Get Mystery Box with random crypto!

'…አበደን እግዚአብሔር ምስክሬ ነው በዐማራ በኩል የሚቆም፣ የሚቋረጥ፣ የሚደክም፣ የሚደበዝዝ፣ የሚ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አበደን እግዚአብሔር ምስክሬ ነው በዐማራ በኩል የሚቆም፣ የሚቋረጥ፣ የሚደክም፣ የሚደበዝዝ፣ የሚበተን፣ የሚሸማቀቅ፣ የሚሸነፍ፣ እጅ የሚሰጥ ታጋይም ሕዝብም የለም።

"…የዐማራ ፋኖ የውስጥ አሠራሩም አመራሩም እየጠራ ይሄዳል። ባንዳውም ከክልሉም ከሃገሪቱም እየተወገደ፣ እየጸዳ ይቀጥላል። እንዲያውም እየቆየ ሲሄድ የዐማራ ትግል ጣፋጭ የወይን ጠጅ እየሆነ ይመጣል። ሁሉም ልጠጣው፣ ላሽትተው፣ ላሽትተው የሚል፣ ያውም ፈረንጅም፣ ዓረብም የሚደመምበት።

"…ወያኔና ብልጽግና ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተሰብስበው ሲመክሩ ውለዋል። በዐማራ ስም የአገው ሸንጎው የወያኔ ዳይፐሩ ሰማ ጥሩነህ ተገኝቷል። በእነ ናሁሰናይ ጀብዱ ሰዎቹ የሚይዙትን፣ የሚጨብጡትን አሳጥቷቸዋል። በእውር ድንብር እቃም ሰውም መፍጀታቸው አይቀርም። የሆነው ሆኖ ከመሸነፍ በቀር ሌላ አማራጭ የላቸውም። እጅ መስጠት ብቻ።

"…የጎንደሩ ፋኖ አርበኛው ናሁሰናይን ቆስሎ ነው ቢያዝም ደሙ ፈስሶ እንዲያልቅና ተሰቃይቶ እንዲሞት ነበር የተፈረደበት። አልሞት ሲል ደግሞ የብልጽግናው ወታደሮች በሽጉጥ እንደበሳሱትና እንደገደሉት ነው የተሰማው። ጓደኞቻችንን ገድሎብናል ያሉ አንዳንዶች አስከሬኑን ለመብላት እንደ እብድ ያደርጋቸው እነደነበረም ተሰምቷል። የሆነማ ያልተለመደ አውሬ ተፈትቶ ተለቋል ነው የሚሉት የአይን እማኞች።

"…የሟች ቤተሰቦች አስከረኔን ለመቀበል ከጎንደር ድረስ ቢመጡም የአቢይና የዳንኤል አገዛዝ አስከሬኑን አልሰጥም ከማለቱም በላይ የሟቾቹን ወላጆች አስሯቸዋል። ምንአልባትም ሳይበሉት አይቀሩም ነው የሚሉኝ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች።

"…70 ሚልዮን ዐማራ እንዴት ብለህ ታሸንፈዋለህ? በሕይወት በመኖርና ባለመኖር መካከል የሚደረግ የህልውና ጦርነት እኮ ነው። ሀገር ትርምስምሱ ይወጣል እንጂ ዐማራ ወደ ኋላ አይመለስም።

• ይኸው ነው።