Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ' '…ለምን ሳይጯጯህ፣ ግርግርም፣ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ሳይደነብር፣ ጫናም፣ የ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ለምን ሳይጯጯህ፣ ግርግርም፣ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ሳይደነብር፣ ጫናም፣ የዲፕሎማሲ ኪሳራም ሳይፈጠርብን ልጆቹን በሕይወት አልያዛችሁም? ለምን ያን ያህል ሰዓት ድረስ በመሃል አዲስ አበባ ያውም በቦሌ አየር መንገዱ አጠገብ ተኩስ እስኪከፈት፣ ጦርነት የተጀመረ እስኪመስል ድረስ ተዘናጋችሁ? ግማሽ ቀን ሙሉ መንገድ ተዘግቶ ደካማነታችን እስኪታይ እስኪጋለጥ ድረስ ምን ስትጠብቁ ነበር? ይሄ ድርጅት (ኢንሳን ማለቱ ነው) እንደ አዲስ ፈርሶ በድጋሚ መሠራት አለበት በማለት አቢይ አሕመድ የኢንሳ ሓላፊዎች ላይ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እብድ እያንባረቀ የሚጮህባቸው በእነ ፋኖ ናሁሰናይ እና አቤኔዘር የአዲስ አበባ ኦፕሬሽን ተበሳጭቶም፣ ደንግጦም ነው። አሁን ቆስሎ ተያዘ የተባለው ልጅ የሚያውቀው ነገር የለም። ዋናው የሚሽኑ ባለቤት ፋኖ ናሁሰናይ ነው።

"…ፋኖ ናሁሰናይ የዐማራ ፋኖ በጎንደር የአጼዎቹ ክፍለ ጦር የቀጠና ዘመቻ መምሪያ ሓላፊ ነበር። ፋኖ ናሁሰናይ የታወቀ የጦር መሪ ሆኖ ሳለ ወደ አዲስ አበባ የተላከው የታሰበውን ሓሳብ፣ የታቀደውን ዕቅድ ያለእሱ ሊፈጸም የሚችል ሌላ ሰው ስላልነበረ ብቻ ነበር ናሁሰናይ ወደ አዱ ገነት የሄደው። ናሁሰናይ በትምህርቱ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ስለነበረ በኢንጂነሪንጉ በኩል ደግሞ ሀገር ለመምራት ጣጣውን ጨርሶ የተቀመጠው ፋኖ ከዚያ በፊት አሁን በራሱ አቅም እያመረተ ስላለው የጦር መሣሪያ የሚያስፈልገውን የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት ከፍ ላለሌላ ጉዳይ የሚረዳውን ተግባር ለመፈጸም ነበር ልጁ የተላከው። እናም ልጁ የተሰጠውን ግዳጅ እና ተልእኮ ለማሳካት ቁጥሩ የማይታወቅ የሰው ኃይል ይዞ ነበር ወደ አዲስ አበባ የሄደው። በዚያም የከተመው። አደገኛም የሆነ ሪስክ ነበር የወሰደው።

"…እነ ናሁሰናይ ምንም ሳይነቃባቸው እየተዝናኑም፣ እየጨፈሩም፣ በእውቀት፣ በምርምር ላይ ለሚፈለገው የቴክኖሎጂ ጉዳይ የተሰጣቸውን ተልእኮ በሚገባ ፈጽመው፣ ጨርሰውም፣ እነርሱ ያልነበሩበት ነገር ግን ልክ በዛሬው እለት ሚያዚያ 7/2016 ዓም በእለተ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ በዓይነቱ ከባድ ነው የተባለ አስደናቂ የፋኖ ኦፕሬሽን እንዲፈጸም መመሪያም ሰጥቶ እሱና የተወሰኑቱ ባለፈው አርብ ሚያዝያ 4/2016 ዓም መጀመሪያ ወደ ሸዋ ከዚያም ወደ ጎንደር ለመመለስ አቅደው ጨርሰው ነበር በመሃል ይሄ ያልተጠበቀ ድንገተኛ ክስተት የተፈጸመው።

