Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 403.82K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 251

2022-10-11 22:49:57
"…ይድረስ ዘመዴ በማለት ከወንድምህ ዘመነ ካሴ ከባህርዳር ማረሚያ ቤት ብሎ አርበኛ ዘመነ ካሴ የጻፈልኝ ደብዳቤ ደርሶኛል። የዛሬ ገጠመኙን እና የፍርድ ቤት ውሎውን ጨምሮ ነው የጻፈልኝ። "ዘመዴ እውነታውን እና እየሆነ ያለውን በአንተ በኩል ለህዝብ አሰሳውቅልኝ በማለት የጻፈልኝን ደብዳቤ ጠዋት ላይ እለጥፍላችኋለሁ።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ

"…ደኅና እደሩልኝ…!!
15.5K viewsedited  19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 18:03:37
በደብረ ታቦር እና በደብረ ማርቆስ የኒቨርሲቲዎች የተፈጠረው ምንድነው?

http://t.me/ZemedkunBekeleZ
57.1K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 18:03:00 በደብረ ታቦር የሆነው እንዲህ ነው።

"…በደቡብ ጎንደር በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትናንት ለፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ፈተናው በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይም በኦሮሚያ ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል መባልን እንደሰሙና እንደራጋገጡም በመናገር አንዳንድ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይጀምራሉ። በዚህ የተነሣ ጥያቄውን አጥብቀው ይጠይቁ የነበሩ ተማሪዎችን ፖሊስ ወደ ዘብጥያ ማውረዱ ይነገራል። ይሄ በዚህ አለፈ።

"…መሸ… ነጋ… ሁለተኛም ቀን ሆነ። ዛሬ ማለት ነው። ጠዋት ላይ ተማሪዎች ትናንት የታሠሩት ተማሪዎች እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀርባሉ። በዚህም መካከል ፈተናው ሳይጀመር በ https://t.me/Qeeroo12 በሚባለው ቴሌግራም ቻናል ላይ እንደተለመደው የጂኦግራፊና የአቲትዩድ ፈተናዎች ናቸው የተባሉ መረጃዎች መለቀቅ ይጀምራሉ። ከውጭ ያለው ህዝብም ፈተናው መሰረቁን በጩኸት መናገር ጀመረ። ተማሪዎች ፈተና ሳይጀምሩ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናው ከመጀመሩም በላይ የቄሮ ሚዲያ ፈተናውን እያሰጣ መሆኑን በመስማት መረጋጋት ጠፋ። ተሜ ተበሳጨ። ተቃወመም።

"…ቆይቶም የጸጥታ ኃይል ወደ ዩኒቨርሲቲው ገባ። ድሮም ለዐማራ ትእግስት የሌለው የፀጥታ ኃይል እንደገባ ተማሪዎቹን መቀጥቀጥ ጀመረ። እጅና ጭንቅላቱን አፈረሱት፣ ቀጠቀጡት። ልክ እንደ ፖሊሱ እንዲደድብና እናዳያስተውል ወገሩት። በዱላ ብቻ አልቆመም ወደ ጥይት ተኩስ ተገባ። ብዙ ተማሪዎችም ወደቁ። ግርግሩ ጦዘ፣ ጦፈም። ከተኩሱ ለማምለጥ በተገኘው አቅጣጫ ሁሉ ተማሪው ሮጠ።

"…አሁን 4 እና 9 በሚል ያልተረጋገጠ ቁጥር ያለው የሞት ወሬ ተማሪዎች መሞታቸው እየተነገረ ነው። የቆሰሉም እንደዚያው። ተማሪዎች አሁን ከፈተና ጣቢያው ወጥተዋል። መነሃሪያው በተማሪዎች ተሞልቷል። መኪና ግን የለም። ትርፍ የጫኑ መኪኖችን ፖሊሶች እያስወረዱ ነው። ህዝቡ ጥቂት ተማሪዎችን ሊያስተናግድ፣ ሊያበላ እና ሊያጠጣ ብቻ ነው የሚችለው። ተማሪው ግን ብዙ ነው። በቀጣይ ምን እንደሚሆን አይታወቅም።

