Get Mystery Box with random crypto!

መልካም… '…የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቶ ሌላ ተጨማሪ 1ሺ አመስጋኝ ተገኝቷል። 2ሺ ሰው ዛሬ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቶ ሌላ ተጨማሪ 1ሺ አመስጋኝ ተገኝቷል። 2ሺ ሰው ዛሬ በእለተ ሥላሴ አመስግኗል። እግዚአብሔር ይመስገን እንደማለት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው፣ ሰይጣን ዲያብሎስን የሚያቃጥለው ሌላ ምንነገር አለ? ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።

"…በትግራይ ሙሉ ለሙሉ፣ በኦሮሚያ በከፊል፣ ሀገር ማስተዳደርን የተቀማው የብልጽግና አገዛዝ በዐማራ ክልል ደግሞ 85-90 % ቱን በፋኖ ተቀምቶ ባዶ እጁን ቀርቷል። የዐማራ ፋኖ አንድን መንግሥት መንግሥት የሚያሰኘውን የቀበሌ፣ የወረዳና የዞን ከተሞችን በሙሉ ተቆጣጥሯል። ፋኖ የዐማራ ክልልን የቀበሌና የወረዳ መዋቅር በጥንቃቄ ሠርቶ ጨርሶ የዐማራን ክልል በስፋት እያስተዳደረ ነው። ከዚህ ታላቅ ተግባር በኋላ ነው የዐማራ ፋኖ ከቀበሌ የሚጀምረውን የመንግሥት አስተዳደር ጨርሶ ዓይኑን ወደ ዋና መናገሻ ከተማዋ ጣል ማድረግ መጀመሩን እያየን ያለነው።

"…አርበኞቹ እነ ፋኖ ናሁሰናይ እና አቤኔዘር አዲስ አበባ ድረስ ምንዓይነት ተልእኮ ሊፈጽሙ ነው የተላኩት? ማንስ ነው ሰማእታቱን የላካቸው? እንደ አሸባሪ ከኪሳቸው የጸሎት መጻሕፍት የተገኘባቸው መንፈሳውያኑ ሰማእታት አብሪ ከዋክብቶቹ የዐማራ ቀንዲሎች እንዴት ተሰዉ? መረጃዎቹን በራሴ መንገድና አቅም አጣርቼ መጥቻለሁ። እናንተስ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?

"…አንድ 100 ሰው እስኪ…