Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 412.24K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-04-15 14:32:00 …ከላይኛው ይቀጠለ… "…አሁን ፋኖ አዲስ አበባ ነው። ዐማራ ሁሉ ፋኖ ነው። ፋኖ በፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ፋኖ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ፋኖ በመከላከያ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በኢንሣ፣ በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ፣ በሚንስትሮች ምክር ቤት፣ በሁሉም ቦታ ነው ያለው። የዐማራ ፋኖ ማለት የዐማራ ሕዝብ በሙሉ ማለት ነው። የንግድ ባንክን፣ ቴሌን ወዘተረፈ ኤልፓን ጭምር በአንድ ጀምበር በተኖችን በመነካካት ብቻ ውድመት ሳያስከትል ሀገር ማጨለም፣ ሽባ ማድረግ የሚቻለው ነው ፋኖ ማለት። ፋኖ ማለት እየተታኮሰ ያለው ብቻ አይደለም። ስሙ ቶሎሳ፣ ገመቺስ ስለሆነ ኦሮሞ ነው ማለት አይደለም። ለምሳሌ የኢንሳን ልጆች የሚጠረጥሯቸውን በሙሉ ከፋኖ ኦፕሬሽን አስወጥተዋቸው ሙሉ በሙሉ በኦሮሞ ተክተዋቸዋል። አሁንም ግን የኢንሳ መረጃ በእጄ ነው። የኦሮሞ ስም መያዙ፣ የደቡብ ተወላጅ በቦታው መተካቱ፣ ለእኔ መረጃ ከመስጠት፣ ደማዊ ዐማራነቱን ያውም እልል ያለ ፋኖ ከመሆንም አያግደውም።

"…ይሄ እኔ በራሴ ጥረት የደረስኩበት መረጃ ነው። አሁን ከዛሬ ጀምሮ ትረካው ይቀየራል። ስሜን ሳይጠቅሱ እነ መሳይ መኮንንም፣ እነ ኢኤምኤስም፣ እነ ደረጄ ሀብተወልድም፣ እነ ሞጣ ቀራንዮም፣ ቲክቶከሩ ሁላ፣ ዩቲዩበሩም ትንተና ውስጥ ይገባል። ግርም እኮ ነው የሚሉኝ። እንዴት ሰው በጨበጣ ዜና ይሠራል? እንዴት ለቪው ብሎ የባጥ የቆጡን ይቀባጥራል? እኔ ግን ጋዜጠኛ አይደለሁም ግን ጋዜጠኛ ምን ሆን እንዴት ሙያውን አክብሮ መሥራት እንዳለበት አንብቤአለሁ። ከቃሌ ሐሰት ቢገኝ የሚገስጸኝ የጎንደር ፋኖ ነው። ሌላህን አልሰማህም። ይኸው ነው። ነጋዴዎች የመረጃ ምንጫችሁ እኔን ሳትጠቅሱ በሉ ሸቅሉ። በራሳቸው ትክክል ናቸውና ሌሎቹ የዘገቡትን ዘገባም አልቃወምም። ለትግሉ እስከጠቀመ ድረስ ምን ክፋት አለው?

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
79.4K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 14:31:46 "ርዕሰ አንቀጽ"

"…ለምን ሳይጯጯህ፣ ግርግርም፣ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ሳይደነብር፣ ጫናም፣ የዲፕሎማሲ ኪሳራም ሳይፈጠርብን ልጆቹን በሕይወት አልያዛችሁም? ለምን ያን ያህል ሰዓት ድረስ በመሃል አዲስ አበባ ያውም በቦሌ አየር መንገዱ አጠገብ ተኩስ እስኪከፈት፣ ጦርነት የተጀመረ እስኪመስል ድረስ ተዘናጋችሁ? ግማሽ ቀን ሙሉ መንገድ ተዘግቶ ደካማነታችን እስኪታይ እስኪጋለጥ ድረስ ምን ስትጠብቁ ነበር? ይሄ ድርጅት (ኢንሳን ማለቱ ነው) እንደ አዲስ ፈርሶ በድጋሚ መሠራት አለበት በማለት አቢይ አሕመድ የኢንሳ ሓላፊዎች ላይ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እብድ እያንባረቀ የሚጮህባቸው በእነ ፋኖ ናሁሰናይ እና አቤኔዘር የአዲስ አበባ ኦፕሬሽን ተበሳጭቶም፣ ደንግጦም ነው። አሁን ቆስሎ ተያዘ የተባለው ልጅ የሚያውቀው ነገር የለም። ዋናው የሚሽኑ ባለቤት ፋኖ ናሁሰናይ ነው።

