Get Mystery Box with random crypto!

የዐርብ ጠዋት ጦማር…!! • የጥንቃቄና የማስተካከያ ጥቆማ የያዘ ጦማር ነው። አንዳንዱን ባይሰሙ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዐርብ ጠዋት ጦማር…!!

• የጥንቃቄና የማስተካከያ ጥቆማ የያዘ ጦማር ነው። አንዳንዱን ባይሰሙት የሚፈልጉ ይኖራሉ። ነገር ግን ቢመርም መስማቱ ፈውስ ነው። ለመከላከያው አድርሱልኝ።

"…ጦርነቱ አስከፊ ነው። አሰቃቂም ጭምር ነው። ከዚህም ከዚያም ይህ ነው የማይባል በቁጥር የማይገለፅ ሰው እያለቀ ነው። ወንድ የተባለ ከዚህም ከዚያም እየወደቀ ነው። በተለይ ደግሞ ከትግሬ ወገን የሚያሳዝነው እረገፈ ያለው ከህፃናት አንሥቶ ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ጭምር መሆኑ ነው። አሁን ከዚያኛው ትውልድ የቀሩት ቢቆጠሩ 20 አይሞሉም። ህዝቡ እየተዋደቀ፣ እየረገፈ ያለው ለእነዚህ 20 ለማይሞሉ በቃኝ ለማያውቁ አረመኔ ጨካኞች ሲል መሆኑም ያሳዝናል።

"…በኢትዮጵያ ወገን እስከአለፈው እሁድ ድረስ በተለይ በቆቦ ግንባር የተዘበራረቀ አሰላለፍ ስለነበረ ከኢትዮጵያ ወገን ብዙ ምርኮኛና ቁስለኛ መመዝገቡን የሚደርሱኝ መረጃዎች ያሳያሉ። ሆስፒታሎች ሞልተው መንገድ ዳር ዳስ ተሠርቶም ህክምና ለመስጠት እየተሞከረ ነው። ከእሁድ ዕለት ወዲህ ግን አሰላለፉ በመቀየሩ ወታደሩ ከጥምር ጦሩ ከዐማራ ልዩ ኃይል እና ከዐማራ ፋኖ እንዲሁም ከዐማራ ሚኒሻ ጋር በመናበብ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግሯል። በዚህም የተነሣ እጅግ ጠንካራ የተባሉ የህወሓት ምሽጎች እየተደረማመሱ ነው። ይሄ በእጅጉ ደስ የሚያሰኝ ነው።

"…ነገር ግን በሌላ በኩል በሰቆጣ ግምባር በህክምና አሰጣጥ በኩል በአንዳንድ ዐማራ ጠል በሆኑ የመከላከያ ኃላፊዎች ዘንድ እየታየ ያለው አረመኔያው የሆነ የጭካኔ ተግባር ከወዲሁ ይስተካከል ዘንድ በመከላከያ ውስጥ እንደ ሃገር የሚያስቡ አካላት ይናገራሉ። ምክሩን ተቀብሎ ማስተካከል ደግሞ የመከላከያ ሓላፊነት ነው።

፩ኛ፦ ቁስለኞችን እኩል ያለማየት፦

"…ይሄ ነገር እየተደጋገመ ነው። አብሮት እንዲዋጋ፣ እንዲዋደቅ ይጠራውና ፋኖው ሲቆስል ለፋኖ በጀት የለኝም፣ አላክምም ብሎ የቆሰለሉ ፋኖዎች ህክምና እንዳያገኙ ማድረግ ፀያፍ ነው። ይህን ትእዛዝ ጥሰው የቆሰለ ፋኖ ሲያክሙ የተገኙ ሃኪሞች በመከላከያ አዛዦች ሲዘለፉ፣ ሲሰደቡ ማየቱም ያሳፍራል። እንኳን ፋኖ የጠላት ጦር እንኳ ቢሆን ህክምና አይከለከልም። (ለሃኪሞቹ ደኅንነት ስል የመከላከያ ሓላፊዎቹን የድንፋታ ቪድዮ አዘገየዋለሁ)

