Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 412.24K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-19 16:54:46 "ርዕሰ አንቀጽ"

"…ዐማራ ማሸነፉን 100% አረጋግጧል። መጪው ጊዜም ዐማራ የሚመራት ኢትዮጵያ መወለዷ እውን ሆኗል። ይሄን ተቃራኒ ወገኖችም፣ የሩቅም የቅርብም ታዛቢዎች በሚገባ ተረድተዋል። ህወሓትም ብልፅግናም አምነዋል። ነገር ግን ዐማሮቹ እየተጨቃጨቁ ያሉት እዚህ ላይ ለመግለጽ በምቸገርበት አስቂኝ ቀላል ጉዳይ ላይ ነው። ትግሉ ነገር ዓለሙን ጣጣውን ጨርሷል። አሁን በማይረባ አጀንዳ ላይ ተቸንክረው እንዲቀሩ አኞ ሥጋ ወርውረውላቸው ከእርሱ ጋር ሲታገሉ እንዲውሉ አድርገዋቸው ነው እንጂ ዐማራው ተራራው 99. 99999% የቤት ሥራ ጣጣውን ጨርሷል። የቀረችዋ ነጥብም ቀላል አይደለችም። የምትናቅም አይደለችም። ከራስ ደጀን ተራራ፣ ከዝቋላና ከኪሊማንጃሮ ተራራ፣ ከሂማሊያ ተራሮች የገዘፈ፣ የረዘመ መስሎ የሚታይ የሚመስል ሽርፍራፊ ነጥብ ነው የቀረው። ነገር ግን ጫን አድርጎ የሚይዝ ገለልተኛ ሽማግሌ ፈጥርቆ ቢይዘው የሚበን፣ የሚተን ተራራ ነው ነጥቡ። የጥጥ ከረሜላ በሉት፣ ሲያዩት ግዙፍ ሲቀርቡት ጥጥ። ደፋር ከተገኘ ይፈታል። ደግሞም ይፈታል። እየፈታነውም ነው።

"…ወያኔ የዐማራውን አቅም አይታዋለች። ገምግማዋለችም። ወያኔ ከነገሩ፣ ከአጀንዳው ወጥታ ትግሬዎች ከዐማራ ጋር ከተጠቃቀሱ፣ በመሬት ጉዳይ ማለቃቀስ አቁመው ከተጣመሩ የብልፅግና ጉዳይ አፈር ከደቼ ነበር የሚበላው። ዐማራው ያለ ትግሬ እገዛና ያለማንም እርዳታ ሥርዓተ መንግሥቱን ከወንበዴ አራጁ ለመቀበል ከጫፍ ደርሷል። ለትግሬ መዳኛ መድኅኑ ወንድሙ ዐማራው ብቻ ነበር። ከፈለገ ከነቃ ብቻ። አዲስ አበባ የተጎለተው ብልጽግና የቀብር ስፍራውን ማሳመር ብቻ ነው የተያያዘው። ገላን ከተማ ላይ የብር ማተሚያ ፋብሪካ ከፍቶ እንደ ጉድ የሚያትመው ብር የሚያድነው መስሎታል። ፋብሪካውን እለጥፍላችኋለሁ። ይህ ሲባል ሸገር ሲቲ ጫፍ ያሰፈሩት ኦነግ አይረብሽም ማለት አይደለም። አለሁ አለሁ ለማለት ሜካፕ ተቀብቶ ስብሰባ የሚያበዛው ብልፅግና እንደሚሞት ወላጆቹ የሆኑት እነአሜሪካም፣ አውሮጳ ዓረቦቹም ዐውቀዋል። ተረድተዋልም። በቀደም ጄኔቫ የተሰበሰቡትም የተዝካር የ40 እና የ80 ማውጫ፣ የሃውልትና የቀብር ሥርዓት ማስፈጸሚያ ብር ለማዋጣት ፈልገው ነው። የማደጎ ልጃቸው ምን አልባት ታክሞ ከዳነም ብለው ነው የወላጅ ነገር ሆኖባቸው ገንዘብ ለማዋጣት የደከሙት። ለሞተ፣ ለበከተ፣ ለገማ፣ ለሸተተ፣ ሰው መሳይ በሸንጎ ነው ገንዘብ ለማዋጣት መዘፍዘፋቸው ያተረፈላቸው ውርደት ነው። የሚገርመው ነገር በጄኔቫው ስብሰባ የስደት ሀገሬ ጀርመንን ጨምሮ በአካል እየረዱት፣ እያገዙት ያሉት እነ ጣልያን፣ ፈረንሳይ እና የዓረብ ሃገራት አልረዱትም። RIP ብልጽግና።