"…በተመሳሳይ ወሬ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ ውዝግብ ተነሥቶ ተማሪዎች ከፈተና ጣቢያው መውጣት ጀምረው የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ ግን በሽማግሌዎች ጣልቃ ገብነት ወደ ፈተና ጣቢያው መመለሳቸው ተነግሯል። ከደብረ ማርቆስ መረጃውን ያቀበለኝ ታማኙ የመረጃ ምንጬ አንዷን ተማሪ ያነጋገራት ሲሆን ተማሪዋም "የሌሎችን አላውቅም እኔ ግን ተማሪዎች ሲወጡ የወጣሁት እጅግ በጣም ስለከበደኝ ነው የወጣሁት" እንዳለችው ነው የነገረኝ። እናም አንዳንድ ፈተናው የከበዳቸው ሰነፍ ተማሪዎች በዚህ ግርግር ተጠቅመው እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አካሄድ ሊሄዱ እንደሚችሉና በቋፍ ላይ ያለን ተማሪ ተረጋግቶ እንዳይፈተን ሊያደርጉት እንደሚችሉ ይጠረጠራል። ሰነፎች እረፉ።

"…ትናንት ፈተናው እስኪያልቅ ድረስ ኢንተርኔት ተዘግቶ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግን ፍርዬ ቢያንስ ቴሌግራምን እንኳ ባለመዝጋቷ ትንሽ ውዝግብ መፈጠሩን አይቻለሁ። በተረፈ እንዲያም እንዲህም ተብሎ በሰላም ይለቅ። ከሞት ከግድያ ያድናችሁ። ይሰውራችሁ። ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ። ተማሪዎች ተረጋግታችሁ ተፈተኑ። እናንተ እንድትረበሹና ተረጋግታችሁ እንድትፈተኑ የሚፈልግ ኃይል እንዳለም ዕወቁ። እየቆየ የሚሆነውን ብናይም ዘንድሮ ግን ፈተናው እንደድሮው በጀማ የመሥራቱ ነገር በጣም የጠበበ መሆኑንም ለማረጋገጥ ችያለሁ። ስህተት ቢኖርም ስህተቱ ግን እንደ አምና ካቻምናው አይሆንም። ተረጋግታችሁ ተፈተኑ።

"…ሻሎም…!  ሰላም…!
59.1K viewsedited  15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 13:31:50 ደግሞ ጀመረሽ…?
ለእህቴ ዘማሪት ምርትነሽ።
          (ክፍል ፪)

"…ከላይ የጀመርኩትን ነው ለመቋጨት የምቀጥለው። ሌላ የሚያናግር አስገዳጅ አናጋሪ አጀንዳ ካልተገኘ በቀር በዚህ ጉዳይ ይሄ የመጨረሻዬ ነው። አልመለስበትም። ከላይ በቪድዮ በምስል የሰማችሁት "ለማርያም" የሚለው መዝሙር የዜማ ደራሲው ዘማሪ አረጋይ ነው። ዘማሪዋ ደግሞ እህቴ ዘማሪ ስንታየሁ ናት። ሲሰሙት ልብ ወከክ የሚያደርገው የዋሽንት፣ መሰንቆና ክራር ከበሮውም ጭምር ኢንትሮው በእነ ዘውዱ ጌታቸው ክራር፣ ዋሽንቱ በኤልያስ፣ እና ከበሮው አካሉ ዮሴፍ ይመስለኛል የተቀመመው። መግቢያው ራሱ ሲሰማ ልብ ይመስጣል። ይሄን የወጣትነቴን መዝሙር "እመቤታችንን" እያሰብኩ ስዘምረውም ሆነ ስሰማው ጭምር ለነፍሴ እረፍት፣ መረጋጋትን ይሰጠኛል። ጥቂት ከምሰጥባቸው መዝሙራት መካከልም አንዱ ይሄ መዝሙር ነው። ዜማውም፣ ግጥሙም ፍፁም የተዋበ የተሳካ መዝሙር ነው። ደግሞስ ልጆቹ የጎላ ቅዱስ ሚካኤል ልጆች አይደሉ? ዘማሪዋን ዘማሪት ስንታየሁን ከማኅበረ ሥላሴ ማኅበር ጀምሮ ነው የማውቃት። እህቷ እና ጓደኛዋ አብራት የምተዘምረው ሸዋዬም አሁን የት እንዳለች ባላውቅም ከአረብ ሃገር ወደ አውሮጳ ተሻግራ በዚያ ትኖር እንደነበር እሰማ ነበር። አረጋይ እዚያው ኢትዮጵያ ነው። ስንትሽ በትዳር ሆና ከዝማሬው ከራቀች ቆየች።

