንብረት የተዘረፈባት፣ ዕልፍ ጀግኖች የወደቁባት፣ በአጠቃላይ የኢኮኖሚዋም፣ የሥነ ልቦናም ድቀት የገጠማት፣ ሆደባሻ ከተማን ነበር። ለዚህ በዘርፈ ብዙ ሀዘን ለተመታ ከተማ ህዝብ ደግሞ የሚያስፈልገው የሚያጽናና፣ የሚያበረታታ፣ ለሥራ የሚያፋጥን፣ የሥነ ልቦና ህክምና የሚሰጥ ሰው ነበር መመደብ የነበረበት።

"…መንዝን በቤተሰብ የሚያስተዳድረው አቶ ግርማ የጅብጥላ ግን ይሄን ትእቢተኛ ሰው መደበ። ህዝቡን ሰብስቦ የሚደነፋበት፣ አሳይሃለሁ፣ እቆርጥሃለሁ፣ እፈልጥሃለሁ እያለ እንደ ከንቲባ ሳይሆን እንደ ጀነራል የሚያደርገው፣ ከወፈሩ አይፈሩ ሆኖ ጮማው አዕምሮውን ደፍኖበት በጦርነቱ የሞቱ የፋኖና የሚሊሻ ቤተሰቦች ላይ ሳይቀር እንደግርማ የጅብጥላ ሲያቅራራ ከረመ ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች።

"…ከዚህም አልፎ ዐቢይን ተሳደባችሁ ብሎ የሸዋ ሮቢትን ወጣቶች በጅምላ ፈጃቸው። በቅርቡም ሁለት ወጣቶችን አስገደለ። ግርማ የሺጥላ ለዚህ ጀብዱ ቪ8 መደበለት። በዐማራ ልዩ ኃይልም እንዲጠበቅ ተደረገ። በቃ ሚጢጢዬ አምባገነን ሆነ። ትናንት ምሽት ግን ውብሸት ባልታወቁ ሰዎች ተገደለ። አብረውት የነበሩትና ግርማ የሺጥላ የመደበለት የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት ፖሊሶችም ጥለውት ሸሹ። አላዳኑትምም። አልተከላከሉለትምም። ሚስቱም ተመታች። ቨ8ቱም ቀረ። የግርማ የጂብጥላም ሞራል አብሮ ደቀቀ። ዐማራን ለማዋረድ ይደክም የነበረው አንደበትም ተዘጋ።

"…ከንቲባው ባለፈው የሸዋሮቢት ወጣቶችን ከረሸነ፣ ካስረሸነ በኋላ የሟች ቤተሰቦች ሀዘን እንዳይቀመጡ አስደረገ። ከለከለ። ሁሉም አዘኑበት። ለዚህ ተግባሩም የመንዙ ግርማ የጅብጥላ ጀግና ብሎ ጠራው። አሞካሸውም። ዛሬ በከንቲባ ውብሸት መኖሪያ ቤት ለቅሶ የሚደርሰው አንድም ሰው ጠፋ። ወዳጄ የሸዋ ህዝብ አይጥላህ። እንዲያውም በከንቲባው ሞት የተነሣ ግርማ የጂብጥላ ጦር ይልካል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ከተማዋ የተለመደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋን ቀጥላለች። ቀጣዩ ከንቲባም ከውብሸት ትምህርት የወሰደ እንደሚሆን ይታመናል ይላሉ ሸዋሮቢቶች።

"…አሁን ከዘመነ ህወሓት ጀምሮ 30 ዓመት ሙሉ ብአዴን ሆነው ዐማራ ህዝብ ላይ ያላገጡ ነውረኞች ደንግጠዋል ይላሉ። አያ ግርማ የጂብጥላም ጠባቂ ቁጥር ይጨመርልኝ ብሏልም ተብሏል። በጠባቂ ብዛት ግን አይዳንም። ቤተሰቡ ያለቀበት፣ የታሠረበት ዐማራ፣ የዐማራ ፋኖ ከሸዋሮቢት ትምህርት የወሰደም ይመስላል። ሃዘን ከገባ አይቀር ብአዴኖች ቤትም ይግባ እንጂ ያሉም ይመስላሉ። አባቱ የተገደለበት፣ ወንድሙ የተገደለበት፣ የታሰረበት ሁላ በቀጣይ ወደ ምሥራቅ ወደ ሸዋሮቢት መመልከቱም አይቀርም። ጎን ለጎን ኦነግም አስወግዶት ቢሆንስ የሚሉም አሉ።