"…ፋኖ ናሁሰናይ የዐማራ ፋኖ በጎንደር የአጼዎቹ ክፍለ ጦር የቀጠና ዘመቻ መምሪያ ሓላፊ ነበር። ፋኖ ናሁሰናይ የታወቀ የጦር መሪ ሆኖ ሳለ ወደ አዲስ አበባ የተላከው የታሰበውን ሓሳብ፣ የታቀደውን ዕቅድ ያለእሱ ሊፈጸም የሚችል ሌላ ሰው ስላልነበረ ብቻ ነበር ናሁሰናይ ወደ አዱ ገነት የሄደው። ናሁሰናይ በትምህርቱ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ስለነበረ በኢንጂነሪንጉ በኩል ደግሞ ሀገር ለመምራት ጣጣውን ጨርሶ የተቀመጠው ፋኖ ከዚያ በፊት አሁን በራሱ አቅም እያመረተ ስላለው የጦር መሣሪያ የሚያስፈልገውን የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት ከፍ ላለሌላ ጉዳይ የሚረዳውን ተግባር ለመፈጸም ነበር ልጁ የተላከው። እናም ልጁ የተሰጠውን ግዳጅ እና ተልእኮ ለማሳካት ቁጥሩ የማይታወቅ የሰው ኃይል ይዞ ነበር ወደ አዲስ አበባ የሄደው። በዚያም የከተመው። አደገኛም የሆነ ሪስክ ነበር የወሰደው።

"…እነ ናሁሰናይ ምንም ሳይነቃባቸው እየተዝናኑም፣ እየጨፈሩም፣ በእውቀት፣ በምርምር ላይ ለሚፈለገው የቴክኖሎጂ ጉዳይ የተሰጣቸውን ተልእኮ በሚገባ ፈጽመው፣ ጨርሰውም፣ እነርሱ ያልነበሩበት ነገር ግን ልክ በዛሬው እለት ሚያዚያ 7/2016 ዓም በእለተ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ በዓይነቱ ከባድ ነው የተባለ አስደናቂ የፋኖ ኦፕሬሽን እንዲፈጸም መመሪያም ሰጥቶ እሱና የተወሰኑቱ ባለፈው አርብ ሚያዝያ 4/2016 ዓም መጀመሪያ ወደ ሸዋ ከዚያም ወደ ጎንደር ለመመለስ አቅደው ጨርሰው ነበር በመሃል ይሄ ያልተጠበቀ ድንገተኛ ክስተት የተፈጸመው።

"…ከየት እንደሆነ ለጊዜው ባይታወቅም የአገዛዙ የስለላ ድርጅት መረጃው ዘግይቶ እንደደረሰው ይገመታል። ልጆቹ አዲስ አበባ እንደመጡ እንጂ ለምን እንደመጡ አገዛዙ አልደረሰበትም። በዚያ ሰዓት ቦሌ ምን እየሠሩ እንደነበረም አላወቀም። ነገር ግን ለሆነ ኦፕሬሽን ወይም ለራሳቸው ጉዳይ በዚያ እንደተገኙ ግን ገምግሟል። ታዛቢዎች የሚሉት በዚህ መጠን ታዋቂ የሆኑ ልጆች ይሄን አደገኛ ተልእኮ ወስደው ሳለ ለምን ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ታሳቢ አድርገው በፍጥነት ቦታ ስለመልቀቅ አላሰቡም ብለው በመጠየቅ ይቆጫሉ። ነገር ግን እነ ናሁሰናይን በላካቸውና ሚሽኑን በሰጣቸው አካል በኩል ደግሞ ይኸው ጥያቄ ሲነሣባቸው የሚመልሱት መልስ "ልጆቹ የተሠጣቸውን የጊዜ ሰሌዳ በአግባቡ ተጠቅመዋል። ድንገት ቢነቃ ተብሎም ይወስዱ ዘንድ የተሰጣቸውንም መመሪያ በጀግንነት ፈጽመዋል። እንደ ጀነራል ክንፈ አብርሃ፣ እንደ ስብሃት ነጋ፣ በካቴና ታስረው ዐማራን አላወረዱም። ይህ ድንገተኛ ሁነት ባይከሰት ኖሮም ይሄኔ ተልእኮአቸውን ፈጽመው ጎንደር ነበሩ። የሆነው ሆኖ ሚሽኑን 100% አሳክተዋል። አሳክተነዋልም። ቀጣዩን የአዲስ አበባ ተልእኮ ደግሞ መጠበቅ ነው የሚሉት ፋኖዎቹ። ይሄንኑ ለእኔ ያረጋገጡልኝን ቃል ባለፈው ሳምንት ከሮይተርስ የዜና ወኪል ጋር ሁለት ሰዓት ሙሉ በፈጀው ውይይታቸው ወቅት እንደረጋገጡለትም ነግረውኛል። አቢይ ከነግሳንግሱ ይወድቃል። ድርድር የሚባል ነገር የለም። አገዛዙ ይገረሰሳል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ይቀጥላሉ ነው የሚሉት ፋኖዎቹ። 