"…እነ ግንቦት 7ን ፋኖን እስከ ማጣጣል፣ አናቱ ለሁለት ይከፈልና የአንዳርጋቸውም ጽጌ ፋኖ ተከፋፍሏል ብሎ እስከመበጥረቅ ያደረሰው የዐማራ ፋኖ የሌሎችን ጣልቃ ገብነት የመከላከል አቅሙን ከ0% ወደ 99. 99999% መድረሱን ስላዩ ነው። የፈረሰውና እስክንድር የሚመራው ሕዝባዊ ግምባር ወደ ሕዝባዊ ሠራዊት ከተቀየረ በኋላም ከእስክንድር ኋላ ያሉ ሰዎች በእስክንድር በኩል እጃቸውን አስረዝመው በዐማራ ፋኖ ውስጥ ለመዳከር መራወጣቸው አልቀረም። እሱም ቢሆን ይሄ መራወጥ አሁን የዐማራው ፋኖ መንቃት ከ0% ወደ 99. 99999% ማደጉ ፉርሽ እያደረገው መጥቷል። ግንባር በለው ሠራዊት በለው፣ ወያኔ በለው አደጋ የመሆን መጠናቸው ቀንሷል። ማዶና ማዶ ሆነው በስደት በጋዜጠኝነት ስም የጋዜጠኝነት ካባ ለብሰው ለዐማራ ፋኖ የመታገያ ማኒፌስቶ የሚያዘጋጁ ፌስታል ፊቶችም በጊዜ ተገፍተው ጥጋቸውን እየያዙ ነው። እነሱ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር ቢኖር ድሮ በደኅና ጊዜ በድብቅ የቀረጹትን የስልክ ውይይት ለማፍረሻነት መጠቀም ብቻ ነው። ልክ የጎጃሙን ማርሸት የእስክንድር ነጋዋ ገንዘብ ያዥ ወሮ ሕይወት በጄኖሳይድ ጉዳይ ቀርጻው አሁን እንደበተኑት ማለት ነው። ወዳጄ በግለሰቦች የግል የስልክ ሀሜት ምክንያት የሚቆም የዐማራ ትግል ግን የለም። አበደን የለም።

"…ሌላው ሞጣ ቀራንዮ እንዳለው የብአዴንም አልሞት ባይ ተጋዳይነት እንቅፋት መፍጠሩ አልቀረም። አሁን ባለው መረጃ አንደኛው ብአዴን በራያ በኩል ከትግሬዎቹ ጋር ተጠቃቅሶ አስቸጋሪ ናቸው የተባሉትን የብልጽግና ሰዎች ማጽዳታቸው፣ የፋኖም ኃይል በዐማራ አድማ ብተናና በዐማራ ሚልሻ እንዲጠናከር ማድረግ ሲታይ የሆነ ነገር መሽተቱ አይቀርም። ብአዴን ሙሉ በሙሉ አደረጃጀቱን ይዞ እኔ ካልመራሁት የሚለውን ዲስኩሩን ይዞ የነበረው ነገር ነው ሞጣ ፋኖ አዲስ አበባ አይገባትም ሲያስብለው የኖረው። በተለይ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቡድን በኩል ከኤርትራ ጋር ባለው ግኑኝነት በሚያቀርበው ሎጀስቲክ የዐማራ ፋኖን ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው መፍጨርጨርም 99. 99999% እየሞተ ስለሆነ አሁን ፋኖን ለመከፋፈል አቅም የለውም። RIP ገዱ።