"…የሆነው ይሄ ነው…!! የሞቱትን የዐማራ ወጣቶች ግን ነፍሳቸውን ይማር። በቀጣይ እንዲሁ ዘገባ ሲኖር አቀርብላችኋለሁ።

#ማሳሰቢያ፦ ከእንግዲህ ወዲህ በፔጄ ላይ እገሌ ታሰረ፣ እገሌ ታፈነ ብዬ የማልዘግብ መሆኔ ይታወቅልኝ። እንደበግ መነዳት ዜና አይሆንም። ውሻው ሰውዬውን መንከሱ ዜና አይሆንም። የተለመደ ነው። ዜና የሚሆነው ሰውዬው ውሻውን የነከሰ እንደሆን ነው።

"… ጠብቁኝ ቆይቼ እመለሳለሁ…!!
12.4K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:31:19
የከንቲባው ፍጻሜ…!!

"…ለጊዜው የምጠቀመው፣ ሃሳቤንም የምገልፀው፣ መልእክቶቼንም የማስተላልፈው በዚህ የቴሌግራም ቻናሌ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ አንድም ፌስቡክ የማልጠቀም መሆኔም በግልጽ ይታወቅልኝ። ተናግሬአለሁ። ከአጭበርባሪዎች ተጠበቁ።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ

https://t.me/zemede_Discussion
19.2K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 12:01:24 "…ቁጥራቸው አይታወቅም። እርሻና ልጆች ትተው ሊቀመንበሩ በጭካኔ የሚልካቸው ናቸው። መሬትም ሚስቱም የምትወረስ ብዙ ሚሊሻ ነው። ስንቅ የላቸውም። ወታደሩም ልዩ ኃይሉም ሬሽን አለው። ሚሊሻው ግን ያሳዝናል። ሦስት ቀን እህል ያልቀመሱ አሉ። ጫማቸው ኤርጌንዶ ነው። እሱ ተበጣጥሶ እግራቸው ነፍሮ ማየት ያሳዝናል። እናም ቢያንስ የሆዳቸው ነገር እና የተተኳሽ፣ የጫማቸው ነገር ቢታሰብበት መልካም ነው።

፰ኛ፦ የበጀት እጥረት

"…አምና በነበረው ጦርነት የህዝብ የደጀን ተሳትፎ እጅግ ግሩም ነበር። በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም እንደዚያው። ነገር ግን ቀለብላባው እና ንኩ ጠቅላይ ሚንሥትር ተብዬው ለገና የመጡትን ዳያስፖራዎች ውሻ ፈትቶ ለቅቆ ካባረራቸው በኋላ ዳያስጶራውም በብልጽግና መንግሥት አኩርፎ እስከአሁን እንቅስቃሴ የለም። ይሄን ያስተባብሩ የነበሩት እነ ታማኝ በየነንም መንግሥት ውሻ አድርጎ አንገቱንም ቅስሙንም ሰብሮ ስለላካቸው የሉም። ዳያስጶራው አፍሯል። ድጋፉም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ቀጥ ብሏል።

