Get Mystery Box with random crypto!

'…ቁጥራቸው አይታወቅም። እርሻና ልጆች ትተው ሊቀመንበሩ በጭካኔ የሚልካቸው ናቸው። መሬትም ሚስቱም | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ቁጥራቸው አይታወቅም። እርሻና ልጆች ትተው ሊቀመንበሩ በጭካኔ የሚልካቸው ናቸው። መሬትም ሚስቱም የምትወረስ ብዙ ሚሊሻ ነው። ስንቅ የላቸውም። ወታደሩም ልዩ ኃይሉም ሬሽን አለው። ሚሊሻው ግን ያሳዝናል። ሦስት ቀን እህል ያልቀመሱ አሉ። ጫማቸው ኤርጌንዶ ነው። እሱ ተበጣጥሶ እግራቸው ነፍሮ ማየት ያሳዝናል። እናም ቢያንስ የሆዳቸው ነገር እና የተተኳሽ፣ የጫማቸው ነገር ቢታሰብበት መልካም ነው።

፰ኛ፦ የበጀት እጥረት

"…አምና በነበረው ጦርነት የህዝብ የደጀን ተሳትፎ እጅግ ግሩም ነበር። በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም እንደዚያው። ነገር ግን ቀለብላባው እና ንኩ ጠቅላይ ሚንሥትር ተብዬው ለገና የመጡትን ዳያስፖራዎች ውሻ ፈትቶ ለቅቆ ካባረራቸው በኋላ ዳያስጶራውም በብልጽግና መንግሥት አኩርፎ እስከአሁን እንቅስቃሴ የለም። ይሄን ያስተባብሩ የነበሩት እነ ታማኝ በየነንም መንግሥት ውሻ አድርጎ አንገቱንም ቅስሙንም ሰብሮ ስለላካቸው የሉም። ዳያስጶራው አፍሯል። ድጋፉም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ቀጥ ብሏል።

"…በሃገር ውስጥም አምና ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች በሙሉ ከደሞዛቸው ሳይቀር እያዋጡ ይደግፉ ነበር። እነ አዳነች አቤቤ ሁላ ግምባር ድረስ ሄደው ስንቅ ሲያቀብሉ፣ ከዚህም የተነሣ እነ ፋሲል የኔዓለም "ዳግማዊ ጣይቱ" ሲሏቸው እንደነበር ይታወሳል። ዘንድሮ ግን ወፍ የለም። ህዝቡም በመንግሥቱ ላይ ስላኮረፈ ጭጭ ምጭጭ ብሏል። ይሄ ነገር ከባድና አደገኛ ነው። ባለሃብቱም አይመለከተኝ የሚል ስሜት ያለው ይመስላል። አርቲስቱም ተደብቋል። እብድ መሪ ያላት ሃገር እንዲህ ናት።

"…የዐማራ ክልል አሁንም ይሄ ፍዳ የወደቀበት ሆኗል። በጀቱ በሙሉ ለጦርነቱ እየዋለ ነው። የሆስፒታል አልጋ በቁስለኞች ተሞልቷል። ሃኪሞች እዚያ ርብርብ ላይ ናቸው። ክልሉ በጀቱን በጊዜ ጨርሶ እጁን አጣጥፎ ከመቀመጥ ውጪ ሌላ አማራጭ ያለው አይመስልም። ኦሮሚያ ግን ልማት ላይ ነች። በጀቷንም በአግባቡ እየተጠቀመች ነው። እናም ይሄ ነገር በቶሎ ቢታሰብበት እና የፌደራሉ መንግሥት ልዩ የሆነ በጀት ለዐማራ ክልል ቢመድብ ይላሉ ወዳጆቼ። እናንተስ ምን ትላላችሁ? ተወያዩበት።

በተረፈ፦ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

• ድል ለሃገሬ መከላከያ…!!
• ድል ለዐማራ ልዩ ኃይል…!!
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!!
• ድል ለዐማራ ሚሊሻ…!!
• ድል ለአፋር ልዩ ኃይል…!!
• ድል ለአፋር ሚሊሻ…!!
• ነፃነት ለትግራይ ህዝብ…!!
• ሞት ለወያኔ እና ለልጆቿ ለብአዴንና ለኦህዴድ…!!