"…በወፎቼ በኩል ደግሞ አሰማርቼ ያስጠየቅዃቸው የአገዛዙ ባለ ሥልጣናት አሉ ብለው የሚነግሩኝ ነገር እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ። "ይሄ ለእኛ ለብልፅግናዎች ከባድ አደጋም፣ ኪሳራም ነው። ታዋቂ የፋኖ መሪ ሆኖ በዚህ ሰዓት ያውም በዚህ መልክ በዋና ከተማዋ ላይ በነፃነት ለብዙ ወራት ደብረዘይት፣ ናዝሬት፣ አምቦና ጅማ ድረስ መንቀሳቀስ ምን ዓይነት ድፍረት፣ ምን ያህል የተፈጥሮ ጀግንነት ቢኖረው ነው? ያውም በጠራራ ፀሐይ ከተማ ውስጥ በድፍረት መንቀሳቀሱ ያስደንቃል ነው የሚሉት አሉኝ። ወያኔ እንኳ በዚያ አቅሟ ያልሞከረችውን ከባድ እና አደገኛ ሚሽን ፋኖ በዚህ መልኩ መፈጸሙ የፋኖን አቅምና ጉልበት፣ ድርጅታዊ ጥንካሬም ነው የሚያሳየው። አሁን የመንግሥት ባለ ሥልጣናትን ለመጠበቅ የተመደበው የመከላከያና የፖሊስ ኃይሉን ራሱ መተማመን አይቻልም። በዘር ፖለቲካ በምትመራ ሀገር ኦሮሞ ነው ብለህ የቀጠርከው ሰው ዐማራ ላለመሆኑ ምን ዓይነት ማረጋገጫ የለንም። ቋንቋና ስም፣ የትውልድ ቦታ እየታየ ነው እንጂ የሚቀጠረው ወታደሩ የኦሮሞ፣ የደቡብም ሰው ስም ይዞ የዐማራ ፋኖ አለመሆኑን በምን እናውቃለን። ሁላችንም አደጋ ላይ ነን እያሉ እንደሆነም ነው የሚነግሩኝ ወፎቼ። እውነት ነው ብዙ ዐማሮች ኦሮሞ መስለው መገርሳና ቶሎሳ ተብለው እየተጠሩ ወሳኝ ቦታ ላይ አሉ።

"…ልጆቹ የተሰጣቸውን ተልእኮ አጠናቀዋል። በዚህ መሃል ግን የፖሊስ ክትትል በዛባቸው። እነርሱም አንድ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ዘግይቶ ገብቷቸዋል። መረጃዎቻቸውን በሙሉ ወደሚፈለገው ስፍራ አስቀድመው በመላክ አድርሰዋል። አብሮት የተሰዋው ሰው ጎንደር ደርሶ ተመልሶ ናሁሰናይን ይዞ ለመመለስ የገባ ታጋይ ነው። የዚያን የተሰዉ እለት ግን ከክትትሉ የተነሣ እንደሚያዙ ሲገባቸው በፍጥነት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ጀመሩ። ከቦሌ መድኃኔዓለም በሚሊኒየም አዳራሽ በ3ኛው በር በዚህ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሠረት ደፋር ቅርንጫፍ በኩል ሲወጡ ይከታተላቸው የነበረው የፖሊስ ኃይል እንዲቆሙ ይጠይቃቸዋል። እጃችሁን ስጡ ነው ፖሊስ የሚለው። የአጼ ቴዎድሮስ ልጆች ደግሞ እንደ እጅህን ስጥ የሚቀፋቸው፣ የሚጸየፉት ነገር የለም። ሞታቸውን ነው የሚመርጡት። እነርሱም ሳይቆሙ ወደፊት መንዳት ይቀጥላሉ። ፖሊሶቹም እነ ናሁሰናይ ያሉበትን መኪና ከፊትና ከኋላ መጥተው ገጭተው በኃይል ገጭተው በአደጋ ያስቆማቸዋል።  ከዚያስ…? ከዚያማ…