"…በሃገር ውስጥም አምና ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች በሙሉ ከደሞዛቸው ሳይቀር እያዋጡ ይደግፉ ነበር። እነ አዳነች አቤቤ ሁላ ግምባር ድረስ ሄደው ስንቅ ሲያቀብሉ፣ ከዚህም የተነሣ እነ ፋሲል የኔዓለም "ዳግማዊ ጣይቱ" ሲሏቸው እንደነበር ይታወሳል። ዘንድሮ ግን ወፍ የለም። ህዝቡም በመንግሥቱ ላይ ስላኮረፈ ጭጭ ምጭጭ ብሏል። ይሄ ነገር ከባድና አደገኛ ነው። ባለሃብቱም አይመለከተኝ የሚል ስሜት ያለው ይመስላል። አርቲስቱም ተደብቋል። እብድ መሪ ያላት ሃገር እንዲህ ናት።

"…የዐማራ ክልል አሁንም ይሄ ፍዳ የወደቀበት ሆኗል። በጀቱ በሙሉ ለጦርነቱ እየዋለ ነው። የሆስፒታል አልጋ በቁስለኞች ተሞልቷል። ሃኪሞች እዚያ ርብርብ ላይ ናቸው። ክልሉ በጀቱን በጊዜ ጨርሶ እጁን አጣጥፎ ከመቀመጥ ውጪ ሌላ አማራጭ ያለው አይመስልም። ኦሮሚያ ግን ልማት ላይ ነች። በጀቷንም በአግባቡ እየተጠቀመች ነው። እናም ይሄ ነገር በቶሎ ቢታሰብበት እና የፌደራሉ መንግሥት ልዩ የሆነ በጀት ለዐማራ ክልል ቢመድብ ይላሉ ወዳጆቼ። እናንተስ ምን ትላላችሁ? ተወያዩበት።

በተረፈ፦ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

• ድል ለሃገሬ መከላከያ…!!
• ድል ለዐማራ ልዩ ኃይል…!!
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!!
• ድል ለዐማራ ሚሊሻ…!!
• ድል ለአፋር ልዩ ኃይል…!!
• ድል ለአፋር ሚሊሻ…!!
• ነፃነት ለትግራይ ህዝብ…!!
• ሞት ለወያኔ እና ለልጆቿ ለብአዴንና ለኦህዴድ…!!
39.0K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 12:01:23 የዐርብ ጠዋት ጦማር…!!

• የጥንቃቄና የማስተካከያ ጥቆማ የያዘ ጦማር ነው። አንዳንዱን ባይሰሙት የሚፈልጉ ይኖራሉ። ነገር ግን ቢመርም መስማቱ ፈውስ ነው። ለመከላከያው አድርሱልኝ።

"…ጦርነቱ አስከፊ ነው። አሰቃቂም ጭምር ነው። ከዚህም ከዚያም ይህ ነው የማይባል በቁጥር የማይገለፅ ሰው እያለቀ ነው። ወንድ የተባለ ከዚህም ከዚያም እየወደቀ ነው። በተለይ ደግሞ ከትግሬ ወገን የሚያሳዝነው እረገፈ ያለው ከህፃናት አንሥቶ ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ጭምር መሆኑ ነው። አሁን ከዚያኛው ትውልድ የቀሩት ቢቆጠሩ 20 አይሞሉም። ህዝቡ እየተዋደቀ፣ እየረገፈ ያለው ለእነዚህ 20 ለማይሞሉ በቃኝ ለማያውቁ አረመኔ ጨካኞች ሲል መሆኑም ያሳዝናል።

"…በኢትዮጵያ ወገን እስከአለፈው እሁድ ድረስ በተለይ በቆቦ ግንባር የተዘበራረቀ አሰላለፍ ስለነበረ ከኢትዮጵያ ወገን ብዙ ምርኮኛና ቁስለኛ መመዝገቡን የሚደርሱኝ መረጃዎች ያሳያሉ። ሆስፒታሎች ሞልተው መንገድ ዳር ዳስ ተሠርቶም ህክምና ለመስጠት እየተሞከረ ነው። ከእሁድ ዕለት ወዲህ ግን አሰላለፉ በመቀየሩ ወታደሩ ከጥምር ጦሩ ከዐማራ ልዩ ኃይል እና ከዐማራ ፋኖ እንዲሁም ከዐማራ ሚኒሻ ጋር በመናበብ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግሯል። በዚህም የተነሣ እጅግ ጠንካራ የተባሉ የህወሓት ምሽጎች እየተደረማመሱ ነው። ይሄ በእጅጉ ደስ የሚያሰኝ ነው።

