Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 412.24K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-04-20 19:41:02
"…የጩጬው ታላቅ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ አይደል። በትምሮም ቢሆን የኔታ ጋር የቆየሁት ሳይቆጠር 12+3 መጠንቀቄንም ላታውቁ ትችሉ ይሆናል። ግን እንደምንም ጨርሻለሁ። የእኔ ወነኛው ችግር በእግንጣልርኛ አፍ መናገር፣ ማንበብና መስማት አለመቻሌ ብቻ ነው እንጂ በሌላው እንኳ አፖስቶ ነህ ብሎኛል ራሱ ሙጂብ አሚኖ። እናም ምን ለማለት ፈልጌ ነው ሶዬውና ባርቲው የ50ኛ ዓመት የልደት በዓሌን በማስመልከት የተናገሩት ክፉ ነገር ይኖር ይሆን እንዴ? ዐውቃለሁ በልደቴ ቀን እንዲህ ብዬ ነገር ማንሳት እንደሌለብኝ ግን ካለ ብዬ ነው።

• አዛኜን እንኳንም ተወለድኩ።
46.5K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 18:38:05
"…50ኛ ዓመት የልደት በዓላችንን በማስመልከት የጀመርነው መርሀ ግብራችንእንደቀጠለ ነው።

"…በቀደመው ጦማር በእኔ ቅሬታ ያላችሁ ወገኖች ሞልጩኝ ሞላልጩኝ ብዬ ፈቃዴን ብሰጥም የሚሞልጨኝ አጣሁ። ጮጋ ከማለት በቀር ምን ላድርግ እንግዲህ?

"…ወፎቼም የልደት በዓላችንን በማስመልከት የመልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

• አዛኜን እንኳንም ተወለድኩ።
50.6K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 17:39:59
ፈቃድ ስለ መስጠት…

"…እስከ አሁን ድረስ 50ኛ ዓመት የልደት በዓሌን በማስመልከት የተወለድኩላቸው የመሰልኳቸው ወዳጆቼ እንደምታዩት በዛሬው እለት የእንኳን ተወለድክልን የደስታ መግለጫ እያጎረፉላችሁልኝ ይገኛል። ለዚህ ዳርቻ ለሌለው ፍፁም አክብሮታችሁ እና ፍቅራችሁ በእግዚአብሔር ስም ዝቅ ብዬ አመሰግናለሁ። ይሄ ለወዳጆቼ የቀረበ የምስጋና መልእክት ነው።

"…በሌላ በኩል ደግሞ ከዘመነ ነፃ ፕሬስ መጽሔት ወጋዜጣ፣ ከዚያም እስክባረር ድረስ ከዘመነ ፌስቡክና ዘመነ ዩቲዩብ፣ ከዚያም ወደ ዘመነ ቴሌግራም ከቴሌግራምም እስከ ቲክቶክ መንደር ድረስ እየተከተሉኝ፣ በዋልኩበት ውለው፣ ባደርኩበት አድረው በጭቃ ዥራፍ ስድባቸው የሚዠልጡኝ፣ ልክልኬን የሚነግሩኝ መስታወት የሆኑ ወዳጆችም አሉኝ። ለእነሱም ደግሞ ዛሬ እድል መስጠት አለብኝ።

"…ገና ዘመድኩን በቀለ የሚለውን ስም ተጽፎ ሲያዩ የሚነስራቸው። ድምጼን ሲሰሙ ቋቅ ለሚላቸው፣ መልኬን ሲያዩ እንደ ቡልጉ፣ እንደ ጭራቅ ለሚቆጥሩኝ፣ ካልሰደቡኝ ጤና ለማያገኙ ወዳጆቼ እድል ልሰጣቸው ይገባል። እነሱስ ያለ እኔ ማን አላቸው። እናም በእኔ በዘመዴ አንጀት ቆሽታችሁ እርር የሚል፣ የሚበግን ደምበኞቼ ጸያፍ ሆኖ የሰው ዓይን የማያቆሽሽ ውርጅብኝ ትወርዱብኝ ዘንድ ፈቃዴን ሰጥቻለሁ። ከ"አንት ቀፋፊ፣ አሸበርቲ፣ ሃያ፣ ሌባ፣ ኡሻ ምናምን ግን እንዳያልፍ። ተናግሬአለሁ። ምናባክንስህና፣ የትአባክ ምናምን የመሰሉ ሀገር በቀል ጥንታዊ ተግሳጾችም የተፈቀዱ ናቸው።