"…ይቀጥላል…

"…መኪናው እንደቆመ ሮጦ አምልጦ ለ25 ደቂቃ ተታኩሶ ለግማሽ ቀን ሙሉ መንገድ አዘግቶ፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን አስደንግጦ፣ አገዛዙን አሸብሮ፣ አየር መንገዱ በሪፐብሊካን ጋርድ እንዲወረር፣ እንዲጠበቅ አድርጎ ኋላ ላይ በጀግንነት የተሰዋው ማነው? የተሰዋው ልጅ አቤኔዘር ነው ወይስ ናሁሰናይ? ፖሊሶቹ ከመኪናው አስወጥተው መሬት ላይ ያስተኙት መኪናዋን ያሽከረክር የነበረው ልጅ ማነው? ከመኪናዋ ውረድ ብለው ካስወረዱት በኋላ ወርዶ ቁም ብሎ ኋላ ላይ ከወደቀበት ቆይቶ ቢነሣም መሣሪያ የደገነበትን ፖሊስ ተኩሶ መሬት ላይ የጣለው ማነው? ከዚያ እዚያው መኪናዋን ከለላ አድርጎ እየተታኮሰ ሳለ የተመታውና የወደቀው ፋኖ ማነው? የሚለውንና ተጨማሪ መረጃዎችን መረጃዎቹን ቃርሜ እንደጨረስኩ እመለሳለሁ። … ከታች ይቀጥላል…
76.1K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 13:36:46
መልካም…

"…የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቶ ሌላ ተጨማሪ 1ሺ አመስጋኝ ተገኝቷል። 2ሺ ሰው ዛሬ በእለተ ሥላሴ አመስግኗል። እግዚአብሔር ይመስገን እንደማለት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው፣ ሰይጣን ዲያብሎስን የሚያቃጥለው ሌላ ምንነገር አለ? ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።

"…በትግራይ ሙሉ ለሙሉ፣ በኦሮሚያ በከፊል፣ ሀገር ማስተዳደርን የተቀማው የብልጽግና አገዛዝ በዐማራ ክልል ደግሞ 85-90 % ቱን በፋኖ ተቀምቶ ባዶ እጁን ቀርቷል። የዐማራ ፋኖ አንድን መንግሥት መንግሥት የሚያሰኘውን የቀበሌ፣ የወረዳና የዞን ከተሞችን በሙሉ ተቆጣጥሯል። ፋኖ የዐማራ ክልልን የቀበሌና የወረዳ መዋቅር በጥንቃቄ ሠርቶ ጨርሶ የዐማራን ክልል በስፋት እያስተዳደረ ነው። ከዚህ ታላቅ ተግባር በኋላ ነው የዐማራ ፋኖ ከቀበሌ የሚጀምረውን የመንግሥት አስተዳደር ጨርሶ ዓይኑን ወደ ዋና መናገሻ ከተማዋ ጣል ማድረግ መጀመሩን እያየን ያለነው።

"…አርበኞቹ እነ ፋኖ ናሁሰናይ እና አቤኔዘር አዲስ አበባ ድረስ ምንዓይነት ተልእኮ ሊፈጽሙ ነው የተላኩት? ማንስ ነው ሰማእታቱን የላካቸው? እንደ አሸባሪ ከኪሳቸው የጸሎት መጻሕፍት የተገኘባቸው መንፈሳውያኑ ሰማእታት አብሪ ከዋክብቶቹ የዐማራ ቀንዲሎች እንዴት ተሰዉ? መረጃዎቹን በራሴ መንገድና አቅም አጣርቼ መጥቻለሁ። እናንተስ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?

"…አንድ 100 ሰው እስኪ…
77.0K viewsedited  10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 09:48:52
“…የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” ማቴ 8፥12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
82.9K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 23:19:37
"…እስከዚያው ይህቺን ባለ ሻኛ ድልብ መሃይም እየሰማችኋት እደሩልኝ…!
88.5K views20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 23:05:02
ለጎንደሮችም ለዐማሮች ሁሉ አሳዩአቸው…!