"…ይሄን መዝሙር ነው እንግዲህ እህታችን ምርትነሽ "ሪሚክስ" አድርጋ እንዲህ ቅጣንባሩን አጥፍታ ባንኮክ ታይላንድ ሄዶ በስፕራይት ጠርሙስ ቢራ ጨምሮ ጠጥቶ ሰክሮ እንደሚረብሽ ሰካራም ጴንጤ እና ወሃቢይ አወለጋግዳ ያቀረበችው። ይሄ በፍጹም ትክክል አይደለም። ምርትነሽ በስንት ድካም ከነበጋሻው፣ ከነዘርፌ፣ ከነትዝታው መንገድ ተለይታ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን የተመለሰች እህቴ ናት። መመለሷን በሰማሁ ጊዜም ካለሁበት ከራየን ወንዝ ማዶ ሆኜ ደውዬ ደስታዬን የገለፅኩላት እህቴም ናት። በመዝሙር ሥራ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍሬ ተዋሕዶ ብዬ በዘመነ VHS የቪሲዲ ሥራን ሟቹ ተስፋዬ ኢዶን ጨምሮ የ12 ዘማርያንን የመዝምር ሥራ " ፍሬ ተዋሕዶ" በሚል በቪድዮ ቀርጬ በመዝሙር መልክ የጀመርኩት እኔ ነኝ። ምርትነሽንም ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ቪድዮ ላይ አካትቼ ሠርቼ ህዝብ ፊት ያቀርብኳትም እኔ ዘመዴ ነኝ። ይሰመርበት…

"…አሁን ግን ይህን ግሩም መዝሙር እህቴ ምርትነሽ እንዲህ ቅጥአምባሩን አጥፍታ አበላሽታ ዘምራው አየሁ። ክራሩን፣ ዋሽንቱን፣ መሰንቆውን አጥፍታ፣ ቤዝ ጊታሩን እንደ ፒያኖ ተጠቅማ አበላሽታ፣ ለዛውን አሳጥታ ስተዘምረው አየሁኝ። መታገስም አቃተኝ። ይሄ እኮ ጌዲኦኛ አይደለም። ጉራጊኛ፣ ጎጃም ጎንደርኛ፣ ወላይትኛም አይደለም። እጅግ የተደከመበት መዝሙር ነው። ልጆቹ አምጠው የወለዱት መዝሙር ነው። የመዝሙሩን ጥንተ ተፈጥሮ ማበላሸት ለምን አስፈለገ? አማካሪዎችሽ እነ ሰለሞን አቡበከር እንደሆን ታጥበው የማይጠሩ ሽንፍላዎች ናቸው። ግማሽ ክርስቲያን እኮ መሆን ጣጣ ነው። የእነሱን ምክር ሰምተሽ ያን የምወደውን መዝሙር በማይሆን፣ እጅግ በሚያስጠላ፣ ቋቅም በሚል አቀራረብ በማቅረብሽ ነው ተቃውሞዬን በግልፅ ለማቅረብ የተገደድኩት። ስለ አዳራሽ መገኘቱ አያገባኝም።