"…ነገር ግን በሌላ በኩል በሰቆጣ ግምባር በህክምና አሰጣጥ በኩል በአንዳንድ ዐማራ ጠል በሆኑ የመከላከያ ኃላፊዎች ዘንድ እየታየ ያለው አረመኔያው የሆነ የጭካኔ ተግባር ከወዲሁ ይስተካከል ዘንድ በመከላከያ ውስጥ እንደ ሃገር የሚያስቡ አካላት ይናገራሉ። ምክሩን ተቀብሎ ማስተካከል ደግሞ የመከላከያ ሓላፊነት ነው።

፩ኛ፦ ቁስለኞችን እኩል ያለማየት፦

"…ይሄ ነገር እየተደጋገመ ነው። አብሮት እንዲዋጋ፣ እንዲዋደቅ ይጠራውና ፋኖው ሲቆስል ለፋኖ በጀት የለኝም፣ አላክምም ብሎ የቆሰለሉ ፋኖዎች ህክምና እንዳያገኙ ማድረግ ፀያፍ ነው። ይህን ትእዛዝ ጥሰው የቆሰለ ፋኖ ሲያክሙ የተገኙ ሃኪሞች በመከላከያ አዛዦች ሲዘለፉ፣ ሲሰደቡ ማየቱም ያሳፍራል። እንኳን ፋኖ የጠላት ጦር እንኳ ቢሆን ህክምና አይከለከልም። (ለሃኪሞቹ ደኅንነት ስል የመከላከያ ሓላፊዎቹን የድንፋታ ቪድዮ አዘገየዋለሁ)

፪ኛ፦ ያልታወቀ የመሳሪያ ክምችት፦

"…የሆስፒታሉን ስም አልገልፀውም። ነገር ግን ከሆስፒታሉ ጀርባ ማንነቱ ያልታወቀ ከፍተኛ መሳሪያ ክምችት አለ። መሳሪያው የወገን ጦር መሳሪያ ነው። መሳሪያው ተቀጣጣይ ፈንጂዎችንም ያካተተ ነው። በየጊዜውም የሚጨምርም ነው። እናም በተቻለ መጠን የመሳሪያ ክምችቱ ከሆስፒታሉ አካባቢ ቢርቅ መልካም ነው። ከፈነዳ ጥፋቱ ከባድ ስለሆነ ከወዲሁ ቢታሰብበት።

፫ኛ፦ ያልጠራ መከላከያ፦

"…በትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ትግርኛ ተናጋሪዎችም ጭምር ናቸው። ይሄን የማያውቁ ወይም አውቀው ማስተዋል የተሳናቸው አንዳንድ የመከላከያ ሓላፊዎች ከሆስፒታሉ ሆነው በስልክ ከወዲያኛው የህወሓት ሓይል ጋር ሲያወሩ፣ መረጃም ለጠላት ሲሰጡ እየታዘቡ ነው። ሓኪሞች። ይሄ ነውር ነው። እንትና በየትኛው ግንባር ነው የተሰለፈው? በዚያ ግምባር ነፍጠኛ ስለሚበዛ አምልጥ፣ በዚህ ግምባር አጥቁ፣ በዚህ እና በዚያ ግምባር የተሰለፈው መድፍ ሲሰማ የሚበተን የቅርብ ምሩቅ ነው። እያሉ ከወዲያኛው ጠላት ጋር የሚያወሩ አሉ። በተለይ ትግራይ ቆይተው የመጡ ቢጠነቀቁ መልካም ነው። አልያም እንደ ደብረ ታቦሩ ሰውዬ ስልካቸውን ጠልፎ እርምጃ መውሰድ ነው። አለበለዚያ የወገን ጦር ይጎዳል።