"…ሟች ናሁሰናይ ተኩሱ አልቆ፣ የኢቲቪ፣ የፋናና የዋልታ ጋዜጠኞች ካሜራ ይዘው መጥተው እስኪቀርጹት ድረስ በዚህ መልኩ ነበር ሲሰቃይ የነበረው። እነ አቢይ አሕመድ፣ እንዲህ ነበር አሰቃይተው ደሙን አፍስሰው፣ ሆስፒታል ሳይወስዱት በጥይት ደብድበው የገደሉት።

"…ይሄን የናሁሰናይን አሟሟት ለዐማራ ህጻናት አሳዩአቸው። የዓለም አቀፍ የወንጀለኛ አያያዝ በኢትዮጵያ በኦሮሞ ብልጽግና እንዴት እንደከረፋም አሳዩ። እንዲህ ዓይነት አሟሟት ሁሉም የብልፅግና አባል እንዲቀምሰው በማድረግ ጣፋጭ በቀል ያስፈልጋል።

"…ይሄ ወንድነት አይደለም። ዛሬ የኦሮሞና የትግሬ አክቲቪስቶች በዚህ ጀግና ሲሳለቁ ሳይ ውዬ እኔ ስስቅባቸው ነው የዋልኩት። ባለታንኳ፣ በለ ሮኬቷ፣ ባለ ቢኤሟ ወያኔ ያልሞከረችውን ባለ ክላሹ ፋኖ አዲስ አበባ ገብቶ አቅሙን አሳይቷል። ፈረንጅ አረቡንም አስደንግጧል።

"…በፋኖ ውስጥ ሆኖ ለወያኔ የሚሠራውን፣ ለብልጽግና በሆዱ የሚገዛውን፣ ትግል ለማስጠለፍ የሚሞከረውን ሁላ ይሄን የናሁሰናይን ሲቃና ስቃይ እያሳያችሁ አደብ እንዲገዛ አድርጉት።

"…እነ አቢይ አህመድ እና እነ ሽመልስ አብዲሳ ኦነጉን አቶ በቴ ኡርጌሳን አዋርደው ገድለው አስከሬኑን በቴሌቭዥን አላሳዩም። ናሁሰናይ እና አቤኔዘር ጋሻው ግን ዐማራ ስለሆኑ በአስከሬናቸው ተሳለቁ። ተሳሳቁ። አላገጡ። ዐማራ ለልጅህ ይሄን ቪድዮ አሳይ። ቂመኛ እና ተበቃይ የማይራራ ትውልድም ፍጠሩበት።

"…ፊልሙን የቀረጸው መንግሥት ነው። ያስቀረሁት እኔ ነኝ። እኔ ዘመድኩን። ዘመድኩን በቀለ። ወጣት ዐማሮች ሞታችሁን በአቤኔዘር እዩ። ባንዳውን አትማሩት። ለብአዴንና ለብአዴን ቤተሰቦችም ይሄን ቪድዮ በስልካቸው ላኩላቸው።

“…ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፤ በኃጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል።” መዝ 58፥10
38.7K views20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 22:19:29
"…አበደን እግዚአብሔር ምስክሬ ነው በዐማራ በኩል የሚቆም፣ የሚቋረጥ፣ የሚደክም፣ የሚደበዝዝ፣ የሚበተን፣ የሚሸማቀቅ፣ የሚሸነፍ፣ እጅ የሚሰጥ ታጋይም ሕዝብም የለም።

"…የዐማራ ፋኖ የውስጥ አሠራሩም አመራሩም እየጠራ ይሄዳል። ባንዳውም ከክልሉም ከሃገሪቱም እየተወገደ፣ እየጸዳ ይቀጥላል። እንዲያውም እየቆየ ሲሄድ የዐማራ ትግል ጣፋጭ የወይን ጠጅ እየሆነ ይመጣል። ሁሉም ልጠጣው፣ ላሽትተው፣ ላሽትተው የሚል፣ ያውም ፈረንጅም፣ ዓረብም የሚደመምበት።

"…ወያኔና ብልጽግና ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተሰብስበው ሲመክሩ ውለዋል። በዐማራ ስም የአገው ሸንጎው የወያኔ ዳይፐሩ ሰማ ጥሩነህ ተገኝቷል። በእነ ናሁሰናይ ጀብዱ ሰዎቹ የሚይዙትን፣ የሚጨብጡትን አሳጥቷቸዋል። በእውር ድንብር እቃም ሰውም መፍጀታቸው አይቀርም። የሆነው ሆኖ ከመሸነፍ በቀር ሌላ አማራጭ የላቸውም። እጅ መስጠት ብቻ።