"…መጀመሪያ ባለቤቶቹን አስፈቅደሻልን? አንቺ ከጌዲኦ ሳትወጪ፣ ከይርጋለም ሳትነሺ ነው ይሄ መዝሙር የወጣው። ምንአልባት ዘማሪ አረጋይን ልታውቂው ትቺዪ እንደሁ እንጂ እርግጠኛ ነኝ ዘማሪዎቹን ስንቴንና ሸዋዬን አታውቂያቸውም። ዝም ብሎ የሰው ልጅ በመሳም ሰበብ ንፍጥ እና ለሃጭ መለቅለቅ ይደብራል። "ጎጆዬ፣ ጓዳዬ፣ ይናዳል ተራራው፣ ይሞላል ሸለቆው ብለሽ ስትዘምሪ ስለከረምሽ" አሁን ስለ እመቤታችን መዘመር ብትፈልጊ እንኳን አዲስ መዝሙር ማውጣት ቢያቅትሽ ቀደም ብሎ የወጣውንና በግሩም ሁኔታ የተዘመረውን መዝሙር አወለጋግዶ መዘመር ደግ አይደለም። ይቀፋልም። እኔ በአንቺ አዲስ ዜማ ስሰማው ከምር ቋቅ ነው ያለኝ።

"…እናም እህቴ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ሆይ መጪው ትውልድ የቀደመውን መዝሙር እውነተኛ ቀለም ትቶ በአንቺ የቤዝ ጊታር ሙዚቃ ተመስጦ በዚያው ዶግማ አድርጎት እንዳይቀር አስወግጂልኝ። እባክሽ ይሄን መዝሙር ከተጫነበት ሁሉ አውርጂልኝ። እኔም ለማነጻጸሪያነት ያመጣሁትን ቆይቼ መላ እፈልግለታለሁ ስል በትህትና እጠይቅሻለሁ። አክባሪ ወንድምሽ ዘመድኩን በቀለ ነኝ። ከራየን ወንዝ ማዶ።

"…ይሄን እዚህ ጋር ዘጋሁ። አሁን ወደ ወለጋ፣ ራያ እና ትግራይ ልብረር።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ
67.2K viewsedited  10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 12:56:42
"…ተቃውሞዬ እዚህ መዝሙር ላይ ነው። ምርትነሽን የምቃወማት እዚህ መዝሙር ላይ ነው። ምክንያቴን ከታች በጽሑፍ ገልጬዋለሁ። ለማነጻጸር እንዲመቻችሁ ከታች ኦሪጅናሉን መዝሙር አስቀምጬላችኋለሁ።

• ምርትነሽ ወዝ አሳጣችው።
• ዜማውን ቆራረጠችው።
• እንደ ድሮ የፊሊፕስ ቴም ነካከሰችው።
~ቤዝ ጊታሩን እንደ ፔያኖ ተጠቀመችበት። ፍፁም የመናፍቃን መዝሙር አስመሰለችው። ጴንጤ ላለመባል የማርያምን መዝሙር የግድ መዘመር ካስፈለገም ኦሪጅናል ቀለሙን ሳይለቅ እንጂ የምን ማኪያቶ አስመስሎ አወላግዶ መዘመር ነው? ምርትነሽ የሚቀርጻት ሰው ነው እንጂ ያጣችው አሁንም የጴንጤን መንገድ፣ በእነ ትዝታው፣ ዘርፌ በጋሻው ጎዳና ትሄዳለች ብዬ ብዙም አላስብም። ከሰለሞን አቡበከር ጋር ገጥማ ግን፣ ከፀጋዬ ሮቶ ጋር ገጥማ ግን ጤነኛ ትሆናለች ብዬም ደግሞ አላስብም። ቫይረሱ ከባድ ነው።