"…ይሄ ፖስት የ50ኛ ዓመት የልደት በዓሌን በማስመልከት ተቃዋሚዎቼ ይሞልጩኝ ዘንድ የለጠፍኩት ልጥፍ ነው። ሌሎች ወዳጅ ዘመዶቼ ግን እነሱ ስለተናገሩኝ፣ ስለሞለጩኝ እናንተ ስለ እኔ ትከላከሉ ዘንድ አያገባችሁም እና ኡስስ ዝም በሉ።

• ተንፕሱና ይውጣላችሁ…!
54.4K viewsedited  14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 13:32:04
የሲያትል ታሪካዊው የቱሪስት መስህብ ሥፍራ…!

"…እነ ሱሬ፣ ሙሌ፣ ዳኒ፣ ወንዴ፣ ነፍሱን በገነት ያኑርልንና መኴ ሆነው እኔ ከራየን ወንዝ ማዶ የመጣሁትን የጀርመኑን ሰው እና ከሜሪላንድ ሀገረ ማርያም የመጣውን ሳሚን ይዘው በከተማቸው እጅግ ድንቅ ታሪካዊ የሆነ ስፍራ፣ ያውም በዓመት ሚልዮኖች ከመላው ዓለም ወደሚጎርፉበት ታሪካዊ ስፍራን ሊያስጎበኙን በመሂናቸው አሳፍረውን ይዘውን ነጎዱ።

"…መሂናይቱን የሆነ ሰፈር አቁመው፣ እንደ ዝቋላ ያለ፣ እንደ ግሸንም ተራራ የመሰለ አስፓልት መንገድ በእግራችን እየተራመድን መጓዙን ተያያዝነው። አዲስ አበባ መርካቶ አዳራሽ አውቶቡስ ተራም አካባቢ በመሰለኝ ሰፈር አቋርጠን፣ እንደ ድሬደዋው ታይዋን ገበያ እየተሸሎኮለክን፣ የሃዋሳ ዓሣ ነጋዴዎችን የመሰሉ የዓሣ መሸጫ ስፍራዎችን አቋርጠን አይደረስ የለ የተባለው ታሪካዊ ስፍራ ደረስን።

"…This is ብሎ ጀመረ የእንግልጣር መምህሬ ሱሬ…This is one of the most attractive tourist destinations in seattle. አለ። ሱሬ እያስጎበኘ ስለሆነ አጠገቤ የነበረውን ሙሌን ጠየቅኩት። ምን እያለ ነው አልኩት። ሙሌም ቆይ ዳኒን ልጠይቅ ብለው ተመካክረው ተረጎሙልኝ። ለትርጉሙ ሳሚም ያዋጣ ይመስለኛል። ብቻ በሲያትል ምርጡ የቱሪስት መስህብ ስፍራ ነው ያሉኝ መሰለኝ።

"…ነጭና ጥቁር፣ ቻይናዊው፣ ዓረቡ በስፍራው ለጉብኝት ይጋፋል። የሚጎበኘውም ታሪካዊ ነገር በዚያ መንደር ውስጥ ባለ ግድግዳ ላይ ፍቅረኛ ማቾች ያኘኩትን ማስቲካ ግድግዳው ላይ ይለጥፋሉ። ጎብኚውም ያኘከውን ማስቲካ ከአፉ አውጥቶ ይለጥፋል። ፎቶ ተነሥተው ይሄዳሉ። አለቀ።

