Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ' '…ከመሳይ መኮነን ጋር ከሚደዋወሉት ፋኖዎች ውስጥ በህይወት ያሉት በጣም ጥቂት | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ከመሳይ መኮነን ጋር ከሚደዋወሉት ፋኖዎች ውስጥ በህይወት ያሉት በጣም ጥቂት ናቸው። እነርሱም ቢሆን አድራሻቸው ይታወቃል። በእርግጥ የፋኖ አመራሮች የእነ መሳይ መኮንን ሚዲያ ምርጫ ያደረጉበት ምክንያት ይታወቃል። የፋኖ አለቆቹ ለሕዝብ ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልእክት በነጻነት ለማስተላለፍ ከሌሎች የዐማራ ሚድያዎች የተሻለ ምቾት ስለሰጣቸው ነው። ምክንያቱም ከእንትና ጋር ስሩ፣ ይህን መንገድ ተከተሉ፣ እንትናን አትመኑት፣ እንትና ባንዳ ነው ወዘተ እያለ በትግላቸው ላይ ጣልቃ እየገባ የሚያደርቃቸው ጋዜጠኛ ስላልሆነ ነው። ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ እንዳይጠረጠር የተደረገ ነው።

"…ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እንደማንኛውም ታጋይ በመርህ ላይ የተመሰረተ ሙያዊ ጥያቄ ብቻ ፋኖዎችን የሚጠይቃቸው ቢመስልም፣ ከእገሌ ጋር ሁኑ፣ እገሌን አትመኑት ባይልም በቃለ መጠይቆቹ ግን መሪ ጥያቄዎችን ማዥጎድጎዱን አልተወም። ለምሳሌ የፋኖን የሰው ኃይል ብዛት? ያሉበትን ቦታ በመስቀልኛ ጥያቄ ይጠይቃል። "አሁን በምን ሁኔታ ላይ እና የት አካባቢ ናችሁ? የሚለው የተለመደ ጥያቄው ልብ ይሏል። ፋኖዎች ከዚህ የተነሣ እንደ መሳይ በመርህ ላይ የተመሠረተ የሚመስል ነገር ግን ውስጡ አደገኛ መርዝ የሆነ ጥያቄ የሚጠይቃቸው በማጣቸው ነው ወደእነ መሳይ የሄዱት ተብሎ ይታመናል። ነገር ግን በዚያም ተባለ በዚህ እየተበሉ ነው። መንግሥትም ፋኖዎቹ መሳይን በደንብ እንዲያምኑትና ግኑኝነታቸውን እንዲያጠነክሩ ለሁለተኛ ጊዜ በሽብር ከስሶላቸዋል።

"…የየፋኖ የላይኛው መዋቅር ከደኅንነት ክንፉ ጋር ተናቦ ''ብልሃት'' የተጓደለበት የትግል አካሄድ ለይቶ ፈጥኖ ማስተካከል ካልቻለ ውሎ አድሮ መዘዙ ብዙ መሆኑ ሊታሰብበት ይገባል። የሚዲያ፣ ኮሚኒኬሽን፣ ኢንዶክትሪኔሽን፣ ፕሮፓጋንዳ ሥራዎች ማዕከላዊነቱን ብቻ ጠብቆ መሠራት አለበት። በዚህ ረገድ የሚታዩ ክፍተቶች መታረም አለባቸው። በየወረዳው ያለ ፋኖ ሁሉ ቃል አቀባይ መሆን የለበትም። የሁሉም ፋኖ ስልክ ተቀምቶ ካልተጠረነፈ በቀር ስልክ የያዙት ፋኖዎች በሙሉ የት እንዳሉ ይታወቃል። ጭራሽ ይባስ ብለው እንደ ሲሳይ ሳተናው የሚባል ፋኖ ዓይነቱ በቀጥታ የቲክቶክ ስርጭት እንደነ ሞጣ እና ዮኒ ማኛ ሲሰዳደብ መዋሉ በፋኖ በኩል በቶሎ መስተካከል ያለበት ነገር ነው። ይሄ በጊዜ ካልታረመ የኋላ ኋላ አደጋውም የከፋ ነው።

"…አሁን አሁን አገዛዙ ከመደበኛ ውጊያ ውጪ በተጠና መንገድ የፋኖ መሪዎች፣ አስተባባሪዎች እና ታዋቂ ተዋጊዎችን ከመደበኛ የውጊያ እቅድ ውጭ አታሎ፣ አዘናግቶ፣ አማልሎ ለመግደል የሚጠቀማቸው ስልቶችና በወገን በኩል ትምህርት ያልተወሰደባቸው ግድፈቶች ተበራክተዋል። ክፍተቱ በዚህ በኩል ከቀጠለ ውጤቱ ከባድ ነው የሚሆነው። አሁን እንደ አዲስ ስልት አድርጎ አገዛዙ በፋኖ ላይ የነደፈው እቅድ እንደሚከተለው ነው።

፩ኛ፦ ወታደሩ ከአለንበት ካምፕ ወይም ምሽግ መጥታችሁ ውጊያ ከፍታችሁ አውጡን ብለው ወደ ፋኖ መሪዎች ይደውላሉ ወይም መንገድ ላይ ያገኙትን ሰው መልእከተኛ አድርገው ይልካሉ። ይህ ሲሆን፦