፬ኛ፦ ማታለል፦

"…በሆስፒታሎች ቀላል ቁጥር የሌላቸወረ በጣም ብዙ የመከላከያ አባላት ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይደርስባቸው የቆሰሉ መስለው ጦርነቱን በመፍራት ብቻ የጓደኛቸውን ደም ተቀብተው የተመቱ መስለው ይመጣሉ። ይሄ የሚገጥም ቢሆንም በዚህ መጠን ግን አላየንም። ወይ የወታደራዊ ሥልጠና ጉድለት ነው። ወይም ደግሞ ተልእኮው ሌላ ነው። እናም ቢስተካከል።

ይህ ሲባል የወያኔ ጦር ደፋር ነው ማለት አይደለም። ወያኔ ህጻናትን ሳይቀር፣ ነፍሰጡር እመጫት ሳይቀር ሥነ ልቦናቸውን በኢትዮጵያና በዐማራ ህዝብ ጥላቻ ሰልባ፣ መርዝ ስትግታቸው፣ በዘፈን፣ በቀረርቶ ሁላ ስትነሽጣቸው ከርማ በመጨረሻም የሚያሳብድ ሀሺሽ እየሰጠች እንደምትማግዳቸው ይታወቃል። የእኛን ከዚያ ማወዳደር አይገባም። ቢሆንም ግን መመርመር ያስፈልጋል።

"…የወገን ጦር ድጋፍ ይፈልጋል። ህዝቡ ደጀን ሲሆን ወታደሩ ይደፍራል። የሙዚቃ ዝግጅት አንደኛው ወታደር ማጀገኛ መንገድ ነው። ድሮ የታወቁ ሙዚቀኞች ግንባር ድረስ ሄደው የሚዚቃ ሥራ በመሥራት ያበረታቱ ነበር። አሁን ያ አይታይም። ሙዚቀኞች በግንባር ሳሉ መሰዋታቸው ሁሉ ይታወሳል። እናም አሁን ያ የለም። ስለዚህ ወታደሩ ከነ ድብርቱ ነው ለውጊያ የሚላከው። በዚህ ላይ የዘር ፖለቲካው ጉዳይ አለ። እናም ቢታሰብበት።

፭ኛ፦ የመረጃ ዝርክርክነት

"…እንዴት እንደሆነ ባናውቅም በግልጽ የህውሓት ወታደሮች የሀገር መከላከያን ልብስ ለብሰው ማታ መረጃ ይዘው ይወጣሉ። ከማን ጋር እንደሚገናኙ ግን አይታወቅም። መከላከያ ውስጡን ቢያጸዳ መልካም ነው።

፮ኛ፦ የዩኒፎርም መመሳሰል

“…ከኦሮሚያ ክልል ሰልጥነው የመጡ አንዳንድ ሳይሆን በብዛት ለዐማራ ያላቸው ጥላቻ ከትግሬው የበለጠ ሆኖ እየተየ ነው። የቆሰለው ወታደር "ወይኔ በማያገባኝ መጥቼ ለነፍጠኛ ስል ቆሰልኩ፣ ትግሬና ዐማራ በተጣላ እኔ ምን ቤት ነኝ እያለ የሚብሰከሰክ ሲታይ ነገርየው ምንድነው ትላለህ። ባለፈው ጦርነትም፣ በአሁንም ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ወደ ትግሬ ገብተው እጅ የሰጡም አሉ። የቆዩትም አሁን ያንኑ ዩኒፎርም ለብሰው የወገን ጦር መስለው እየገቡ ነውና በዚህ በኩል ጥብቅ ቁጥጥር እና ፍተሻ ቢደረግ መልካም ነው።

