Get Mystery Box with random crypto!

ከላይኛው የቀጠለ… '…እኔ ወደ እርቅ ውይይቱ ውስጥ ከመግባቴ በፊት ግን አምላኬ ባመለከተኝ ቀ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከላይኛው የቀጠለ… "…እኔ ወደ እርቅ ውይይቱ ውስጥ ከመግባቴ በፊት ግን አምላኬ ባመለከተኝ ቀኝ ትከሻዬንም በሸከከኝ መልኩ የሁለቱንም አካላት የግለሰባዊም ሆነ የቡንድን ፍላጎት፣ ጠባይ፣ ርዕይ፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ አቋም ወዘተ ጥናት ለማድረግ ፈቃድ ጠይቄ፣ በዚያ ላይ ገዳማውያን በጸሎት እንዲያግዙኝ ሱባኤ አስይዤ፣ የጥሞና ጊዜም ወሰጄ፣ እነሱ እየቸኮሉ፣ አፍጥንልን እያሉ፣ እኔ ግን እንደ ሰጋር ፈረስ በልጓም ይዤ፣ ይዋል ይደርም ብዬ። ትእግስትን አስተምሬ፣ የምፈልገውን የተሟላ መረጃና ማስረጃ ከሰበሰብኩ በኋላ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ መጋቢት 27/2016 ዓም እነ ጋሽ መሳፍንት የሚመሩት ግሩፕ ደውሎልኝ የሽምግልናው ሂደት ተጀመረ። የአባቶች ጸሎት ሳይለየኝ ሁሉንም ገራም አደረገልኝ። ቀጥሎ የእነ ሟቹ ሜጀር ጀነራል ውብአንተ ቡድን የነበረውና አሁን አርበኛ ባዬ የሚመራውን ቡድን አነጋገርኩ። በመቀጠል ሁለቱንም ቡድኖች አገናኝቼ አነጋገርኩ። ተወያዩ፣ ተራረሙ፣ ወደ አንድነት የማየመጧቸውን ነገሮች ሁለቱም ሊተዉ ቃል ተገባቡ። አንደኛው ቡድን ምሎ፣ ያውም በአፄ ቴዎድሮስ አፅም፣ በታጋዮች በተሰዉት ደም፣ በጎንደር፣ አልፎም በዐማራ ሕዝብ ስም ምለው ከጨረሱ በኋላ ሌላኛው ቡድን ያፈርስ፣ ይተወው ዘንድ እንደ አንደኛው ቡድን ይምል ዘንድ ሲጠየቅ ስልኩ ተቋረጠ። ቡድኑ በሙሉ ድራሽ አባቱ ጠፋ። ለወትሮው በሰከንድ ይገኙ የነበሩት ሁሉ ጠፉ።

"…እኛም ተስፋ ሳንቆርጥ ውይይቱን አሳደርነው። ያኛውን ቡድን አመስግኜ፣ እነዚህንም ኔትወርክ ይሆናል ብዬ አሳምኜ፣ ክፉ ደግ ቃላት እንዳይናገሩም አሳስቤ። እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔርም ያክብራቸው እኒህኛዎቹ ክፉ ደግም ሳይናገሩ በይደር አሳደርነው። ያኛው ቡድን በተደጋጋሚ ይሠራ የነበረውን ዐውቃለሁ። ኔትወርኩ የተቋረጠበት እያስመሰለ የት ሄዶ ከማን ጋር እንደሚማከርም ዐውቃለሁ። የሚገርመው ነገር ግን እዚያኛው ቡድንም ውስጥ ሲገቡ ከዚያኛው ቡድን ውስጥ ያሉት ወፎቼ እኔን በጎን አስገብተው የሚሆነውን ሴራ ነሁሉ ማዳመጤ አልቀረም። እኔ ግን ይሄ ሁሉ ሴራ እያለ እያወቅሁ ውይይቱ ፍሬያማ እንደሆነ እና 99. 99999% ማለቁን ለሕዝቡ ሁሉ በቴሌግራም ገጼ አወጅኩ።

"…መሸ ነጋ፣ በነጋታው የስብሰባው ሰዓት ደረሰ። እንቅልፍ አጥተን፣ ከሰውነት ተራ ወጥተን፣ በስንት ድካም የጀመርነው ጉዳይ ከጫፍ ሳይደርስ በዚያኛው ወገን መጥፋት የተቋረጠውን ውይይት ለማስቀጠልና ቃላቸውን ለመቀበል ሁሉም ጓጓ። ዘወትር በሸዋውም፣ አሁንም በጸሎት ከፍተው በጸሎት የሚቋጩልን ካህንም ተገኝተዋል፣ የሁሉም ወገን ታዛቢዎች ገሚሱ ከእንቅልፉ ተቀስቅሶ፣ ገሚሱ ሥራ አስፈቅዶ፣ ገንዘቡን ከስክሶ፣ ተገኝቷል። ማሰንቆ አልቀረም ባለፈው ቀን ሲገኝ። የቀረ የጎንደር ፋኖ አልነበረም ውይይቱ የተቋረጠ ቀን። እናም እኔ የሆዴን በሆዴ፣ የልቤን በልቤ ይዤ ሰላምታ አቀረብኩ ለሁሉም…

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ቆይቶ ይቀጥላል… በትእግስት ጠብቁኝ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።