• አክሱም፣ ላሊበላ፣ የሐረር ግንብ፣ ሶፍኡመር፣ የፋሲል ግንብ ደኅና ሰንበት ብዬ እኔም ፎቶ ተነሥቼ ወደ ስደት ሀገሬ ነካሁት።

• አዛኜን እንኳንም ተወለድኩ…!
64.1K views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 12:34:02
"…መልካም…

"…ለወትሮው ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንገባው ወደ ተወዳጁ ርዕሰ አንቀጻችን ነበር። ለዛሬ ግን 50ኛ የልደት በዓላችንን በማስመልከት ዘና ፈታ፣ ደግሞም ቆንጠጥ የሚያደርጉ መርሀ ግብሮችን በቤታችን ስናካሂድ እንውላለን።

"…ፎቶው የእንግሊዝኛ መምህሬ የእነ ሱሬ መኖሪያ ሀገር የምትገኘው ሲያትል ከተማ ናት። በዚህች ከተማ እነ ሱሬ 49ነኛ የልደት በዓሌን በማስመልከት ያስጎበኙኝን ድንቅና ታሪካዊ ስፍራ ቀጥሎ አሳያችኋለሁ። ስፍራውን ለማየት ከመላው ዓለም በመቶ ሚልዮን የሚቆጠሩ ጎብኚዎች እንደሚጎርፉበት የነገሩኝ ደግሞ ሙሌ እና ዳኒ ናቸው። እኔና ሳሚ የሜሪላንዱ ፈዘዝን፣ ተደመምን አይገልጸውም።

• ማርያምን እንኳንም ተወለድኩ። እንኳንም ተወለድኩላቸው። እንኳንም ተወለድኩባቸው።
64.2K viewsedited  09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 10:40:16
"…እናንተው ዛሬ እኮ ልደቴ ነው። እንደ ቀልድ በዋዛ ፈዛዛ ምንም ዓይነት ቁምነገር ሳልሠራበት ዘመኔ እንደ ሸማኔ መወርወሪያ ሩጦ ተወርውሮ ዛሬ ሚያዚያ 12/2016 ዓም በእለተ ቅዱስ ሚካኤል ድፍን 50 ዓመት ሞላኝ። ለማንኛውም ስላሳለፍኳቸው 49 የውጣ ውረድ፣ የኀዘንና የደስታ፣ የስደት ዓመታት ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን። “…የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንገሠጻለንና።” መዝ 90፥10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
68.1K viewsedited  07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 22:27:24
"…የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ በተመለከተ የሁለቱም የአስተያየት መስጫ ሰንዱቆች ተከፍተዋል። ወደ መኝታ የመሄጃ ሰዓታችሁ እስኪደርስም ድረስ በጨዋ ደንብ መተንፈስ ትችላላችሁ። ሃላስ…
75.9K viewsedited  19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 21:39:31 "ርዕሰ አንቀጽ"

"…ከጠዋቱ የቀጠለ…

"…ውይይቱ በተቋረጠ ቀን የቀረ የጎንደር ፋኖ አልነበረም። እኔም የሆዴን በሆዴ፣ የልቤን በልቤ ይዤ ለጀማው ሰላምታ አቀረብኩ። ሁላቸውም ሰላምታዬን ተቀበሉኝ። እንደልማዳችን ማን መጣ? ማንስ ቀረ ብዬም ጠየቅኩ። አንደኛው ወገን ብቻ መምጣቱን፣ ሌላኛው ወገን ግን ዛሬም አለመቅረቡ ተነገረን። የቀሩበትም ምክንያት ተነገረ። የቀረበውም ምክንያት አሳማኝ ስለመሰለኝ ምክንያታቸውን ተቀብለን በይደር አቆየነው።

