Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ” ቀወሲ በላይ Vs ቅድስት ሥላሴ '…ኦሮሞነቱ ጊዜ የሰጠው፣ የጃዋር፣ የአቢይ አ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ”

ቀወሲ በላይ Vs ቅድስት ሥላሴ

"…ኦሮሞነቱ ጊዜ የሰጠው፣ የጃዋር፣ የአቢይ አሕመድ፣ የአዳነች አበቤ፣ የሽመልስ አብዲሳ የጡት አባት፣ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት መሥራች፣ የፈይሳ አዱኛ ታቦት ቀራጭ፣ የኮሬ ነጌኛው አባል፣ የኦህዴድ የፓርላማ ተመራጭ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድቤት ዳኛ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀውሲ በላይ መኮንን 6 ሚልዮን 50 ሺ ዶላር በውጭ ሀገር ወደሚገኘው ባንክ ዶላር ሲያዘዋውር ቁጥጥር ስር መዋሉን ቀደም ሲል ዘግቤ ነበር። ዘገባዬን ፋና ዛሬ አረጋግጦልኛል። ክብር ለወፎቼ።

"…በሌላ ዜና ጥንታዊው እና 4ኪሎ የሚገኘው የአጋእዝተዓለም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለእድሳት ከሚፈልገው 172 ሚልዮን ብር,90 ሚልዮን ብር ብቻ አግኝቶ ቀሪ 82 ሚልዮን የኢትዮጵያ ብር የሚሰጥ ሰው ስለጠፋ የእድሳት ጊዜው መራዘሙን በይፋ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

"…ለበላይ መኮንን ኦሮሞነቱ ያድነዋል። አቢይ አህመድ ይደርስለታል ተብሎ ይጠረጠራል። በላይ ሲያዝ "ቆይ አንድጊዜ አቢይ ጋር ልደውል" ያለውም እኮ የሚያውቀው፣ የሚተማመንበት ነገርም ስላለው ነው። ዳኞቹም፣ ፎሊሶቹም፣ ዐቃቤ ሕጎቹም በአንዲት ስልክ ከጥፍራቸው ውስጥ ማስደበቅ ይችላል። የውጭ ምንዛሬ ሃራራ ያለበት አገዛዙ ለመውረስ ካልፈለገ በቀር፣ ገንዘቡም የየማይፈለጉ ባለሥልጣናት ወይም ድርጅቶች ካልሆነ በቀር፣ አልያም ኦሬክሶችን አስከፍቷቸው ሊበቀሉት ካልፈለጉ በቀር ሰሞኑን ሊፈቱት ይችላሉ።

"…ለቅድስት ሥላሴ ግን ከእኛው ውጪ ማን ይድረስ?…“…በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?” ሐጌ 1፥4

• ይሄ ይሄ እየታየ ሰዉ ግን ሙዳየ ምጸዋት አልሰጥም ቢል ይፈረድበታልን?

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።