ቁጥር አንዱ ምርትነሽ የዘመረችው ነው።
ሁለተኛ ኦሪጅናሉ እህቴ ዘማሪት ስንታየሁ የዘመረችው ነው።
ሦስተኛው ደግሞ ስማቸውን ያላወቅኩት ዘማርያን የዘመሩት ነው። ምርትነሽ አወላግዳ ስትዘምረው መዘምራኑ ግን ኦሪጅናሉን ዘምረውታል። እነ ሰለሞን አቡበከር ኦሪጅናሉን ማጥፋት ነው አላማቸው። ይሄንን ነው የምቃወመው።
3.4K views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 12:13:36 ዘማሪ ነው። ሁላችሁ ስለጨፈጨፋችኋት፣ ለይታችሁ ስለወገራችኋት ስለዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ግን እጽፋለሁ። ስለ ምርቴም የምጽፈው ለምን በአዳራሹ ተገኝተሽ ዘመርሽ ብዬ ሳይሆን በአዳራሹ ውስጥ ተገኝተሽ አጣመሽ፣ ሰባብረሽ የዘመርሽው መዝሙር ትክክል አይደለም ብዬ እንዳትደግመው ልማጸናት ነው። ስለራሷም መዝሙር አያገባኝም። ስትፈልግ በጉራጊኛ፣ ስትፈልግ በጎጃም በጎንደርኛ፣ ስትፈልግ በምንጃርኛ፣ ከቻለች ለምን በሬጌ ስልት አትጨፍረውም። አያገባኝም። እኔ ግን የቆየ ኦርቶዶክሳዊ የሰው መዝሙር ስትዘምሪ አስተካክለሽ ዘምሪ ብቻ ለማለት ነው የምጽፍባት እንጂ ለምን አዳራሽ ተገኘሽ ብዬ አይደለም። ከአዳራሽ ማን እንደቀረ ነው ምርትነሽ የምትቀረው? ምርቴ አይደለም አዳራሽ ለምን ስታዲዮም አትዘምርም። ማን እንደተነቀፈ፣ ማን እንደተከለከለ ነው የምነቅፋት? የእኔ የአሁኑ ተቃውም ምርቴ ላይ ብቻ ነው። ምርቴንም የምቃወመው ከላይ ጠቆም እንዳደረኳችሁ አበላሽታ ስለዘመረችው መዝሙር ብቻ ነው። ምርቴም ትረዳኛለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ባትረዳኝም የራሷ ጉዳይ… ኬሬዳሽ…!!

"…ክፍል ፪ ኢ ቃ ጢ ላ ሎ… ጠቢቁ…!!
14.2K viewsedited  09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 12:13:36 ደግሞ ጀመረሽ…?
ለእህቴ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን።
              (ክፍል ፩)

• እንደ መግቢያ…!!

"…በወለጋ እና በራያ ስላለው የህዝብ መከራ አውጥቼ የምጽፍበትን፣ ስለ ምስኪኖች የምጮህበትን ውድ ሰዓቴን ነው ውትወታው ስለበዛብኝ ብቻ ነው ለጊዜው እነሱን ቆም አድርጌ የሰሞኑን የአዳራሽ ግርግር በተመለከተ አጠር ብላ ረዘም ያለች ሃሳብ ሰጥቼ ለማለፍ ስል በዚህ ጦማር የተከሰትኩት። ሆኖም ግን (ጽድቅን ፅድቅ) ብሎ በመጻፍ ቤተ ክርስቲያኒቱን ስለማያውቃት የተሃድሶ ማኅበር ስብስብ ዝርዝር ሃተታ ልጽፍ አይደለም የመጣሁት። ስለ አዳራሽ ጉባኤም ሰፊ ሃሳብ አልሰጥም። የእኔኑ ወንድም ዘማሪ ሉልሰገድ ጌታቸው (ቋንቋዬነሽን) ጨምሮ በዚያ አዳራሽ ስለተገኙት ዘማርያንም ከአንዷ ዘማሪት በቀር ምንም አይነት አስተያየት መስጠት አልፈልግም። ምክንያቱም በአዳራሽ ተገኝቶ መዘመርን፣ ጉባኤ በአዳራሽ መሥራትን፣ ለይተን ለአንድ ስብስብ ማጥቂያ አድርገው የሚኳትኑ አስመሳይ የሃይማኖት ዘረኞችን መቀላቀል ስለማልፈልግ ነው። አሁን ዋይ ዋይ ስትል እኮ ለሃይማኖትህ የተቆረቆርክ ትመስላለህ። ለማያውቅህ ታጠን።