"…ከየት እንደሆነ ለጊዜው ባይታወቅም የአገዛዙ የስለላ ድርጅት መረጃው ዘግይቶ እንደደረሰው ይገመታል። ልጆቹ አዲስ አበባ እንደመጡ እንጂ ለምን እንደመጡ አገዛዙ አልደረሰበትም። በዚያ ሰዓት ቦሌ ምን እየሠሩ እንደነበረም አላወቀም። ነገር ግን ለሆነ ኦፕሬሽን ወይም ለራሳቸው ጉዳይ በዚያ እንደተገኙ ግን ገምግሟል። ታዛቢዎች የሚሉት በዚህ መጠን ታዋቂ የሆኑ ልጆች ይሄን አደገኛ ተልእኮ ወስደው ሳለ ለምን ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ታሳቢ አድርገው በፍጥነት ቦታ ስለመልቀቅ አላሰቡም ብለው በመጠየቅ ይቆጫሉ። ነገር ግን እነ ናሁሰናይን በላካቸውና ሚሽኑን በሰጣቸው አካል በኩል ደግሞ ይኸው ጥያቄ ሲነሣባቸው የሚመልሱት መልስ "ልጆቹ የተሠጣቸውን የጊዜ ሰሌዳ በአግባቡ ተጠቅመዋል። ድንገት ቢነቃ ተብሎም ይወስዱ ዘንድ የተሰጣቸውንም መመሪያ በጀግንነት ፈጽመዋል። እንደ ጀነራል ክንፈ አብርሃ፣ እንደ ስብሃት ነጋ፣ በካቴና ታስረው ዐማራን አላወረዱም። ይህ ድንገተኛ ሁነት ባይከሰት ኖሮም ይሄኔ ተልእኮአቸውን ፈጽመው ጎንደር ነበሩ። የሆነው ሆኖ ሚሽኑን 100% አሳክተዋል። አሳክተነዋልም። ቀጣዩን የአዲስ አበባ ተልእኮ ደግሞ መጠበቅ ነው የሚሉት ፋኖዎቹ። ይሄንኑ ለእኔ ያረጋገጡልኝን ቃል ባለፈው ሳምንት ከሮይተርስ የዜና ወኪል ጋር ሁለት ሰዓት ሙሉ በፈጀው ውይይታቸው ወቅት እንደረጋገጡለትም ነግረውኛል። አቢይ ከነግሳንግሱ ይወድቃል። ድርድር የሚባል ነገር የለም። አገዛዙ ይገረሰሳል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ይቀጥላሉ ነው የሚሉት ፋኖዎቹ። 

"…በወፎቼ በኩል ደግሞ አሰማርቼ ያስጠየቅዃቸው የአገዛዙ ባለ ሥልጣናት አሉ ብለው የሚነግሩኝ ነገር እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ። "ይሄ ለእኛ ለብልፅግናዎች ከባድ አደጋም፣ ኪሳራም ነው። ታዋቂ የፋኖ መሪ ሆኖ በዚህ ሰዓት ያውም በዚህ መልክ በዋና ከተማዋ ላይ በነፃነት ለብዙ ወራት ደብረዘይት፣ ናዝሬት፣ አምቦና ጅማ ድረስ መንቀሳቀስ ምን ዓይነት ድፍረት፣ ምን ያህል የተፈጥሮ ጀግንነት ቢኖረው ነው? ያውም በጠራራ ፀሐይ ከተማ ውስጥ በድፍረት መንቀሳቀሱ ያስደንቃል ነው የሚሉት አሉኝ። ወያኔ እንኳ በዚያ አቅሟ ያልሞከረችውን ከባድ እና አደገኛ ሚሽን ፋኖ በዚህ መልኩ መፈጸሙ የፋኖን አቅምና ጉልበት፣ ድርጅታዊ ጥንካሬም ነው የሚያሳየው። አሁን የመንግሥት ባለ ሥልጣናትን ለመጠበቅ የተመደበው የመከላከያና የፖሊስ ኃይሉን ራሱ መተማመን አይቻልም። በዘር ፖለቲካ በምትመራ ሀገር ኦሮሞ ነው ብለህ የቀጠርከው ሰው ዐማራ ላለመሆኑ ምን ዓይነት ማረጋገጫ የለንም። ቋንቋና ስም፣ የትውልድ ቦታ እየታየ ነው እንጂ የሚቀጠረው ወታደሩ የኦሮሞ፣ የደቡብም ሰው ስም ይዞ የዐማራ ፋኖ አለመሆኑን በምን እናውቃለን። ሁላችንም አደጋ ላይ ነን እያሉ እንደሆነም ነው የሚነግሩኝ ወፎቼ። እውነት ነው ብዙ ዐማሮች ኦሮሞ መስለው መገርሳና ቶሎሳ ተብለው እየተጠሩ ወሳኝ ቦታ ላይ አሉ።

