Get Mystery Box with random crypto!

ፈቃድ ስለ መስጠት… '…እስከ አሁን ድረስ 50ኛ ዓመት የልደት በዓሌን በማስመልከት የተወለድኩላ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ፈቃድ ስለ መስጠት…

"…እስከ አሁን ድረስ 50ኛ ዓመት የልደት በዓሌን በማስመልከት የተወለድኩላቸው የመሰልኳቸው ወዳጆቼ እንደምታዩት በዛሬው እለት የእንኳን ተወለድክልን የደስታ መግለጫ እያጎረፉላችሁልኝ ይገኛል። ለዚህ ዳርቻ ለሌለው ፍፁም አክብሮታችሁ እና ፍቅራችሁ በእግዚአብሔር ስም ዝቅ ብዬ አመሰግናለሁ። ይሄ ለወዳጆቼ የቀረበ የምስጋና መልእክት ነው።

"…በሌላ በኩል ደግሞ ከዘመነ ነፃ ፕሬስ መጽሔት ወጋዜጣ፣ ከዚያም እስክባረር ድረስ ከዘመነ ፌስቡክና ዘመነ ዩቲዩብ፣ ከዚያም ወደ ዘመነ ቴሌግራም ከቴሌግራምም እስከ ቲክቶክ መንደር ድረስ እየተከተሉኝ፣ በዋልኩበት ውለው፣ ባደርኩበት አድረው በጭቃ ዥራፍ ስድባቸው የሚዠልጡኝ፣ ልክልኬን የሚነግሩኝ መስታወት የሆኑ ወዳጆችም አሉኝ። ለእነሱም ደግሞ ዛሬ እድል መስጠት አለብኝ።

"…ገና ዘመድኩን በቀለ የሚለውን ስም ተጽፎ ሲያዩ የሚነስራቸው። ድምጼን ሲሰሙ ቋቅ ለሚላቸው፣ መልኬን ሲያዩ እንደ ቡልጉ፣ እንደ ጭራቅ ለሚቆጥሩኝ፣ ካልሰደቡኝ ጤና ለማያገኙ ወዳጆቼ እድል ልሰጣቸው ይገባል። እነሱስ ያለ እኔ ማን አላቸው። እናም በእኔ በዘመዴ አንጀት ቆሽታችሁ እርር የሚል፣ የሚበግን ደምበኞቼ ጸያፍ ሆኖ የሰው ዓይን የማያቆሽሽ ውርጅብኝ ትወርዱብኝ ዘንድ ፈቃዴን ሰጥቻለሁ። ከ"አንት ቀፋፊ፣ አሸበርቲ፣ ሃያ፣ ሌባ፣ ኡሻ ምናምን ግን እንዳያልፍ። ተናግሬአለሁ። ምናባክንስህና፣ የትአባክ ምናምን የመሰሉ ሀገር በቀል ጥንታዊ ተግሳጾችም የተፈቀዱ ናቸው።

"…ይሄ ፖስት የ50ኛ ዓመት የልደት በዓሌን በማስመልከት ተቃዋሚዎቼ ይሞልጩኝ ዘንድ የለጠፍኩት ልጥፍ ነው። ሌሎች ወዳጅ ዘመዶቼ ግን እነሱ ስለተናገሩኝ፣ ስለሞለጩኝ እናንተ ስለ እኔ ትከላከሉ ዘንድ አያገባችሁም እና ኡስስ ዝም በሉ።

• ተንፕሱና ይውጣላችሁ…!