"…መሽቶ ነጋ። በሁለተኛው ቀን የተባለው የቀጠሮ ሰዓት ደረሰ። ሁላችንም በሰዓታችን ተገኘን። እንቅልፍ እንዳይጥለው ቀዝቃዛ ውኃ እግሩን ዘፍዝፎ የሚቀመጥም ነበር። የሆነው ሆኖ ዛሬም ግን አንደኛው ወገን አልመጣም። አለመምጣቱን ሳውቅ ዛሬም ለጸሎት እንነሣ ብዬ ቀቀሪውን አዘዝኩ። ጸሎት አድርገን ከፈጸምን በኋላ ግን የመረረ ንግግር አደረግኩ። ሽምግልናው የደረሰበትን አጠቃላይ ሂደትም ለሕዝብ ይፋ አድርጌ እቋጨዋለሁ ብዬም ሽምግልናውን አክብረው ለቀሩቱ ገለጥኩ። እናንተ ግን እግዚአብሔር ያክብራችሁ በርቱ በማለትም ተሰናበትኳቸው። ለምንአልባቱ ተፀፅተው ከተመለሱ፣ ለጎንደር አንድነት፣ ለዐማራ አንድነት አስበው ከተመለሱ አለሁ በእገሌ በኩል ልትጠሩኝ ትችላላችሁ ብዬ ነበር የተሰናበትኩት።

"…መሸ፣ ነጋ በሌላኛው ቀን ዛሬ ሆነ። የሽምግልናውን ውጤት ለሕዝብ ይፋ የማደርገው ነገ ቢሆንም ዛሬ ለነገው ዐዋጄ የመግቢያ ምልክት የሚሆን መብረቃዊ ብልጭታ ያለው ምልክት የመስጫ ዕለቴ ነበር።

"…የጎንደሩን ብቻ ሳይሆን የሸዋዎቹም የእርቁ ነጠላ ተሸምኖ አልቆ ቁጭቱ፣ መቋጭያው ላይ አንደኛው ወገን አስከ ዛሬዋ ድረስ አልተሳካለትም ነበር። እርቁ አልቆ፣ ይቅር መባባሉ አልቆ መቋጫው ላይ ሰይጣን ገብቶ ግግም ብሎም ነበር። በመሃል ሰይጣን የሸዋውን የተሰበሰበ ምርጥ ስንዴ ለመበተን ያልደከመው ድካም፣ ያል ጫራው ጭረት፣ ያልቆፈረው ጉድጓድ አልነበረም። እሳቱን እንደማጥፋት ቤንዚን ይዘው ለማቀጣጠል የሚሮጠውን መንጋ እያየሁ እታዘብ ነበር። ዐውቆ በድፍረት፣ ሳያውቅ በስህተት የተፈጠረን በደል ኃጢአት ይቅር እንደማለት ድንጋይ ይዞ ወጋሪው ለጉድ ነበር። እኔ ግን በደለ፣ ኃጢአት ሠራ የተባለውን ሁላ እያቀረብኩ ሁለተኛ እንዳትበድል የሚለውን የአምላኬን ወርቃማ ቃል እየጠቀስኩ በሰላም ኑሩ እያልኩ በመሸኘት በማጽናናትም በሁለቱም በኩል የሚረጨው ቤንዚል አካባቢ እሳትና ክብሪት እንዳያልፍ እየተሟገትኩ አይደረስ የለም ዛሬን ደረስኩ።

"…ጎንደሮችም ደወሉ። በቃ ልክ አላደረግንም። የጎንደር ታጋዮችንም ደም፣ የአጼ ቴዎድሮስንም አፅም አስወቅሰናል፣ በንፁሐን ዐማሮች በሚፈሰው ደማቸውም ጭምር ተወቅሰናል እናም ከወንድሞቻችን ተመልሰን በይቅርታ ለመቋጨት ተመልሰናል። አንተንም ዘመዴንም፣ ታዛቢ ሽማግሌዎችንም ቅር አሰኝተናል፣ እናም እንመለስና እንቋጨው በማለት ለእርቅ እጃቸውን ወደላይ ከፍ አድርገው ተማርከው ተመልሰዋል። እኔም የጠፋው ልጅ በተገኘ ጊዜ አባት የተደሰተውን ደስታ በሚያስንቅ መልኩ ተደስቼ እጄን ለሽምግልናው ዘርግቼ የቀጠሮውን ቀን በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ።

