Get Mystery Box with random crypto!

መልካም… '…የአመስጋኙ ቁጥር የሚፈለገውን 1ሺ የአመስጋኞች ቁጥር ስለሞላ አሁን የምስጋናው ክፍ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የአመስጋኙ ቁጥር የሚፈለገውን 1ሺ የአመስጋኞች ቁጥር ስለሞላ አሁን የምስጋናው ክፍለ ጊዜ ተጠናቅቋል። ከምስጋናው ቀጥሎ የምንሄደው ያው እንደተለመደው በሁሉ ዘንድ ወደሚናፈቀው የ"ርዕሰ አንቀጽ" መርሀ ግብራችን ነው የምናመራው።

"…በዛሬው የርዕሰ አንቀጽ መርሀ ግብራችን እኔ እንድመራው በፍጥነትም እንድጨርሰው በሁሉም ወገን ሓላፊነት ተጭኖብኝ ተገድጄ የገባሁበትና 99. 99999% "የጎንደሩና የሸዋ ፋኖ አንድነት የሽምግልና ጉዳይ" ከምን እንደደረሰ ላሳውቃችሁ ወደድሁ። ፈለግሁም። ደግሞም አማረኝም። የሁላችሁም ጭንቀት ስለሚገባኝ፣ ስለምረዳውም ጥቂት ባካፍላችሁ እና ባስተነፍሳችሁስ ብዬም ወሰንኩ?

"…የቀረችኝን ፐርሰንት በማወቅም ባለማወቅም፣ በስንፍናም፣ በሴራም ይሁን በሥራ፣ በዳተኝነትም የሁን በዳታ ማስቸገር የዘገዩብኝን እናንተው ደውላችሁ ጫና በመፍጠር ታግዙኝ እንደሁ ብዬ ነው ወደ እናንተ መምጣቴ። በጣም፣ ቀላል፣ የማይረባ ነገር ነው የቀረው። የከበደው ነገር አልቋል። ተጠናቅቋል። በይቅርታም ታልፏል። ተማምለዋል። ይቅርም ተባብለዋል።

• እህሳ ለመስማት ብቻ ሳይሆን እኔን ለማገዝ ዝግጁ ናችሁ…?