"…ብዙዎቻችሁ የምትንቁት በሳቅ በፈገግታም ነውር ቃሉን እየጠጣችሁ የምታልፉት ሞጣ ቀራንዮ ወይም ወንድሙ የጎጃም ብአዴን የብልጽግና ሰው የሆነው ሂውስተን ቴክሳስ የሚኖረው አቶ ማማሩ መንግስቴ አንለይም የዋዛ ሰው አይምሰላችሁ። ሞጣ ቀራንዮ "ፋኖ አዲስ አበባ አይገባም። ፋኖ አዲስ አበባ እንዳይገባ ያደረግነው እኛ ነን። የሚኒልክ ቤተ መንግሥት እንገባለን ብላችሁ አልነበር? ታዲያ ከምን አትገቡም? ፋኖ አዲስ አበባ እንዲገባም፣ እንዳይገባም የምናደርገው እኛ ነን ብሎ የሚበጠረቀው እንዲሁ ዝም ብሎ ፋራ ስለሆነ የሚመስለው የትየለሌ ሰው ነው ያለው። ሞጣ እውነቱን ነው። ሞጣን የያዙት የወሎ ብአዴኖች እነ ደመቀ መኮንን እና እነ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው። ለዚህ ነው ሞጣ ገዱንና ደመቀን የሚያሞካሸው። ሞጣ በከፈሉት ገንዘብ ልክ ነው የነገሩትን ይዞ የሚበጠረቀው። ብአዴንም በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ፋኖን ይዘናታል ብለው ነበር የሚያምኑት። ደግሞም እውነት ነበር። አሁንም የብአዴን እጁ በፋኖ ውስጥ ጠፍቷል ማለት አይደለም። የብአዴን እጁ ረጅም ነው። ይሄንንም በራያ እና በወልቃይት በኩል ስላለው ሁኔታ መረጃው የለኝም እንጂ አምላከ ዐማራ ወኢትዮጵያ ልዑል እግዚአብሔር ረድቶኝ በሸዋና በጎንደር 99. 99999% የብአዴንን ሴል አፍርሰን ጨርሰነዋል። አንገቱ ላይ የቆምንበት አለ። የሚያጣጥር አለ። ለፋኖ የገበረ እጁን የሰጠም አለ። ብአዴን በሸዋ እና በጎንደር ያለውን እጁን ቆርጠነዋል። ጎምደነዋል። እስትንፋሱ ደግሞ በቅርቡ ያቆማል።

"…የጎንደር ፋኖዎች በሰው ኃይል፣ በፖለቲካ ንቃተ ህሊና፣ በሎጀስቲክ፣ በኔትወርክ፣ በጀግንነት፣ በመግባባት፣ በመደማመጥ ቀድሞ በመንቃት ከሌሎቹ የተሻለ ልምድ ያላቸው ናቸው። ከኋላ የመጣው ጎጃም እና ወሎም ጀግንነቱ ተነግሮ፣ ተዘርዝሮም አያልቅም። ሸዋ ወያኔ በልታ ጨርሳው። ብአዴን ሽባ አድርጎት ቢኖርም በዚህ 4 ዓመት እንደ እንቦሳ ጥጃ ነው እንደ አዲስ ተወልዶ የወይፈን ጉልበት ይዞ ጋራ ሸንተረሩን የሞላው። ጎንደሮች ምን ቀድመው ቢደረጁ ለሁለት መከፈላቸው አልቀረም። አንደኛው ቡድን ፋፍዴን፣ ብአዴን ወዘተረፈ፣ ሌላኛውን ቡድን ግምባሩ፣ ሠራዊቱ የሚባሉት ቀርበው አንቀው ይዘዋቸው ነበር። ሌሎቹን ቀፍዳጆች እዚህ ላይ አላነሣም። የሆነው ሆኖ በሸዋ በእነ ጋሽ አሰግድ እና ሻለቃ መከታው መካከል የነበረውን ጠብ ለዝቦ፣ አርቀነውም ወደ አንድነት ለማምጣት የነበረኝን የሽምግልና ውጤት የሰሙት ጎንደሮች ሁለቱም ቡድኖች አሜሪካና ጎንደር ባሉ ወኪሎቻቸው በኩል ቀረቡኝ። መረጡኝም። እኔም ሁለቱንም አገኘኋቸው። ሁለቱም ያለልዩነት ይሁንታቸውን ሰጡኝ። ከታች ይቀጥላል…
76.4K viewsedited  13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 15:56:07
ማስታወሻ…