"…ሸዋዎቹም ደወሉ። አነጋገሩኝም። በኔትወርክ፣ በእኔ ያለመመቸት፣ በስንፍና፣ በቸልተኝነት የዘገየውንና የታዘዙትን በዛሬው ዕለት ፈጸሙ። አቅርቡ የተባሉትንም በሙሉ አቀረቡ። ተነጋገርን፣ ተወያየን፣ በደስታም ተቀጣጠርን። ውጤቱን በጋራ እናየዋለን። ሁሉም ውይይቶቻችን የተቀረጹ ናቸው። ታሪካዊ ቀረጻ። ለትውልድ የሚተላለፍ ቀረጻ ነው። እናም አሁን ልቤ አርፏል።

"…የእኔ ሽምግልና በሁሉም ጥሪና ምርጫ ነው። ሲያጠፉ በእኔ መገሰጽን መርጠው፣ ፈቅደው ነው የመረጡኝ፣ የጠሩኝም። ብዙ ሰዎች እሱ ምን አገባውም ሲሉ አደምጣለሁ። በተለይ ርእዮተ እስክንድር የሚለው የኋትስ ግሩፕ ላይ እሱ ምን አገባው? አለምአቀፍ የግጭት አፈታት አልተማረ፣ ማንበብና መጻፍ አይችል፣ እንግሊዝኛ አይናገር አይሰማ አይጽፍ፣ አያነብ፣ ምን አገባውና ነው እሱ ብለው ሲንጨረጨሩብኝ እንደሚውሉም አያለሁ፣ እመለከታለሁም። እግዚአብሔር ያሳያችሁ ጋሽ መሳፍንትን፣ ጋሽ ባዬን፣ ጋሽ መከታውንና ጋሽ አሰግድን ለማስታረቅ እንግሊዝኛ ማወቅ መስፈርት ሲሆን። ኮተታም ሁላ። ለማንኛውም በአማርኛ ቋንቋ እየተወያዩ ከዚህ ደርሰዋል።

"…ቲክቶክ ላይ አብዮት የሚያቀጣጥሉ፣ የሚያጫጭሱ፣ ፌስቡክ ላይ አቧራ የሚያጨሱ የትየለሌ ናቸው። ዐማራ የሚያሸንፍ መሆኑ ቁርጥ እየሆነ ሲመጣ በዐማራ በኩል ታዝለው 4ኪሎ የሚናፍቁም የትየለሌ ናቸው። የከሰረ ጡረተኛ ዳያስጶራ ሁሉ ቀሪ ዘመኑን በፋኖ ታዝሎ አንቱ፣ የተከበሩ ምኒስትር መባልን ፈልጎም ቋምጧል። ከአሁን ስንት ሕንፃ እንደሚሠራ ወስኖ ፕላንና ዲዛይን አሠርቶ የተቀመጠ የኡበር ሹፌር ሁላ አለ። እነ ወይዘሮ እገሊትም በቀረቡት ፋኖ ልክ ሙቀት እየተሰማቸው አዛዥ ናዛዥ የሆኑ ሁላ ቁጥር ስፍር የላቸውም።

"…ከጋዜጠኝነት ባሻገር የትግል ማኒፌስቶ አዘጋጅተው ፋኖን ለመጠምዘዝ የሚሞክሩ ምስኪኖች ሁላም አይቻለሁ። የፋኖ ትግል ከባድ ነው። አትችሉትም። የፋኖ ትግል የእግዚአብሔር ቁጣ ነው። ስዩም ተሾመ ተበሳጭቶ አረፋ ሲደፍቅ ሳየው አቢይ አሕመድ እንደተዠለጠ እና እየተነፋረቀ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። አሁን በዚሁ ከገገሙ። እኔንም ቢሆን በመሃላቸው አድርገው መነጋገር አቁመው በራሳቸው መንገድ፣ ባህል፣ ሃይማኖት መወያየት ከጀመሩ በዐማራ በኩል ነፋስ አይገባም።