"…የጎንደሩ ፋኖ አርበኛው ናሁሰናይን ቆስሎ ነው ቢያዝም ደሙ ፈስሶ እንዲያልቅና ተሰቃይቶ እንዲሞት ነበር የተፈረደበት። አልሞት ሲል ደግሞ የብልጽግናው ወታደሮች በሽጉጥ እንደበሳሱትና እንደገደሉት ነው የተሰማው። ጓደኞቻችንን ገድሎብናል ያሉ አንዳንዶች አስከሬኑን ለመብላት እንደ እብድ ያደርጋቸው እነደነበረም ተሰምቷል። የሆነማ ያልተለመደ አውሬ ተፈትቶ ተለቋል ነው የሚሉት የአይን እማኞች።

"…የሟች ቤተሰቦች አስከረኔን ለመቀበል ከጎንደር ድረስ ቢመጡም የአቢይና የዳንኤል አገዛዝ አስከሬኑን አልሰጥም ከማለቱም በላይ የሟቾቹን ወላጆች አስሯቸዋል። ምንአልባትም ሳይበሉት አይቀሩም ነው የሚሉኝ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች።

"…70 ሚልዮን ዐማራ እንዴት ብለህ ታሸንፈዋለህ? በሕይወት በመኖርና ባለመኖር መካከል የሚደረግ የህልውና ጦርነት እኮ ነው። ሀገር ትርምስምሱ ይወጣል እንጂ ዐማራ ወደ ኋላ አይመለስም።

• ይኸው ነው።
45.8K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 16:58:48
"…እንኳን ከፍ ላለ ግዙፍ ዓላማ ይቅርና በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ለጥፋትም ኃጢአት፣ ወንጀል ለመሥራትም እንኳ ቢሆን ጥብቅ የሆነ ዲሲፒሊን ወሳኝ ነው። ሃላስ።
73.8K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 15:47:14
መልካም… ርዕሰ አንቀጹ ይህን ይመስል ነበር። ይህ የእኔና የወፎቼ ሓሳብ ነው። እናንተ ደግሞ ቀረ የምትሉት ካለ ጨነምራችሁ፣ የበዛም ከሆነ ቀንሳችሁ እስቲ ሓሳባችሁን በጨዋ ደንብ አንሸራሽሩ። ስድብ ያስቀስፋል። ከተነሣው ሓሳብም ውጪ መቀባጠር ያስቀጣል። የምትቆጡም ካላችሁ በጨዋ ደንብ ተቆጡ። ተናግሬአለሁ።

• አንድ… ለማ… ሠለስተ… ጀምሩ…
77.1K views12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 14:24:49 "ርዕሰ አንቀጽ"

"…ከመሳይ መኮነን ጋር ከሚደዋወሉት ፋኖዎች ውስጥ በህይወት ያሉት በጣም ጥቂት ናቸው። እነርሱም ቢሆን አድራሻቸው ይታወቃል። በእርግጥ የፋኖ አመራሮች የእነ መሳይ መኮንን ሚዲያ ምርጫ ያደረጉበት ምክንያት ይታወቃል። የፋኖ አለቆቹ ለሕዝብ ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልእክት በነጻነት ለማስተላለፍ ከሌሎች የዐማራ ሚድያዎች የተሻለ ምቾት ስለሰጣቸው ነው። ምክንያቱም ከእንትና ጋር ስሩ፣ ይህን መንገድ ተከተሉ፣ እንትናን አትመኑት፣ እንትና ባንዳ ነው ወዘተ እያለ በትግላቸው ላይ ጣልቃ እየገባ የሚያደርቃቸው ጋዜጠኛ ስላልሆነ ነው። ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ እንዳይጠረጠር የተደረገ ነው።

"…ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እንደማንኛውም ታጋይ በመርህ ላይ የተመሰረተ ሙያዊ ጥያቄ ብቻ ፋኖዎችን የሚጠይቃቸው ቢመስልም፣ ከእገሌ ጋር ሁኑ፣ እገሌን አትመኑት ባይልም በቃለ መጠይቆቹ ግን መሪ ጥያቄዎችን ማዥጎድጎዱን አልተወም። ለምሳሌ የፋኖን የሰው ኃይል ብዛት? ያሉበትን ቦታ በመስቀልኛ ጥያቄ ይጠይቃል። "አሁን በምን ሁኔታ ላይ እና የት አካባቢ ናችሁ? የሚለው የተለመደ ጥያቄው ልብ ይሏል። ፋኖዎች ከዚህ የተነሣ እንደ መሳይ በመርህ ላይ የተመሠረተ የሚመስል ነገር ግን ውስጡ አደገኛ መርዝ የሆነ ጥያቄ የሚጠይቃቸው በማጣቸው ነው ወደእነ መሳይ የሄዱት ተብሎ ይታመናል። ነገር ግን በዚያም ተባለ በዚህ እየተበሉ ነው። መንግሥትም ፋኖዎቹ መሳይን በደንብ እንዲያምኑትና ግኑኝነታቸውን እንዲያጠነክሩ ለሁለተኛ ጊዜ በሽብር ከስሶላቸዋል።

