Get Mystery Box with random crypto!

የሲያትል ታሪካዊው የቱሪስት መስህብ ሥፍራ…! '…እነ ሱሬ፣ ሙሌ፣ ዳኒ፣ ወንዴ፣ ነፍሱን በገነት | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሲያትል ታሪካዊው የቱሪስት መስህብ ሥፍራ…!

"…እነ ሱሬ፣ ሙሌ፣ ዳኒ፣ ወንዴ፣ ነፍሱን በገነት ያኑርልንና መኴ ሆነው እኔ ከራየን ወንዝ ማዶ የመጣሁትን የጀርመኑን ሰው እና ከሜሪላንድ ሀገረ ማርያም የመጣውን ሳሚን ይዘው በከተማቸው እጅግ ድንቅ ታሪካዊ የሆነ ስፍራ፣ ያውም በዓመት ሚልዮኖች ከመላው ዓለም ወደሚጎርፉበት ታሪካዊ ስፍራን ሊያስጎበኙን በመሂናቸው አሳፍረውን ይዘውን ነጎዱ።

"…መሂናይቱን የሆነ ሰፈር አቁመው፣ እንደ ዝቋላ ያለ፣ እንደ ግሸንም ተራራ የመሰለ አስፓልት መንገድ በእግራችን እየተራመድን መጓዙን ተያያዝነው። አዲስ አበባ መርካቶ አዳራሽ አውቶቡስ ተራም አካባቢ በመሰለኝ ሰፈር አቋርጠን፣ እንደ ድሬደዋው ታይዋን ገበያ እየተሸሎኮለክን፣ የሃዋሳ ዓሣ ነጋዴዎችን የመሰሉ የዓሣ መሸጫ ስፍራዎችን አቋርጠን አይደረስ የለ የተባለው ታሪካዊ ስፍራ ደረስን።

"…This is ብሎ ጀመረ የእንግልጣር መምህሬ ሱሬ…This is one of the most attractive tourist destinations in seattle. አለ። ሱሬ እያስጎበኘ ስለሆነ አጠገቤ የነበረውን ሙሌን ጠየቅኩት። ምን እያለ ነው አልኩት። ሙሌም ቆይ ዳኒን ልጠይቅ ብለው ተመካክረው ተረጎሙልኝ። ለትርጉሙ ሳሚም ያዋጣ ይመስለኛል። ብቻ በሲያትል ምርጡ የቱሪስት መስህብ ስፍራ ነው ያሉኝ መሰለኝ።

"…ነጭና ጥቁር፣ ቻይናዊው፣ ዓረቡ በስፍራው ለጉብኝት ይጋፋል። የሚጎበኘውም ታሪካዊ ነገር በዚያ መንደር ውስጥ ባለ ግድግዳ ላይ ፍቅረኛ ማቾች ያኘኩትን ማስቲካ ግድግዳው ላይ ይለጥፋሉ። ጎብኚውም ያኘከውን ማስቲካ ከአፉ አውጥቶ ይለጥፋል። ፎቶ ተነሥተው ይሄዳሉ። አለቀ።

• አክሱም፣ ላሊበላ፣ የሐረር ግንብ፣ ሶፍኡመር፣ የፋሲል ግንብ ደኅና ሰንበት ብዬ እኔም ፎቶ ተነሥቼ ወደ ስደት ሀገሬ ነካሁት።

• አዛኜን እንኳንም ተወለድኩ…!