"…በትግሉ የቆዩት አረጋውያኑ ለወጣቶቹም ዕድል እየሰጡ፣ እነሱ እንደበሬ፣ ወጣቶቹን እንደወይፈን አንድ ላይ አጣምሮ ማረስ ከጀመሩ ትግሉ ከዳር ይደርሳል። ከህወሓት ጋር ሳይሆን ከትግሬ ከሕዝቡ ጋርም ውይይት ቢጀመር ኦሮሙማው አይቀልድባቸውም ነበር። ብአዴኖችንም ቢሆን ሁሉንም ከመግፋት የሚመከረውን በቄስ በሼህ እየመከሩ የትግላቸው አጋር ቢያደርጉም መልካም ነው። አልመለስ ያለውን ደግሞ ያው መኮርኮም ተፈጥሮአዊ ነው። ከኦሮሞም ሆነ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ቢገፉአቸውም ዐማሮቹ ግን በቀደመ ፍቅራቸውና አቃፊነታቸው መቀጠል። መከላከያ ሠራዊቱ ሲማረክ በፍቅር መያዙን አጠንክረው መያዙ ያተርፉበታል።

"…በተረፈ በዐማራ ትግል ላይ መሽንክ ለመሆን የምትሞክር ዐማራ ነኝ ባይም ብትሆን እኔ የሀረርጌው ቆቱ መራታው ዘመዴ፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ አልፋታህም። የፈለግከውን በለኝ አልፋታህም። ጩህ እሪ በል። ቀውጠው ምንም አባክ አታመጣም። አልቅስ። መጪው ጊዜ የዐማራ ነው። ዐማራ የሚመራት ኢትዮጵያ እውን ትሆናለች። ፍቅር፣ ፍትሕ በምድሪቱ ይነግሳል። ክልል ይፈርሳል። ድንበር ከጎረቤት ሀገር ጋር ብቻ ነው የሚሰመረው። ደም አፍሳሾች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ዘራፊ ወንበዴዎች በሙሉ በፍትሕ ይዳኛሉ። የጃቸውንም ያገኛሉ። ኢትዮጵያዊ የሆነ በሙሉ ልቡ ከፈቀደበት ሥፍራ ሁሉ ለጤናው ተስማሚ ከሆነ ስፍራ ሂዶ የሚኖርበት፣ ሀብት አፍርቶ የሚኖርበት የተረጋጋ ሀገር ይፈጠራል። ለዚህም ተስፋ ሳልቆርጥ እደክማለሁ።

"…አንተ ቁጭ ብለህ አውራ፣ ፎግር፣ ፎትት፣ ተርብ፣ ደስኩር፣ እኔ ዘመዴ ግን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር በሟሟቅ ላይ እገኛለሁ። አለቀ።