"…ይቅርታ ይሄ ከርዕሰ አንቀጼ ጋር የሚያያዝ ስለሆነ እያደመጣችሁት ጠብቁኝ። ልጁ ሞኝ መስሏችሁ ንቃችሁት የምትስቁ፣ የምታጣጥሉት ሰዎች እረፉ። ልጁን የሚጋልበው እና እንዲህ እንዲናገር የቀጠረውን ነው ያደቀቅነው። ያኮሰመንነው። ሞጣ ለምንድነው እንዲህ በል ተብሎ የሚለው። መልሱን የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ላይ ታገኙታላችሁ።

"…የማይሞቀኝ እኔ ዘመዴን፣ በመስደብ፣ በማዋረድ፣ በማበሻቀጥ ፀጥ የሚያሰኙኝ መስሏቸው የዳከሩት በሙሉ አፈር ከደቼ አስግጠናቸዋል። ሞኝ መሳይ የገደል ማሚቶ በበቀቀናቸው ነገ አረሳስተው ቢመጡም ሞጣንና ላኪዎቹንም ከቲክቶክ መንደር ጫማ ሰቅለው ለጊዜው እንዲያርፉ አድርገናቸዋል።

• 99. 99999% ያለቀው የዐማራ ፋኖ አንድነት ከምን እንደደረሰ ልለጥፍላችሁ ነኝ። ዋግም፣ ጠንቋዩ፣ አስማተኛው፣ ባለ ቆሌው ሁሉ ቆሌውን ገፈናዋል። ዐማራ አይሸነፍም። ኢትዮጵያን የሚያሳርፋት ዐማራ ብቻ ነው። አራት ነጥም።

"…ተመልሼ እመጣለሁ። እያደመጣችሁኝ ጠብቁኝ። በዚህ ጦማር ላይ ነገርየውን ከመመርመር በቀር ሞጣን አናንቆ የሚሳደብ ሰው ካየሁ እቀስፈዋለሁ። ሰምተሃል።

• እመለሳለሁ…!
77.5K viewsedited  12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 15:23:31
መልካም…

"…የአመስጋኙ ቁጥር የሚፈለገውን 1ሺ የአመስጋኞች ቁጥር ስለሞላ አሁን የምስጋናው ክፍለ ጊዜ ተጠናቅቋል። ከምስጋናው ቀጥሎ የምንሄደው ያው እንደተለመደው በሁሉ ዘንድ ወደሚናፈቀው የ"ርዕሰ አንቀጽ" መርሀ ግብራችን ነው የምናመራው።

"…በዛሬው የርዕሰ አንቀጽ መርሀ ግብራችን እኔ እንድመራው በፍጥነትም እንድጨርሰው በሁሉም ወገን ሓላፊነት ተጭኖብኝ ተገድጄ የገባሁበትና 99. 99999% "የጎንደሩና የሸዋ ፋኖ አንድነት የሽምግልና ጉዳይ" ከምን እንደደረሰ ላሳውቃችሁ ወደድሁ። ፈለግሁም። ደግሞም አማረኝም። የሁላችሁም ጭንቀት ስለሚገባኝ፣ ስለምረዳውም ጥቂት ባካፍላችሁ እና ባስተነፍሳችሁስ ብዬም ወሰንኩ?