"…የአዳራሽ እና የሆቴል ጉባኤ ልክ አይደለም ብለን ተሟግተን በስንት መከራ በስንት ተጋድሎ ካስቀረን በኋላ እኮ ነው ትልቁ ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ ሚጢጢዎቹ ማኅበራት ሁላ ሳይቀሩ ታላላቅ ጉባኤዎችን በየሆቴሉና በየአዳራሹ ሲያደረጉ የከረሙት። እና ያኔ ዝም ጮጋ ብለህ ትከርምና አሁን ድንገት ተነሥተህ ትወበራለህ። ቀፋላ ሁላ…!! በፖስተር ላይ ከቅዱሳን ሥዕላት ጋር ጭምር የዘማሪ፣ የሰባኪ ምሥል እንዳይታተም ተሟግተን፣ ለፍተን፣ ለፍተን ያስቀረነውን ዛሬ ዛሬ በስመ ኦርቶዶክስ ሰባኪነት ስም ሰባኪውም፣ ዘማሪውም በየፖስተሩ ላይ ሥዕለ አድኅኖውን ሚጢጢ፣ ነጥብ አሳክሎ፣ የራሱን ፎቶ ደግሞ ከኪሊማንጃሮ ተራራ የገዘፈ አሳክሎ እያሠራ በየአደባባዩ ሲለጥፍ ባላየ ባልሰማ ዝም፣ ጭጭ ብለህ ትከርምና አሁን ድንገት ብድግ ብለህ ልክ እንደአዲስ ትወበራለህ። አስመሳይ ነህ። ፈሪሳዊን የምታስንቅ አስመሳይ። የምትፈራው ስታገኝ ጭጭ፣ የምትንቀው ስታገኝ መወብራት ደስስ አይልም። ክርስቲያን ማለት በዓላማው የማይወላውል፣ ቀጥ ያለ፣ ፊት አይቶ የማያደላ ማለት ነው። አንተ ግን ጎጤ ነገር ነህ።

"…እነ በጋሻው ደሳለኝን በአዳራሽ፣ በሆቴል ተገኝተው፣ ጉባኤ እንዳይሠሩ፣ ገንዘብ እንዳይለምኑ፣ ምእመናንን እንዳይሰበስቡ ሞገትን። እነበጋሻውን፣ እነ ከፍያለው ቱፋን አዳራሽ ለአዳራሽ፣ ሆቴል ለሆቴል አሯሯጥን። እነሱም እጅ ሰጡ፣ ድራሽ አባታቸውም ጠፋ። በዚያው በአዳራሽ ልክፍት ተለክፈው አዳራሽ ከፍተው ወጥተው ቀሩ። ከዚያ በኋላስ ምንድነው የሆነው? የእነ በጋሻውን የአዳራሽ ጉባኤ፣ የሆቴል ጉባኤ ካስቆምን በኋላ በምትኩ እኮ ወደ አዳራሽ ጉባኤ የተመሙት ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ማኅበራት ናቸው። ሰባኪያን፣ ዘማርያን ናቸው። ለእነ ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ የሚፈቀድ የሆቴል አዳራሽ ለሌሎች የሚከለከልበት ምክንያት ምንድነው? የገባው ያስረዳኝ። ያውም  እኮ ክትፎ የሚያዘጋጁ፣ ወይንና ውስኪ በሚያወርዱ አዳራሾች ነው ጉባኤው የሚሠራው። በእነ በጋሻው ላይ ዱላ ሲያወርድ የከረመው ሰባኪ ነኝ፣ ዘማሪ ነኝ፣ ወላ ቀናኢ ምእመን ነኝ ባይ ሁላ ለካስ ይቀና የነበረው ለቀኖናው መጣስ ሳይሆን በእነ በጋሻው ሃብት፣ ሰው መሰብሰብ፣ መኪና መቀያየር እንጂ ለሃይማኖቱ አልነበረም። እነ በጋሻውን ከመድረክ አውርዶ አዳሜ እሱ መድረክ ላይ ወጥቶ እንደነበጋሻው በተዋሕዶ ስም ሲነግድ ማን ተናገረው? በየአዳራሹ ሲነግድ፣ በቤተ ክርስቲያን ስም ሚሊዮኖችን ሲዘርፍ፣ የመጽሐፍ ምረቃ፣ የሲዲ ምረቃ እያለ በየሆቴሎቹ አዳራሾች ሲንገዋለል ማን ተናገረ? መጋቤ ሃዲስ እሸቱ እና ዶር ቀሲስ ዘበነ በየ ብሔራዊ ቲያትሩ፣ በየ ክትፎ ቤት አዳራሹ የስታንዳፕ ኮሜዲ ምሽት አዘጋጅተው በሳቅ ህዝቡን ሲያፈርሱት ማን ተናገረ። የውም ከፓስተር ከኡስታዝ ጋር እየተጎራረሱ፣ እየተመራረቁ። አሁንም እንደዚያው ነው። ምድረ ምቀኛ። ሃይማኖት፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጣስ ሳይሆን የሚያንገበግብህ ቅናት ነው። ተበለጥን፣ ተወዳዳሪ መጣብን፣ የፈረንጅ ላም፣ ላሜ ቦራ ምእመናኖቻችንን የሚቀማን የተደራጀ ዘመናዊ ኃይል መጣብን የሚሉ የቀናተኞች ድምጽ ነው።

