Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ ናሁሰናይ…! '…የአርበኛ ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይን በተመለከተ የኦሮሙማው የብልጽግናው አገዛዝ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መረጃ ናሁሰናይ…!

"…የአርበኛ ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይን በተመለከተ የኦሮሙማው የብልጽግናው አገዛዝ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሠርቶ በዩቲዩብ የጫናውን ዜና አንሥቶታል።

"…በሌላ ዜና የኦሮሞው ብልጽግና ገድየዋለሁ ብሎ በይፋ ያወጀውን የሟቹን አስከሬና እስከዛሬ ድረስ ለቤተሰቡም አልሰጥም ማለቱም ተነግሯል። አስከሬን አንሰጥም ጥፉ ከዚህ ብሎ ቤተሰብ እንደሚያባርር ነው የሚነገረው።

"…ማረጋገጫ ባይኖረኝም፣ የደረሰኝ መረጃም ባይኖርም ናሁሰናይን በተመለከተ አንዳንድ ሰዎች እንዳልሞተና በቅዱስ ጳውሎስ የጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ በጥብቅ የመንግሥት ፖሊሶች ክትትል ህክምና እየተሰጠው ነው የሚሉ አሉ። አሉ ነው እንጂ ያረጋገጠልኝ ሰው ግን የለም።

"…የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የሠራውን ዜና ከዩቱዩብ ማውረዱ ከዚህ በሕይወት ከመኖር ዜና ጋር ይያያዝ አይያያዝ ግን የማውቀው ነገር የለም። አስከሬኑን ለቤተሰብ አንሰጥም ያሉበትም ምክንያት ከዚሁ ልጁ በሕይወት ከመኖሩ ጋር የተያያዘ ይሆን? እንጠይቃለን።

"…ምንአልባት መረጃ እናገኝበት እንደሁ ብለው በሕይወት አትርፈው ከዳኑት በኋላ ቁስሉን እየነካኩ በመመርመር ኋላላይ ሊገድሉት አቅደው አስቀድመው ሞቱን ያወጁት ለዚያ ነው የሚሉም አሉ።

• ለማንኛውም EBC ያወረደውን ቪድዮ ለታሪክ አስቀምጡት። ያዙት።