"…የቀረችኝን ፐርሰንት በማወቅም ባለማወቅም፣ በስንፍናም፣ በሴራም ይሁን በሥራ፣ በዳተኝነትም የሁን በዳታ ማስቸገር የዘገዩብኝን እናንተው ደውላችሁ ጫና በመፍጠር ታግዙኝ እንደሁ ብዬ ነው ወደ እናንተ መምጣቴ። በጣም፣ ቀላል፣ የማይረባ ነገር ነው የቀረው። የከበደው ነገር አልቋል። ተጠናቅቋል። በይቅርታም ታልፏል። ተማምለዋል። ይቅርም ተባብለዋል።

• እህሳ ለመስማት ብቻ ሳይሆን እኔን ለማገዝ ዝግጁ ናችሁ…?
78.4K views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 12:25:01
“…በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤” 2ኛ ጢሞ 2፥20

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
83.8K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 21:49:35
"…ተወዳጆች ሆይ…!

"…እነሆ ትእግስትን በአካል ተዋወቋት… ትእግስት፣ መልኳ፣ ቁመናዋ፣ አቋሟ ምን ይመስላል ቢሉ ይኸው ይሄንን የምታዩትን ባለማዕተብ ልጅ ነው የምትመስለው። ቁርጥ እሱን።

"…አከበርኩት ልጁን፣ ባለ ማዕተቡን። እጁን ቢሰነዝር፣ ሰውየው ሽማግሌው ቢጎዳም፣ ባይጎዳም ፖሊስ ቢመጣ፣ የአንገቱ ማዕተብ ብቻ ልጁን ያስቀጠቅጠው ከዚያም አልፎ ያስገድለው ነበር። በዚያ ላይ ሼኪው…
92.3K viewsedited  18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 20:45:00
ሓሳብ ስጡበት እስቲ…!

"…ሰውየው የጎጃም ዐማራ ናቸው። ቀን ጥሏቸው ቢርባቸው እንጀራ ፍለጋ እግራቸው ወዳመራቸው ሄዱ። ኦሮሚያ ደረሱ። እናም ኦሮሞዎቹ በዚህ መልክ እያስተናገዷቸው ነው።

"…ሰውየው የተራቡ፣ የደኸዩ፣ የተቸገሩ፣ ያጡ፣ የነጡ መሆናቸውን ለኦሮሞዎቹ በተማጽኖ እየነገሯቸው ነው። በማርያም በእግዚአብሔር እያሉም እየተማጸኑአቸው ነው። ኦሮሞዎቹ ግን  ለምን ክልላችን ኦሮሚያ መጣህ እያሉ በጥፊ፣ በዱላ፣ በእርግጫ፣ በጡጫ እየወገሯቸው ነው። ኦሮሞ እኮ አቃፊ ነው ይልሃል ቆይቶ…

"…የተሰበከው ጥላቻ ፍሬ አፍርቷል። አሁን ከፖለቲከኞቹ መንደር አይደለም ጥላቻው። በዘፈን፣ በቀረርቶ፣ በሽለላ የዐማራን ጥላቻ እየጋቱ ያሳደጉት ትውልድ አሁን የጥላቻ ስብከቱን ትርክት ፍሬ ማፈስ ጀምሯል። እንደ ሕዝብ በጥላቻ ማበዱን ከዚህ በላይ ማሳያ የለም። የዐማራ ጥላቻው የጾታ እና የእድሜ ገደብ የለውም። ሽማግሌው በከዘራ፣ ታዳጊዎቹ በጥፊ ነው ዐማራ ነው የተባለ የሚደበድቡት። ኅዘኔታ፣ ርህራሄ የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም። ደግነቱ ኦሮሞ ጣጣ የለውም። ይሄንን ግማታም፣ የከረፋ ዘግናኝ ወንጀሉን በገዛ ስልኩ ቀርጾ በቲክቶክ ይበትነዋል። ከኦሮሚያ ወደ የመን ለመሰደድ ሱማሌላንድ ላይ የተያዙ ኦሮሞዎች ዛሬ የዜና መነጋገሪያ ነበር። ስደት ክፉ ነው። ስደተኛ፣ ራብ ያጠቃው ሰው መደብደብ፣ ማዋረድ ወንጀልም፣ ግፍም፣ ኃጢአትም ነው። ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ።