"…የየፋኖ የላይኛው መዋቅር ከደኅንነት ክንፉ ጋር ተናቦ ''ብልሃት'' የተጓደለበት የትግል አካሄድ ለይቶ ፈጥኖ ማስተካከል ካልቻለ ውሎ አድሮ መዘዙ ብዙ መሆኑ ሊታሰብበት ይገባል። የሚዲያ፣ ኮሚኒኬሽን፣ ኢንዶክትሪኔሽን፣ ፕሮፓጋንዳ ሥራዎች ማዕከላዊነቱን ብቻ ጠብቆ መሠራት አለበት። በዚህ ረገድ የሚታዩ ክፍተቶች መታረም አለባቸው። በየወረዳው ያለ ፋኖ ሁሉ ቃል አቀባይ መሆን የለበትም። የሁሉም ፋኖ ስልክ ተቀምቶ ካልተጠረነፈ በቀር ስልክ የያዙት ፋኖዎች በሙሉ የት እንዳሉ ይታወቃል። ጭራሽ ይባስ ብለው እንደ ሲሳይ ሳተናው የሚባል ፋኖ ዓይነቱ በቀጥታ የቲክቶክ ስርጭት እንደነ ሞጣ እና ዮኒ ማኛ ሲሰዳደብ መዋሉ በፋኖ በኩል በቶሎ መስተካከል ያለበት ነገር ነው። ይሄ በጊዜ ካልታረመ የኋላ ኋላ አደጋውም የከፋ ነው።

"…አሁን አሁን አገዛዙ ከመደበኛ ውጊያ ውጪ በተጠና መንገድ የፋኖ መሪዎች፣ አስተባባሪዎች እና ታዋቂ ተዋጊዎችን ከመደበኛ የውጊያ እቅድ ውጭ አታሎ፣ አዘናግቶ፣ አማልሎ ለመግደል የሚጠቀማቸው ስልቶችና በወገን በኩል ትምህርት ያልተወሰደባቸው ግድፈቶች ተበራክተዋል። ክፍተቱ በዚህ በኩል ከቀጠለ ውጤቱ ከባድ ነው የሚሆነው። አሁን እንደ አዲስ ስልት አድርጎ አገዛዙ በፋኖ ላይ የነደፈው እቅድ እንደሚከተለው ነው።

፩ኛ፦ ወታደሩ ከአለንበት ካምፕ ወይም ምሽግ መጥታችሁ ውጊያ ከፍታችሁ አውጡን ብለው ወደ ፋኖ መሪዎች ይደውላሉ ወይም መንገድ ላይ ያገኙትን ሰው መልእከተኛ አድርገው ይልካሉ። ይህ ሲሆን፦

~ በፋኖ በኩል ጠላት ስልክ ቁጥራችንን ከየት አግኝቶት ነው የደወለልን ብሎ ያለመጠርጠር፣ ምን ያመጣል ባይነት ግብዝነት፣ አጉል ጀብደኝነት፣ አላስፈላጊ መስዋእትነት፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ጠቀሜታ የሌላቸው ውጊያዎች ጉልበትንና አቅምን፣ የሰው ኃይልን ከመጨረስ በቀር አዋጭ ያልሆኑ ናቸው።

~ በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን እኔ ያለሁት ገጠር ነው። አገዛዙ የት ያገኘኛል የሚል ባዶ ፉከራ እና የመሳሰሉ ግብዝ አስተሳሶበች ስላሉ በፍጥነት መታረም አለባቸው። ፋኖዎቹ ያልገባቸው ነገር ወደ ፋኖዎቹ የሚደወለው ሲግናል ዲቴክት ለማድረግ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።

፪ኛ፦ ልንከዳ ነው፤ ኑ ሽፋን ሰጥታችሁ አውጡን የሚሉ መልእክቶች ከወታደሩ በብዛት ይላካሉ ወደ ፋኖ አለቆች። ይሄም ውሸት ነው። ይሄም አንዱ አገዛዙ የነደፈው ስልት ነው። ይሰመርበት።