"…"ፍኖተ ጽድቅ ማኅበር" በተሃድሶዎቹ እንደተቋቋመ ዛሬ ነው እንዴ የታያችሁ? የማኅበሩ መሥራች፣ በገንዘብ ኢንቨስት የሚያደርገው ባለሃብት በቀጥተኛው መንገድ ሳይሆን በጓሮ በር መጥቶ በመምህር ምህረተአብ አሰፋ የሲዲ ምርቃት፣ የቴሌቭዥን የአየር ሰዓት ክፍያ ላይ ተገኝቶ በነበረ ሰዓት ምህረተአብ በቃ ይኸው ፀጋዬ ሮቶ ተመልሷል፣ ተሃድሶነቱን ትቷል፣ አቡነ መቃርዮስ ይጸልዩለት፣ ፋንታሁን ሙጨ አልቅስለት ብሎ ካባ አልብሶ፣ መድረክ ላይ በግንባሩ እንዲደፋ አድርጎ፣ ቀኖና ሰጥቶት፣ ገንዘብ ለራሳቸው ሲቀባበሉት ቆይተው ዛሬ የእዚሁ ባለሀብት ማኅበር ደርጅቶ መፋፋት ሲጀምር የምን መንጫጫት ነው? "አሀ ከዚህ ሰውዬ ጋር የተጠጉ ግለሰቦች መጡብን እኮ፣ ዝናችንን፣ የሀብት ምንጫችን የሆኑትን ምእመናኖቻችንን ሊቀሙን መጡብን ብሎ መወብራት አስመሳይ ቀጣፊነት ነው። ምድረ ሌባ ሞላጫ ሁላ። ፐ ለሃይማኖትህ ተቆርቁረህ ሞተሃል?

