Get Mystery Box with random crypto!

…ከላይኛው ይቀጠለ… '…አሁን ፋኖ አዲስ አበባ ነው። ዐማራ ሁሉ ፋኖ ነው። ፋኖ በፌዴሬሽን ም | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

…ከላይኛው ይቀጠለ… "…አሁን ፋኖ አዲስ አበባ ነው። ዐማራ ሁሉ ፋኖ ነው። ፋኖ በፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ፋኖ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ፋኖ በመከላከያ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በኢንሣ፣ በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ፣ በሚንስትሮች ምክር ቤት፣ በሁሉም ቦታ ነው ያለው። የዐማራ ፋኖ ማለት የዐማራ ሕዝብ በሙሉ ማለት ነው። የንግድ ባንክን፣ ቴሌን ወዘተረፈ ኤልፓን ጭምር በአንድ ጀምበር በተኖችን በመነካካት ብቻ ውድመት ሳያስከትል ሀገር ማጨለም፣ ሽባ ማድረግ የሚቻለው ነው ፋኖ ማለት። ፋኖ ማለት እየተታኮሰ ያለው ብቻ አይደለም። ስሙ ቶሎሳ፣ ገመቺስ ስለሆነ ኦሮሞ ነው ማለት አይደለም። ለምሳሌ የኢንሳን ልጆች የሚጠረጥሯቸውን በሙሉ ከፋኖ ኦፕሬሽን አስወጥተዋቸው ሙሉ በሙሉ በኦሮሞ ተክተዋቸዋል። አሁንም ግን የኢንሳ መረጃ በእጄ ነው። የኦሮሞ ስም መያዙ፣ የደቡብ ተወላጅ በቦታው መተካቱ፣ ለእኔ መረጃ ከመስጠት፣ ደማዊ ዐማራነቱን ያውም እልል ያለ ፋኖ ከመሆንም አያግደውም።

"…ይሄ እኔ በራሴ ጥረት የደረስኩበት መረጃ ነው። አሁን ከዛሬ ጀምሮ ትረካው ይቀየራል። ስሜን ሳይጠቅሱ እነ መሳይ መኮንንም፣ እነ ኢኤምኤስም፣ እነ ደረጄ ሀብተወልድም፣ እነ ሞጣ ቀራንዮም፣ ቲክቶከሩ ሁላ፣ ዩቲዩበሩም ትንተና ውስጥ ይገባል። ግርም እኮ ነው የሚሉኝ። እንዴት ሰው በጨበጣ ዜና ይሠራል? እንዴት ለቪው ብሎ የባጥ የቆጡን ይቀባጥራል? እኔ ግን ጋዜጠኛ አይደለሁም ግን ጋዜጠኛ ምን ሆን እንዴት ሙያውን አክብሮ መሥራት እንዳለበት አንብቤአለሁ። ከቃሌ ሐሰት ቢገኝ የሚገስጸኝ የጎንደር ፋኖ ነው። ሌላህን አልሰማህም። ይኸው ነው። ነጋዴዎች የመረጃ ምንጫችሁ እኔን ሳትጠቅሱ በሉ ሸቅሉ። በራሳቸው ትክክል ናቸውና ሌሎቹ የዘገቡትን ዘገባም አልቃወምም። ለትግሉ እስከጠቀመ ድረስ ምን ክፋት አለው?

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!