Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ' '…ዐማራ ማሸነፉን 100% አረጋግጧል። መጪው ጊዜም ዐማራ የሚመራት ኢትዮጵያ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ዐማራ ማሸነፉን 100% አረጋግጧል። መጪው ጊዜም ዐማራ የሚመራት ኢትዮጵያ መወለዷ እውን ሆኗል። ይሄን ተቃራኒ ወገኖችም፣ የሩቅም የቅርብም ታዛቢዎች በሚገባ ተረድተዋል። ህወሓትም ብልፅግናም አምነዋል። ነገር ግን ዐማሮቹ እየተጨቃጨቁ ያሉት እዚህ ላይ ለመግለጽ በምቸገርበት አስቂኝ ቀላል ጉዳይ ላይ ነው። ትግሉ ነገር ዓለሙን ጣጣውን ጨርሷል። አሁን በማይረባ አጀንዳ ላይ ተቸንክረው እንዲቀሩ አኞ ሥጋ ወርውረውላቸው ከእርሱ ጋር ሲታገሉ እንዲውሉ አድርገዋቸው ነው እንጂ ዐማራው ተራራው 99. 99999% የቤት ሥራ ጣጣውን ጨርሷል። የቀረችዋ ነጥብም ቀላል አይደለችም። የምትናቅም አይደለችም። ከራስ ደጀን ተራራ፣ ከዝቋላና ከኪሊማንጃሮ ተራራ፣ ከሂማሊያ ተራሮች የገዘፈ፣ የረዘመ መስሎ የሚታይ የሚመስል ሽርፍራፊ ነጥብ ነው የቀረው። ነገር ግን ጫን አድርጎ የሚይዝ ገለልተኛ ሽማግሌ ፈጥርቆ ቢይዘው የሚበን፣ የሚተን ተራራ ነው ነጥቡ። የጥጥ ከረሜላ በሉት፣ ሲያዩት ግዙፍ ሲቀርቡት ጥጥ። ደፋር ከተገኘ ይፈታል። ደግሞም ይፈታል። እየፈታነውም ነው።

"…ወያኔ የዐማራውን አቅም አይታዋለች። ገምግማዋለችም። ወያኔ ከነገሩ፣ ከአጀንዳው ወጥታ ትግሬዎች ከዐማራ ጋር ከተጠቃቀሱ፣ በመሬት ጉዳይ ማለቃቀስ አቁመው ከተጣመሩ የብልፅግና ጉዳይ አፈር ከደቼ ነበር የሚበላው። ዐማራው ያለ ትግሬ እገዛና ያለማንም እርዳታ ሥርዓተ መንግሥቱን ከወንበዴ አራጁ ለመቀበል ከጫፍ ደርሷል። ለትግሬ መዳኛ መድኅኑ ወንድሙ ዐማራው ብቻ ነበር። ከፈለገ ከነቃ ብቻ። አዲስ አበባ የተጎለተው ብልጽግና የቀብር ስፍራውን ማሳመር ብቻ ነው የተያያዘው። ገላን ከተማ ላይ የብር ማተሚያ ፋብሪካ ከፍቶ እንደ ጉድ የሚያትመው ብር የሚያድነው መስሎታል። ፋብሪካውን እለጥፍላችኋለሁ። ይህ ሲባል ሸገር ሲቲ ጫፍ ያሰፈሩት ኦነግ አይረብሽም ማለት አይደለም። አለሁ አለሁ ለማለት ሜካፕ ተቀብቶ ስብሰባ የሚያበዛው ብልፅግና እንደሚሞት ወላጆቹ የሆኑት እነአሜሪካም፣ አውሮጳ ዓረቦቹም ዐውቀዋል። ተረድተዋልም። በቀደም ጄኔቫ የተሰበሰቡትም የተዝካር የ40 እና የ80 ማውጫ፣ የሃውልትና የቀብር ሥርዓት ማስፈጸሚያ ብር ለማዋጣት ፈልገው ነው። የማደጎ ልጃቸው ምን አልባት ታክሞ ከዳነም ብለው ነው የወላጅ ነገር ሆኖባቸው ገንዘብ ለማዋጣት የደከሙት። ለሞተ፣ ለበከተ፣ ለገማ፣ ለሸተተ፣ ሰው መሳይ በሸንጎ ነው ገንዘብ ለማዋጣት መዘፍዘፋቸው ያተረፈላቸው ውርደት ነው። የሚገርመው ነገር በጄኔቫው ስብሰባ የስደት ሀገሬ ጀርመንን ጨምሮ በአካል እየረዱት፣ እያገዙት ያሉት እነ ጣልያን፣ ፈረንሳይ እና የዓረብ ሃገራት አልረዱትም። RIP ብልጽግና።