፫ኛ፦ እኛ ልንከዳ ነበር ነገር ግን የፋኖ አመራሮች መጥተው ካልተቀበሉን በቀር እናንተን ተራ ተዋጊዎች ስለሆናችሁ አናምንም የሚሉትም ውሸት ነው። መክዳት የፈለገ መክዳት፣ ወይም እዚያው ከካምፑ መጀመር ነው እንጂ አዋጊ ጀነራሉን፣ ኮሎኔሉን ከድቶ የምን እንደገና በረሃ ወርዶ አዋጊ ጀነራል ኮሎኔሉን ልወጋ እፈልጋለሁ ማለት ነው? የእገሌ ባለሥልጣን፣ የአቢይ ጋርድ የነበረ ኮማንዶ ነው ምናምን ትክክል አይደለም። አቢይን ሲጠብቅ ከርሞ አቢይን ከድቶ ጫካ በረሃ ወርዶ ከዚያ እየተዋጋ የከዳውን መሪ ሲገድል አስባችሁታል? ይሄም መታረም አለበት።

፬ኛ፦ የያዝነውን መሳሪያ እና ተተኳሽ ጥይት መሸጥ እንፈልጋለን። እኛን ሳይገድል ገንዘብ ከፍሎ መሳሪያውን የሚረከብ ታማኝ ሰው እንፈልጋለን የሚሉትም ዐውቀው ነው። ትግሉን ደግፎ ከሆነ ዋጋ ከፍሎ ነው እንጂ እንዴት ንግድ ቁማር ይፈጽማል…?

"…ለየትኛውም የፋኖ ኦፕሬሽን ፊቱ በሁሉ ዘንድ ፕሮፋይል ያለው ሰው እንዴት ይመረጣል? በዚህ መንግሥት መታወቂያ እያየ ከምኑም የሌለበትን ዐማራ ፋኖ ነህ እያለ በሚያሰቃይበት ዘመን የፋኖ አለቃ ሆኖ በሚዲያ፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚታወቅ ሰው መርጦ መላክ ትክክል አይሆንም። እነ ስዩም መስፍን ሰገራ እየተቀቡ፣ እብድ መስለው የሰለሉበት ሀገር ላይ፣ በጦርነት ወቅት ውጊያ ላይ ሲተኩስ ፎቶው፣ ቪድዮው የተበተነ ሰው ለኦፕሬሽን መላክ አግባብ አይሆንም።

"…የሆነው ሆኖ የፋኖ ከባድ ደወል በአዲስ አበባ ተደውሏል። የፋኖ ትግል አዲስ አበባ ገብቷል። የሚታረመው ታርሞ፣ የሚስተካከለው ተስተካክሎ፣ ትግሉ እንደሁ መቀጠሉ አይቀርም። ማሸነፉም እንዲሁ።

"…በፋኖ ትግል ውስጥ ወያኔ፣ ብአዴን፣ ግንቦት 7/ኢዜማ ራሱ ብልፅግና አይናቸውን መጣለቸው፣ መጎመዥተቸው አልቀረም። ትግሉ፣ ፍትጊያው ከባድ ነው። አሸናፊው ግን የዐማራ ፋኖ ነው። ብልፅግና ከዚህም በላይ ለዐማራ የደገሰው ድግስ እንዳለ ነው። የሃይማኖት ካርዱ አይደለም ለዐማራ ለምሥራቅ አፍሪካም የሚተርፍ ነው። መከላከያን ከዐማራ ክልል አውጥቶ ዐማራን በሚሊሻና በዐድማ ብተና አሰልጥኖ፣ አስታጥቆ፣ ከፋኖ ጋር እርስ በእርስ ለማጋደል ዝግጅቱንም ጨርሷል። በአድማ ብተናና በሚሊሻ ከሰለጠኑ በኋላ ከነትጥቃቸው ወደ ፋኖ የሚገቡት እንዳሉ ሆነው ይህ ያልገባቸው እና ከወንድሞቻቸው ጋር የሚተኮሱ እንዳሉም ሳይዘነጋ። እዚህ ላይም መሥራት ያስፈልጋል።

"…የፋኖ ቃልአቀባይነት ማዕከላዊነቱን ይጠብቅ። የፋኖዎቹ በሙሉ ስልካቸው ይጠርነፍ። እጅ የሚሰጡ፣ የሚከዱ ወታደሮች ፍተሻው ይጠንክር፣ ቢቻል ስልክ አለመጠቀም።

ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
79.3K views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