"…ዐማራ የምትታገለው ከዚህ ብሔራዊ ውርደት ለመገላገል፣ ለመውጣት መሆኑን እመን። የማንም ጨቅላ የሚያነውርህ፣ የሚያሸማቅቅህ እንዳትሆን፣ ለልጆቻችሁም ጭምር ይሄንን ውርደት እያሳያችሁ ልጆቻችሁ አምርረው ለነፃነታቸው እንዲታገሉ አድርጉ። ኦሮሞዎቹ ግን ክፉ ዘር ነው የተዘራባቸው።

• ከምር አሁን ይህስ ምን ይባላል…?
92.0K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 17:44:39
መረጃ ናሁሰናይ…!

"…የአርበኛ ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይን በተመለከተ የኦሮሙማው የብልጽግናው አገዛዝ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሠርቶ በዩቲዩብ የጫናውን ዜና አንሥቶታል።

"…በሌላ ዜና የኦሮሞው ብልጽግና ገድየዋለሁ ብሎ በይፋ ያወጀውን የሟቹን አስከሬና እስከዛሬ ድረስ ለቤተሰቡም አልሰጥም ማለቱም ተነግሯል። አስከሬን አንሰጥም ጥፉ ከዚህ ብሎ ቤተሰብ እንደሚያባርር ነው የሚነገረው።

"…ማረጋገጫ ባይኖረኝም፣ የደረሰኝ መረጃም ባይኖርም ናሁሰናይን በተመለከተ አንዳንድ ሰዎች እንዳልሞተና በቅዱስ ጳውሎስ የጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ በጥብቅ የመንግሥት ፖሊሶች ክትትል ህክምና እየተሰጠው ነው የሚሉ አሉ። አሉ ነው እንጂ ያረጋገጠልኝ ሰው ግን የለም።

"…የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የሠራውን ዜና ከዩቱዩብ ማውረዱ ከዚህ በሕይወት ከመኖር ዜና ጋር ይያያዝ አይያያዝ ግን የማውቀው ነገር የለም። አስከሬኑን ለቤተሰብ አንሰጥም ያሉበትም ምክንያት ከዚሁ ልጁ በሕይወት ከመኖሩ ጋር የተያያዘ ይሆን? እንጠይቃለን።

"…ምንአልባት መረጃ እናገኝበት እንደሁ ብለው በሕይወት አትርፈው ከዳኑት በኋላ ቁስሉን እየነካኩ በመመርመር ኋላላይ ሊገድሉት አቅደው አስቀድመው ሞቱን ያወጁት ለዚያ ነው የሚሉም አሉ።

• ለማንኛውም EBC ያወረደውን ቪድዮ ለታሪክ አስቀምጡት። ያዙት።
39.7K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 14:10:39
መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጻችን አጠር ያለች ስለሆነች ወደ ውይይቱ መግባት እንችላለን። ቅዳሴ የማይቀድስ ሶዬ እንዲ ሚልዮን በሚልዮን ዶላር ተጥለቅልቆ ስታዩ አይገርምላችሁም?

"…በኦሮሞ ስም የሚዘርፉት ባለ ጊዜዎች ከዚህ በፊት በትግሬ ስም ሲዘርፉ እንደከረሙት ዘራፊዎች ጊዜ፣ ዘመን ፊቱን አዙሮ እንደፈረደባቸው ሰዎች አበላሉን፣ አሰራረቁን፣ አዘራረፉን ያወቁበት አይመስለንም። የኦሬክስ ወኪል ነን የሚሉት ሌቦች እንደ ትጌክሶቹ ወኪል ነን እንደሚሉት አዘራረፉ ወዝ የለውም። መጣም፣ መጣም ፍጥጥ ግግም ግጥጥ ያለ አዘራረፍ ነው የሚሉ መተርጉማንም አሉ።