፪ኛ፦ ያልታወቀ የመሳሪያ ክምችት፦

"…የሆስፒታሉን ስም አልገልፀውም። ነገር ግን ከሆስፒታሉ ጀርባ ማንነቱ ያልታወቀ ከፍተኛ መሳሪያ ክምችት አለ። መሳሪያው የወገን ጦር መሳሪያ ነው። መሳሪያው ተቀጣጣይ ፈንጂዎችንም ያካተተ ነው። በየጊዜውም የሚጨምርም ነው። እናም በተቻለ መጠን የመሳሪያ ክምችቱ ከሆስፒታሉ አካባቢ ቢርቅ መልካም ነው። ከፈነዳ ጥፋቱ ከባድ ስለሆነ ከወዲሁ ቢታሰብበት።

፫ኛ፦ ያልጠራ መከላከያ፦

"…በትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ትግርኛ ተናጋሪዎችም ጭምር ናቸው። ይሄን የማያውቁ ወይም አውቀው ማስተዋል የተሳናቸው አንዳንድ የመከላከያ ሓላፊዎች ከሆስፒታሉ ሆነው በስልክ ከወዲያኛው የህወሓት ሓይል ጋር ሲያወሩ፣ መረጃም ለጠላት ሲሰጡ እየታዘቡ ነው። ሓኪሞች። ይሄ ነውር ነው። እንትና በየትኛው ግንባር ነው የተሰለፈው? በዚያ ግምባር ነፍጠኛ ስለሚበዛ አምልጥ፣ በዚህ ግምባር አጥቁ፣ በዚህ እና በዚያ ግምባር የተሰለፈው መድፍ ሲሰማ የሚበተን የቅርብ ምሩቅ ነው። እያሉ ከወዲያኛው ጠላት ጋር የሚያወሩ አሉ። በተለይ ትግራይ ቆይተው የመጡ ቢጠነቀቁ መልካም ነው። አልያም እንደ ደብረ ታቦሩ ሰውዬ ስልካቸውን ጠልፎ እርምጃ መውሰድ ነው። አለበለዚያ የወገን ጦር ይጎዳል።

፬ኛ፦ ማታለል፦

"…በሆስፒታሎች ቀላል ቁጥር የሌላቸወረ በጣም ብዙ የመከላከያ አባላት ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይደርስባቸው የቆሰሉ መስለው ጦርነቱን በመፍራት ብቻ የጓደኛቸውን ደም ተቀብተው የተመቱ መስለው ይመጣሉ። ይሄ የሚገጥም ቢሆንም በዚህ መጠን ግን አላየንም። ወይ የወታደራዊ ሥልጠና ጉድለት ነው። ወይም ደግሞ ተልእኮው ሌላ ነው። እናም ቢስተካከል።

ይህ ሲባል የወያኔ ጦር ደፋር ነው ማለት አይደለም። ወያኔ ህጻናትን ሳይቀር፣ ነፍሰጡር እመጫት ሳይቀር ሥነ ልቦናቸውን በኢትዮጵያና በዐማራ ህዝብ ጥላቻ ሰልባ፣ መርዝ ስትግታቸው፣ በዘፈን፣ በቀረርቶ ሁላ ስትነሽጣቸው ከርማ በመጨረሻም የሚያሳብድ ሀሺሽ እየሰጠች እንደምትማግዳቸው ይታወቃል። የእኛን ከዚያ ማወዳደር አይገባም። ቢሆንም ግን መመርመር ያስፈልጋል።

"…የወገን ጦር ድጋፍ ይፈልጋል። ህዝቡ ደጀን ሲሆን ወታደሩ ይደፍራል። የሙዚቃ ዝግጅት አንደኛው ወታደር ማጀገኛ መንገድ ነው። ድሮ የታወቁ ሙዚቀኞች ግንባር ድረስ ሄደው የሚዚቃ ሥራ በመሥራት ያበረታቱ ነበር። አሁን ያ አይታይም። ሙዚቀኞች በግንባር ሳሉ መሰዋታቸው ሁሉ ይታወሳል። እናም አሁን ያ የለም። ስለዚህ ወታደሩ ከነ ድብርቱ ነው ለውጊያ የሚላከው። በዚህ ላይ የዘር ፖለቲካው ጉዳይ አለ። እናም ቢታሰብበት።