"…እነ ግንቦት 7ን ፋኖን እስከ ማጣጣል፣ አናቱ ለሁለት ይከፈልና የአንዳርጋቸውም ጽጌ ፋኖ ተከፋፍሏል ብሎ እስከመበጥረቅ ያደረሰው የዐማራ ፋኖ የሌሎችን ጣልቃ ገብነት የመከላከል አቅሙን ከ0% ወደ 99. 99999% መድረሱን ስላዩ ነው። የፈረሰውና እስክንድር የሚመራው ሕዝባዊ ግምባር ወደ ሕዝባዊ ሠራዊት ከተቀየረ በኋላም ከእስክንድር ኋላ ያሉ ሰዎች በእስክንድር በኩል እጃቸውን አስረዝመው በዐማራ ፋኖ ውስጥ ለመዳከር መራወጣቸው አልቀረም። እሱም ቢሆን ይሄ መራወጥ አሁን የዐማራው ፋኖ መንቃት ከ0% ወደ 99. 99999% ማደጉ ፉርሽ እያደረገው መጥቷል። ግንባር በለው ሠራዊት በለው፣ ወያኔ በለው አደጋ የመሆን መጠናቸው ቀንሷል። ማዶና ማዶ ሆነው በስደት በጋዜጠኝነት ስም የጋዜጠኝነት ካባ ለብሰው ለዐማራ ፋኖ የመታገያ ማኒፌስቶ የሚያዘጋጁ ፌስታል ፊቶችም በጊዜ ተገፍተው ጥጋቸውን እየያዙ ነው። እነሱ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር ቢኖር ድሮ በደኅና ጊዜ በድብቅ የቀረጹትን የስልክ ውይይት ለማፍረሻነት መጠቀም ብቻ ነው። ልክ የጎጃሙን ማርሸት የእስክንድር ነጋዋ ገንዘብ ያዥ ወሮ ሕይወት በጄኖሳይድ ጉዳይ ቀርጻው አሁን እንደበተኑት ማለት ነው። ወዳጄ በግለሰቦች የግል የስልክ ሀሜት ምክንያት የሚቆም የዐማራ ትግል ግን የለም። አበደን የለም።

"…ሌላው ሞጣ ቀራንዮ እንዳለው የብአዴንም አልሞት ባይ ተጋዳይነት እንቅፋት መፍጠሩ አልቀረም። አሁን ባለው መረጃ አንደኛው ብአዴን በራያ በኩል ከትግሬዎቹ ጋር ተጠቃቅሶ አስቸጋሪ ናቸው የተባሉትን የብልጽግና ሰዎች ማጽዳታቸው፣ የፋኖም ኃይል በዐማራ አድማ ብተናና በዐማራ ሚልሻ እንዲጠናከር ማድረግ ሲታይ የሆነ ነገር መሽተቱ አይቀርም። ብአዴን ሙሉ በሙሉ አደረጃጀቱን ይዞ እኔ ካልመራሁት የሚለውን ዲስኩሩን ይዞ የነበረው ነገር ነው ሞጣ ፋኖ አዲስ አበባ አይገባትም ሲያስብለው የኖረው። በተለይ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቡድን በኩል ከኤርትራ ጋር ባለው ግኑኝነት በሚያቀርበው ሎጀስቲክ የዐማራ ፋኖን ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው መፍጨርጨርም 99. 99999% እየሞተ ስለሆነ አሁን ፋኖን ለመከፋፈል አቅም የለውም። RIP ገዱ።