፮ኛ፦ በሞባይል ስልክ እየቀረጹ መዋጋት

"…አንዳንድ ወታደሮች ውጊያውን ትተው ቲክቶክ ሁላ ሲሠሩ ማየት ይደንቃል። በቤተ ክርስቲያን ዝማሬ ሲዘመር ጭብጨባ ትተው የማያዩትን ቪዲዮ ሲቀርጹ እንደሚውሉ ሴቶች በጦር ግንባርም ከጠላት ጋር እየተዋጉ ቪድዮ መቅረጽ እጅግ አደገኛ ነው። አንዳንዶች ቀጥታ ስርጭት ስለሚያስተላልፉም ለወገን ጦር ጉዳት ነው። በሰቆጣ ግንባር ግን የመከላከያ ሓላፊዎች ወደ ውጊያው የሚገቡ ወታደሮችን ስልክ ለቅመው መዝግበው ሲያስቀምጡ ታየተዋል። ይሄ የሚበረታታ ነው። በሁሉም ግምባሮች እንዲህ የሚድያ ሥራ የሚሠሩ ብቻ ፈቃድ ያላቸው ቢዘግቡ መልካም ነው። ወታደሩ ሬሳ ቀርጾ ለናትናኤል መኮንን እና ለእኔ ለመላክ ከሚጣደፍ ውጊያው ላይ ቢያተኩር መልካም ነው።

፯ኛ፦ የዐማራ ሚሊሻን በተመለከተ

"…የዐማራ ሚሊሻ አደረጃጀት የለውም። የቀበሌውን ሊቀመንበር ትእዛዝ ተቀብሎ የሚመጣ የዋህ ገበሬ ነው። የጦር መሣሪያውም ኋላቀር ነው። ብአዴኖች ፍፁም አረመኔዎች መሆናቸው የሚያስታውቀው በሽተኛ ሚሊሻ እዚያው ሄደህ አንድ ወያኔ ገለህ ሙት ብለው መላካቸው ነው። ይሄ ነውር ነው። ኃጢአትም ግፍም ወንጀልም ነው።

ሚሊሻው የተተኳሽ እጥረትም አለበት። በቁጥር ያለችውን ጥይት ከጨረሰ በቃ ከመሞት ውጪ ተስፋ የለውም። መገናኛ ሬድዮ የለውም። ከልዩ ኃይሉ፣ ከመከላከያው እና ከፋኖው ጋር ተደርቦ የሚገባ ነው። የትምህርት ዝግጅት የለም። ጦሩ ሲበተን ወዴት እንደሚሄዱም አያውቁም። መከላከያውን ያከብሩታል፣ ይፈሩታል፣ ይኮሩበታል። እናም የታዘዙትን ሁሉ " እሺ ጌታዬ ብለው ከመፈጸም በቀር ሌላ አያውቁም።
37.9K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 11:51:39
የዐርብ ረፋድ ጦማሬ ነው።

"…ጦርነቱ መቆሙ አይቀርም። አንድ ቀን አንዱ ሲደክመው መቆሙ አይቀርም። ነገር ግን እስከዚያው ትግሬና ዐማራ ተጨፋጭፎ ቁጥሩ መቀነስ አለበት። በትግሬ በኩል እንደምታዩት አሮጊቷ አዛውንት እናት እንኳ ሳይቀሩ ነው የተሰለፉት። ለዝርፊያም፣ ለግድያም። ይሄ የጥላቻ ፖለቲካ የወለደው ክፉ ደዌ ነው።

"…በሁለቱም በኩል ሞትም ቁስለኛም የትየለሌ ነው። ሃኪም ቤት ሞልቶ መንገድ ዳር ዳስ ተሠርቶ እየተካመ ነው። ለማንኛውም ዘንዶ ጥምጥም፣ ሊማሊሞ የመሰለ ጦማሬን ከታች አንብቡልኝ። ከደበራችሁ አጫጭሩ ጦማር እስኪለጠፍ ባላየ ባልሰማ እለፉት።



የምጠቀመው፣ ሃሳቤን የምገልፀው፣ መልእክቴንም የማስተላልፈው በዚህ ቴሌግራም ቻናሌ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ፌስቡክ የማልጠቀም መሆኔም ይገለፅ፣ ይታወቅልኝ። ተናግሬአለሁ።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ

https://t.me/zemede_Discussion
42.3K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