፭ኛ፦ የመረጃ ዝርክርክነት

"…እንዴት እንደሆነ ባናውቅም በግልጽ የህውሓት ወታደሮች የሀገር መከላከያን ልብስ ለብሰው ማታ መረጃ ይዘው ይወጣሉ። ከማን ጋር እንደሚገናኙ ግን አይታወቅም። መከላከያ ውስጡን ቢያጸዳ መልካም ነው።

፮ኛ፦ የዩኒፎርም መመሳሰል

“…ከኦሮሚያ ክልል ሰልጥነው የመጡ አንዳንድ ሳይሆን በብዛት ለዐማራ ያላቸው ጥላቻ ከትግሬው የበለጠ ሆኖ እየተየ ነው። የቆሰለው ወታደር "ወይኔ በማያገባኝ መጥቼ ለነፍጠኛ ስል ቆሰልኩ፣ ትግሬና ዐማራ በተጣላ እኔ ምን ቤት ነኝ እያለ የሚብሰከሰክ ሲታይ ነገርየው ምንድነው ትላለህ። ባለፈው ጦርነትም፣ በአሁንም ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ወደ ትግሬ ገብተው እጅ የሰጡም አሉ። የቆዩትም አሁን ያንኑ ዩኒፎርም ለብሰው የወገን ጦር መስለው እየገቡ ነውና በዚህ በኩል ጥብቅ ቁጥጥር እና ፍተሻ ቢደረግ መልካም ነው።

፮ኛ፦ በሞባይል ስልክ እየቀረጹ መዋጋት

"…አንዳንድ ወታደሮች ውጊያውን ትተው ቲክቶክ ሁላ ሲሠሩ ማየት ይደንቃል። በቤተ ክርስቲያን ዝማሬ ሲዘመር ጭብጨባ ትተው የማያዩትን ቪዲዮ ሲቀርጹ እንደሚውሉ ሴቶች በጦር ግንባርም ከጠላት ጋር እየተዋጉ ቪድዮ መቅረጽ እጅግ አደገኛ ነው። አንዳንዶች ቀጥታ ስርጭት ስለሚያስተላልፉም ለወገን ጦር ጉዳት ነው። በሰቆጣ ግንባር ግን የመከላከያ ሓላፊዎች ወደ ውጊያው የሚገቡ ወታደሮችን ስልክ ለቅመው መዝግበው ሲያስቀምጡ ታየተዋል። ይሄ የሚበረታታ ነው። በሁሉም ግምባሮች እንዲህ የሚድያ ሥራ የሚሠሩ ብቻ ፈቃድ ያላቸው ቢዘግቡ መልካም ነው። ወታደሩ ሬሳ ቀርጾ ለናትናኤል መኮንን እና ለእኔ ለመላክ ከሚጣደፍ ውጊያው ላይ ቢያተኩር መልካም ነው።

፯ኛ፦ የዐማራ ሚሊሻን በተመለከተ

"…የዐማራ ሚሊሻ አደረጃጀት የለውም። የቀበሌውን ሊቀመንበር ትእዛዝ ተቀብሎ የሚመጣ የዋህ ገበሬ ነው። የጦር መሣሪያውም ኋላቀር ነው። ብአዴኖች ፍፁም አረመኔዎች መሆናቸው የሚያስታውቀው በሽተኛ ሚሊሻ እዚያው ሄደህ አንድ ወያኔ ገለህ ሙት ብለው መላካቸው ነው። ይሄ ነውር ነው። ኃጢአትም ግፍም ወንጀልም ነው።

ሚሊሻው የተተኳሽ እጥረትም አለበት። በቁጥር ያለችውን ጥይት ከጨረሰ በቃ ከመሞት ውጪ ተስፋ የለውም። መገናኛ ሬድዮ የለውም። ከልዩ ኃይሉ፣ ከመከላከያው እና ከፋኖው ጋር ተደርቦ የሚገባ ነው። የትምህርት ዝግጅት የለም። ጦሩ ሲበተን ወዴት እንደሚሄዱም አያውቁም። መከላከያውን ያከብሩታል፣ ይፈሩታል፣ ይኮሩበታል። እናም የታዘዙትን ሁሉ " እሺ ጌታዬ ብለው ከመፈጸም በቀር ሌላ አያውቁም።