~ በፋኖ በኩል ጠላት ስልክ ቁጥራችንን ከየት አግኝቶት ነው የደወለልን ብሎ ያለመጠርጠር፣ ምን ያመጣል ባይነት ግብዝነት፣ አጉል ጀብደኝነት፣ አላስፈላጊ መስዋእትነት፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ጠቀሜታ የሌላቸው ውጊያዎች ጉልበትንና አቅምን፣ የሰው ኃይልን ከመጨረስ በቀር አዋጭ ያልሆኑ ናቸው።

~ በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን እኔ ያለሁት ገጠር ነው። አገዛዙ የት ያገኘኛል የሚል ባዶ ፉከራ እና የመሳሰሉ ግብዝ አስተሳሶበች ስላሉ በፍጥነት መታረም አለባቸው። ፋኖዎቹ ያልገባቸው ነገር ወደ ፋኖዎቹ የሚደወለው ሲግናል ዲቴክት ለማድረግ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።

፪ኛ፦ ልንከዳ ነው፤ ኑ ሽፋን ሰጥታችሁ አውጡን የሚሉ መልእክቶች ከወታደሩ በብዛት ይላካሉ ወደ ፋኖ አለቆች። ይሄም ውሸት ነው። ይሄም አንዱ አገዛዙ የነደፈው ስልት ነው። ይሰመርበት።

፫ኛ፦ እኛ ልንከዳ ነበር ነገር ግን የፋኖ አመራሮች መጥተው ካልተቀበሉን በቀር እናንተን ተራ ተዋጊዎች ስለሆናችሁ አናምንም የሚሉትም ውሸት ነው። መክዳት የፈለገ መክዳት፣ ወይም እዚያው ከካምፑ መጀመር ነው እንጂ አዋጊ ጀነራሉን፣ ኮሎኔሉን ከድቶ የምን እንደገና በረሃ ወርዶ አዋጊ ጀነራል ኮሎኔሉን ልወጋ እፈልጋለሁ ማለት ነው? የእገሌ ባለሥልጣን፣ የአቢይ ጋርድ የነበረ ኮማንዶ ነው ምናምን ትክክል አይደለም። አቢይን ሲጠብቅ ከርሞ አቢይን ከድቶ ጫካ በረሃ ወርዶ ከዚያ እየተዋጋ የከዳውን መሪ ሲገድል አስባችሁታል? ይሄም መታረም አለበት።

፬ኛ፦ የያዝነውን መሳሪያ እና ተተኳሽ ጥይት መሸጥ እንፈልጋለን። እኛን ሳይገድል ገንዘብ ከፍሎ መሳሪያውን የሚረከብ ታማኝ ሰው እንፈልጋለን የሚሉትም ዐውቀው ነው። ትግሉን ደግፎ ከሆነ ዋጋ ከፍሎ ነው እንጂ እንዴት ንግድ ቁማር ይፈጽማል…?

"…ለየትኛውም የፋኖ ኦፕሬሽን ፊቱ በሁሉ ዘንድ ፕሮፋይል ያለው ሰው እንዴት ይመረጣል? በዚህ መንግሥት መታወቂያ እያየ ከምኑም የሌለበትን ዐማራ ፋኖ ነህ እያለ በሚያሰቃይበት ዘመን የፋኖ አለቃ ሆኖ በሚዲያ፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚታወቅ ሰው መርጦ መላክ ትክክል አይሆንም። እነ ስዩም መስፍን ሰገራ እየተቀቡ፣ እብድ መስለው የሰለሉበት ሀገር ላይ፣ በጦርነት ወቅት ውጊያ ላይ ሲተኩስ ፎቶው፣ ቪድዮው የተበተነ ሰው ለኦፕሬሽን መላክ አግባብ አይሆንም።

"…የሆነው ሆኖ የፋኖ ከባድ ደወል በአዲስ አበባ ተደውሏል። የፋኖ ትግል አዲስ አበባ ገብቷል። የሚታረመው ታርሞ፣ የሚስተካከለው ተስተካክሎ፣ ትግሉ እንደሁ መቀጠሉ አይቀርም። ማሸነፉም እንዲሁ።

"…በፋኖ ትግል ውስጥ ወያኔ፣ ብአዴን፣ ግንቦት 7/ኢዜማ ራሱ ብልፅግና አይናቸውን መጣለቸው፣ መጎመዥተቸው አልቀረም። ትግሉ፣ ፍትጊያው ከባድ ነው። አሸናፊው ግን የዐማራ ፋኖ ነው። ብልፅግና ከዚህም በላይ ለዐማራ የደገሰው ድግስ እንዳለ ነው። የሃይማኖት ካርዱ አይደለም ለዐማራ ለምሥራቅ አፍሪካም የሚተርፍ ነው። መከላከያን ከዐማራ ክልል አውጥቶ ዐማራን በሚሊሻና በዐድማ ብተና አሰልጥኖ፣ አስታጥቆ፣ ከፋኖ ጋር እርስ በእርስ ለማጋደል ዝግጅቱንም ጨርሷል። በአድማ ብተናና በሚሊሻ ከሰለጠኑ በኋላ ከነትጥቃቸው ወደ ፋኖ የሚገቡት እንዳሉ ሆነው ይህ ያልገባቸው እና ከወንድሞቻቸው ጋር የሚተኮሱ እንዳሉም ሳይዘነጋ። እዚህ ላይም መሥራት ያስፈልጋል።

"…የፋኖ ቃልአቀባይነት ማዕከላዊነቱን ይጠብቅ። የፋኖዎቹ በሙሉ ስልካቸው ይጠርነፍ። እጅ የሚሰጡ፣ የሚከዱ ወታደሮች ፍተሻው ይጠንክር፣ ቢቻል ስልክ አለመጠቀም።

ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።