"…አሁን ጥያቄው ቀውሲ በላይ ኦሮሞነቱ የቡዳ መድኃኒት ሆኖት ከዘብጥያ ይለቁታል ወይስ… እንትን ያደርጉትና … ምን ማለት ፈልጌ ነበረ ጠፋብኝ። …ብቻ እናንተ ግምታችሁን አስፍሩ፣ ሓሳብ አስተያየታችሁንም በጨዋ ደንብ ግለጹና ወደ ቀጣዩ መርሀ ግብራችን እናመራለን።

• ተንፒሱ…!
57.7K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 13:48:56
"ርዕሰ አንቀጽ”

ቀወሲ በላይ Vs ቅድስት ሥላሴ

"…ኦሮሞነቱ ጊዜ የሰጠው፣ የጃዋር፣ የአቢይ አሕመድ፣ የአዳነች አበቤ፣ የሽመልስ አብዲሳ የጡት አባት፣ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት መሥራች፣ የፈይሳ አዱኛ ታቦት ቀራጭ፣ የኮሬ ነጌኛው አባል፣ የኦህዴድ የፓርላማ ተመራጭ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድቤት ዳኛ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀውሲ በላይ መኮንን 6 ሚልዮን 50 ሺ ዶላር በውጭ ሀገር ወደሚገኘው ባንክ ዶላር ሲያዘዋውር ቁጥጥር ስር መዋሉን ቀደም ሲል ዘግቤ ነበር። ዘገባዬን ፋና ዛሬ አረጋግጦልኛል። ክብር ለወፎቼ።

"…በሌላ ዜና ጥንታዊው እና 4ኪሎ የሚገኘው የአጋእዝተዓለም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለእድሳት ከሚፈልገው 172 ሚልዮን ብር,90 ሚልዮን ብር ብቻ አግኝቶ ቀሪ 82 ሚልዮን የኢትዮጵያ ብር የሚሰጥ ሰው ስለጠፋ የእድሳት ጊዜው መራዘሙን በይፋ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

"…ለበላይ መኮንን ኦሮሞነቱ ያድነዋል። አቢይ አህመድ ይደርስለታል ተብሎ ይጠረጠራል። በላይ ሲያዝ "ቆይ አንድጊዜ አቢይ ጋር ልደውል" ያለውም እኮ የሚያውቀው፣ የሚተማመንበት ነገርም ስላለው ነው። ዳኞቹም፣ ፎሊሶቹም፣ ዐቃቤ ሕጎቹም በአንዲት ስልክ ከጥፍራቸው ውስጥ ማስደበቅ ይችላል። የውጭ ምንዛሬ ሃራራ ያለበት አገዛዙ ለመውረስ ካልፈለገ በቀር፣ ገንዘቡም የየማይፈለጉ ባለሥልጣናት ወይም ድርጅቶች ካልሆነ በቀር፣ አልያም ኦሬክሶችን አስከፍቷቸው ሊበቀሉት ካልፈለጉ በቀር ሰሞኑን ሊፈቱት ይችላሉ።

"…ለቅድስት ሥላሴ ግን ከእኛው ውጪ ማን ይድረስ?…“…በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?” ሐጌ 1፥4

• ይሄ ይሄ እየታየ ሰዉ ግን ሙዳየ ምጸዋት አልሰጥም ቢል ይፈረድበታልን?

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
57.2K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 13:19:52
መልካም…

"…እንደተለመደው ከምሥጋና ቀጥሎ ርዕሰ አንቀጽ ልጽፍ ነኝ። አንብባችሁስ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ? …የምጠይቃችሁ ይሁነኝ ብዬ ነው። መንደሩን ድብልቅልቅ ስታደርጉት የጠላት መንጋ ሰራዊት እንዴት እንደሚሸበር ስለማታውቁ ነው።

• ዝግጁ…?
55.8K viewsedited  10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