• ድል ለዐማራው ፋኖ…!
• ለተገፋው ለዐማራው ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
76.0K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 18:07:16
"…እናንተው… ርዕሰ አንቀጹን ልቀጥልና ልቋጨው አይደል…?
78.8K views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 16:57:23 ከላይኛው የቀጠለ… "…እኔ ወደ እርቅ ውይይቱ ውስጥ ከመግባቴ በፊት ግን አምላኬ ባመለከተኝ ቀኝ ትከሻዬንም በሸከከኝ መልኩ የሁለቱንም አካላት የግለሰባዊም ሆነ የቡንድን ፍላጎት፣ ጠባይ፣ ርዕይ፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ አቋም ወዘተ ጥናት ለማድረግ ፈቃድ ጠይቄ፣ በዚያ ላይ ገዳማውያን በጸሎት እንዲያግዙኝ ሱባኤ አስይዤ፣ የጥሞና ጊዜም ወሰጄ፣ እነሱ እየቸኮሉ፣ አፍጥንልን እያሉ፣ እኔ ግን እንደ ሰጋር ፈረስ በልጓም ይዤ፣ ይዋል ይደርም ብዬ። ትእግስትን አስተምሬ፣ የምፈልገውን የተሟላ መረጃና ማስረጃ ከሰበሰብኩ በኋላ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ መጋቢት 27/2016 ዓም እነ ጋሽ መሳፍንት የሚመሩት ግሩፕ ደውሎልኝ የሽምግልናው ሂደት ተጀመረ። የአባቶች ጸሎት ሳይለየኝ ሁሉንም ገራም አደረገልኝ። ቀጥሎ የእነ ሟቹ ሜጀር ጀነራል ውብአንተ ቡድን የነበረውና አሁን አርበኛ ባዬ የሚመራውን ቡድን አነጋገርኩ። በመቀጠል ሁለቱንም ቡድኖች አገናኝቼ አነጋገርኩ። ተወያዩ፣ ተራረሙ፣ ወደ አንድነት የማየመጧቸውን ነገሮች ሁለቱም ሊተዉ ቃል ተገባቡ። አንደኛው ቡድን ምሎ፣ ያውም በአፄ ቴዎድሮስ አፅም፣ በታጋዮች በተሰዉት ደም፣ በጎንደር፣ አልፎም በዐማራ ሕዝብ ስም ምለው ከጨረሱ በኋላ ሌላኛው ቡድን ያፈርስ፣ ይተወው ዘንድ እንደ አንደኛው ቡድን ይምል ዘንድ ሲጠየቅ ስልኩ ተቋረጠ። ቡድኑ በሙሉ ድራሽ አባቱ ጠፋ። ለወትሮው በሰከንድ ይገኙ የነበሩት ሁሉ ጠፉ።

"…እኛም ተስፋ ሳንቆርጥ ውይይቱን አሳደርነው። ያኛውን ቡድን አመስግኜ፣ እነዚህንም ኔትወርክ ይሆናል ብዬ አሳምኜ፣ ክፉ ደግ ቃላት እንዳይናገሩም አሳስቤ። እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔርም ያክብራቸው እኒህኛዎቹ ክፉ ደግም ሳይናገሩ በይደር አሳደርነው። ያኛው ቡድን በተደጋጋሚ ይሠራ የነበረውን ዐውቃለሁ። ኔትወርኩ የተቋረጠበት እያስመሰለ የት ሄዶ ከማን ጋር እንደሚማከርም ዐውቃለሁ። የሚገርመው ነገር ግን እዚያኛው ቡድንም ውስጥ ሲገቡ ከዚያኛው ቡድን ውስጥ ያሉት ወፎቼ እኔን በጎን አስገብተው የሚሆነውን ሴራ ነሁሉ ማዳመጤ አልቀረም። እኔ ግን ይሄ ሁሉ ሴራ እያለ እያወቅሁ ውይይቱ ፍሬያማ እንደሆነ እና 99. 99999% ማለቁን ለሕዝቡ ሁሉ በቴሌግራም ገጼ አወጅኩ።

"…መሸ ነጋ፣ በነጋታው የስብሰባው ሰዓት ደረሰ። እንቅልፍ አጥተን፣ ከሰውነት ተራ ወጥተን፣ በስንት ድካም የጀመርነው ጉዳይ ከጫፍ ሳይደርስ በዚያኛው ወገን መጥፋት የተቋረጠውን ውይይት ለማስቀጠልና ቃላቸውን ለመቀበል ሁሉም ጓጓ። ዘወትር በሸዋውም፣ አሁንም በጸሎት ከፍተው በጸሎት የሚቋጩልን ካህንም ተገኝተዋል፣ የሁሉም ወገን ታዛቢዎች ገሚሱ ከእንቅልፉ ተቀስቅሶ፣ ገሚሱ ሥራ አስፈቅዶ፣ ገንዘቡን ከስክሶ፣ ተገኝቷል። ማሰንቆ አልቀረም ባለፈው ቀን ሲገኝ። የቀረ የጎንደር ፋኖ አልነበረም ውይይቱ የተቋረጠ ቀን። እናም እኔ የሆዴን በሆዴ፣ የልቤን በልቤ ይዤ ሰላምታ አቀረብኩ ለሁሉም…

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ቆይቶ ይቀጥላል… በትእግስት ጠብቁኝ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
79.4K views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