"…ልጆቹ የተሰጣቸውን ተልእኮ አጠናቀዋል። በዚህ መሃል ግን የፖሊስ ክትትል በዛባቸው። እነርሱም አንድ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ዘግይቶ ገብቷቸዋል። መረጃዎቻቸውን በሙሉ ወደሚፈለገው ስፍራ አስቀድመው በመላክ አድርሰዋል። አብሮት የተሰዋው ሰው ጎንደር ደርሶ ተመልሶ ናሁሰናይን ይዞ ለመመለስ የገባ ታጋይ ነው። የዚያን የተሰዉ እለት ግን ከክትትሉ የተነሣ እንደሚያዙ ሲገባቸው በፍጥነት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ጀመሩ። ከቦሌ መድኃኔዓለም በሚሊኒየም አዳራሽ በ3ኛው በር በዚህ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሠረት ደፋር ቅርንጫፍ በኩል ሲወጡ ይከታተላቸው የነበረው የፖሊስ ኃይል እንዲቆሙ ይጠይቃቸዋል። እጃችሁን ስጡ ነው ፖሊስ የሚለው። የአጼ ቴዎድሮስ ልጆች ደግሞ እንደ እጅህን ስጥ የሚቀፋቸው፣ የሚጸየፉት ነገር የለም። ሞታቸውን ነው የሚመርጡት። እነርሱም ሳይቆሙ ወደፊት መንዳት ይቀጥላሉ። ፖሊሶቹም እነ ናሁሰናይ ያሉበትን መኪና ከፊትና ከኋላ መጥተው ገጭተው በኃይል ገጭተው በአደጋ ያስቆማቸዋል።  ከዚያስ…? ከዚያማ…

"…ይቀጥላል…

"…መኪናው እንደቆመ ሮጦ አምልጦ ለ25 ደቂቃ ተታኩሶ ለግማሽ ቀን ሙሉ መንገድ አዘግቶ፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን አስደንግጦ፣ አገዛዙን አሸብሮ፣ አየር መንገዱ በሪፐብሊካን ጋርድ እንዲወረር፣ እንዲጠበቅ አድርጎ ኋላ ላይ በጀግንነት የተሰዋው ማነው? የተሰዋው ልጅ አቤኔዘር ነው ወይስ ናሁሰናይ? ፖሊሶቹ ከመኪናው አስወጥተው መሬት ላይ ያስተኙት መኪናዋን ያሽከረክር የነበረው ልጅ ማነው? ከመኪናዋ ውረድ ብለው ካስወረዱት በኋላ ወርዶ ቁም ብሎ ኋላ ላይ ከወደቀበት ቆይቶ ቢነሣም መሣሪያ የደገነበትን ፖሊስ ተኩሶ መሬት ላይ የጣለው ማነው? ከዚያ እዚያው መኪናዋን ከለላ አድርጎ እየተታኮሰ ሳለ የተመታውና የወደቀው ፋኖ ማነው? የሚለውንና ተጨማሪ መረጃዎችን መረጃዎቹን ቃርሜ እንደጨረስኩ እመለሳለሁ። … ከታች ይቀጥላል…