"…ብዙዎቻችሁ የምትንቁት በሳቅ በፈገግታም ነውር ቃሉን እየጠጣችሁ የምታልፉት ሞጣ ቀራንዮ ወይም ወንድሙ የጎጃም ብአዴን የብልጽግና ሰው የሆነው ሂውስተን ቴክሳስ የሚኖረው አቶ ማማሩ መንግስቴ አንለይም የዋዛ ሰው አይምሰላችሁ። ሞጣ ቀራንዮ "ፋኖ አዲስ አበባ አይገባም። ፋኖ አዲስ አበባ እንዳይገባ ያደረግነው እኛ ነን። የሚኒልክ ቤተ መንግሥት እንገባለን ብላችሁ አልነበር? ታዲያ ከምን አትገቡም? ፋኖ አዲስ አበባ እንዲገባም፣ እንዳይገባም የምናደርገው እኛ ነን ብሎ የሚበጠረቀው እንዲሁ ዝም ብሎ ፋራ ስለሆነ የሚመስለው የትየለሌ ሰው ነው ያለው። ሞጣ እውነቱን ነው። ሞጣን የያዙት የወሎ ብአዴኖች እነ ደመቀ መኮንን እና እነ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው። ለዚህ ነው ሞጣ ገዱንና ደመቀን የሚያሞካሸው። ሞጣ በከፈሉት ገንዘብ ልክ ነው የነገሩትን ይዞ የሚበጠረቀው። ብአዴንም በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ፋኖን ይዘናታል ብለው ነበር የሚያምኑት። ደግሞም እውነት ነበር። አሁንም የብአዴን እጁ በፋኖ ውስጥ ጠፍቷል ማለት አይደለም። የብአዴን እጁ ረጅም ነው። ይሄንንም በራያ እና በወልቃይት በኩል ስላለው ሁኔታ መረጃው የለኝም እንጂ አምላከ ዐማራ ወኢትዮጵያ ልዑል እግዚአብሔር ረድቶኝ በሸዋና በጎንደር 99. 99999% የብአዴንን ሴል አፍርሰን ጨርሰነዋል። አንገቱ ላይ የቆምንበት አለ። የሚያጣጥር አለ። ለፋኖ የገበረ እጁን የሰጠም አለ። ብአዴን በሸዋ እና በጎንደር ያለውን እጁን ቆርጠነዋል። ጎምደነዋል። እስትንፋሱ ደግሞ በቅርቡ ያቆማል።

"…የጎንደር ፋኖዎች በሰው ኃይል፣ በፖለቲካ ንቃተ ህሊና፣ በሎጀስቲክ፣ በኔትወርክ፣ በጀግንነት፣ በመግባባት፣ በመደማመጥ ቀድሞ በመንቃት ከሌሎቹ የተሻለ ልምድ ያላቸው ናቸው። ከኋላ የመጣው ጎጃም እና ወሎም ጀግንነቱ ተነግሮ፣ ተዘርዝሮም አያልቅም። ሸዋ ወያኔ በልታ ጨርሳው። ብአዴን ሽባ አድርጎት ቢኖርም በዚህ 4 ዓመት እንደ እንቦሳ ጥጃ ነው እንደ አዲስ ተወልዶ የወይፈን ጉልበት ይዞ ጋራ ሸንተረሩን የሞላው። ጎንደሮች ምን ቀድመው ቢደረጁ ለሁለት መከፈላቸው አልቀረም። አንደኛው ቡድን ፋፍዴን፣ ብአዴን ወዘተረፈ፣ ሌላኛውን ቡድን ግምባሩ፣ ሠራዊቱ የሚባሉት ቀርበው አንቀው ይዘዋቸው ነበር። ሌሎቹን ቀፍዳጆች እዚህ ላይ አላነሣም። የሆነው ሆኖ በሸዋ በእነ ጋሽ አሰግድ እና ሻለቃ መከታው መካከል የነበረውን ጠብ ለዝቦ፣ አርቀነውም ወደ አንድነት ለማምጣት የነበረኝን የሽምግልና ውጤት የሰሙት ጎንደሮች ሁለቱም ቡድኖች አሜሪካና ጎንደር ባሉ ወኪሎቻቸው በኩል ቀረቡኝ። መረጡኝም። እኔም ሁለቱንም አገኘኋቸው። ሁለቱም ያለልዩነት ይሁንታቸውን ሰጡኝ። ከታች ይቀጥላል…