"…እደግመዋለሁ ስለ አዳራሽ ጉባኤ ሃሳብ አልሰጥም። ስለ ፖስተር ሃሳብ አልሰጥም። ታግለን፣ ታግለን፣ ታስረንበት ሁላ ጭምር ዋጋ ከፍለንበት ቀርቶ ነበር። ከቀረ በኋላ ግን ሁልሽም ተነካክተሽ፣ መልሰሽ ተዘፍቀሽበት ስታብጂበት ከቆየሽ በኋለ ደርሰሽ አሁን ዋይ ዋይ ስትዪ ይደብራል። እነ በጋሻው ደሳለኝን በተቃወምክበት አፍህ እነ ምህረተአብንም መቃወም የግድ ይልህ ነበር። የጥላቻ ተቃውሞ እኮ አይደለም። በፍቅር ልክ አይደላችሁም ማለት ሳትደፍር አሁን ደርሰህ ፍኖተ ጽድቅ የሚባለውን የተሃድሶ ማኅበር ለመቃወም አትላላጥ። ከተቃወምክ ሁለቱንም። የመጽሐፍ፣ የሲዲ ምረቃ ላይ ባለሀብቱ ከሆቴል በቀር አይመጣልንም እያልክ ባለሀብቱን ፍለጋ ሆቴል ለሆቴል ስትልከሰከስ፣ ስትርመጠመጥ ከርመህ አሁን አንተ የምን የአዳራሽ ተቃውሞው ነው ይዘህ የምትዘበዝበው። ሌላው አዳራሽ ሲከሰት ግን ኡኡ ሃይማኖቴ ተደፈረ። ይሄ ኃጢአት ነው፣ ወንጀልም ነው። ከባድ ነው። ወዘተ ብሎ ማናፋት። ሌላው የአንተ የመሰለህ ግን ሲንቦጫረቅ እያየህ ዲዳና ደንቆሮ፣ ማየት የተሳነውም ሆነህ ቁጭ። ከተቃወምክ ሌላውን በተቃወምክበት አፍህ ማኅበረ ቅዱሳንም በሆቴል ጉባኤ ሲጣድ መቃወም፣ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌም፣ ምህረተአብም፣ ዳንኤል ክብረትም፣ ምንዳዬ ብርሃኑም በሆቴል ሲጣድ መቃወም አለብህ እንጂ የሆኑ ሰዎችን ለይተህ እየመረጥክ ስትንጫጫ ይደብራል። ደግሞስ በገጠር እየታረደ፣ እየተቃጠለ፣ እየወደመ ስላለው የሃይማኖት አባትህ፣ ወንድም እህቶችህ ምንም ሳትተነፍስ አሁን ደርሰህ አዳራሽ ውስጥ ተዘመረ ብለህ ፌስቡኩን ሙሉ በሙሉ ፍኖተ ጽድቅ፣ ፍኖተ ጽድቅ እያስባልክ ስታላዝንበት ማየት ሼም ነው። ኧረ እፈር።

"…እኔ አሁን በፍኖተ ጽድቅ ተብዬው አዳራሽ ውስጥ ስለተገኙት ዘማርያንና ሰባኪያን አልጽፍም። ስለ ሉሌም ጭምር አልጽፍም። ስለ ቸርነትም አልጽፍም። ቸርነት እንኳ ሃይማኖት የለውም። አይደለም አዳራሽ ቃልቻ ቤት ገንዘብ ይገኛል ከተባለ አይኑን የማያሽ ከልጅነቱ ጀምሮ የማውቀው ሰው ስለሆነ ስለ እሱ አልጽፍም። ስለ የትምወርቅ በገና አልጽፍም። እናንተም ለይታችሁ ስላልጻፋችሁበት ስለ ዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ እኔም አልጽፍም። ቴዲ ፀጋው ነው። ምን የተገለጠ ኃጢአት ቢሠራ ዱላ የማይበዛበት ሁሉ የሚከልለው
14.5K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 12:02:13
"…መልእክቱ ደርሶኛል። ሌላሌላው ጉዳይ ይዞኝ ነው እንጂ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ አስተያየት ሰጥቼ ለማለፍ ፈልጌ ሃሳቤን ጽፌ ካስቀመጥኩ ቆየሁ። አሁን ግን ውትወታው ሲበዛብኝ ብቻ ሳይሆን ያን የጻፍኩትን ሃሳቤን አስመዝግቤ፣ ለታሪክም አስቀምጬ ለማለፍ ስል መጥቻለሁ። ታዲያ ስናወራ፣ እኔም ለማውራት ለመደስኮር ስመጣ እንደተለመደው ነጭ ነጯን ነው የምንነጋገረው እንጂ ወርቅ ቅብ ብሎ ነገር የለም። የሚሰማኝን ዝርግፍ። የሚከፋው ይኖራል ጉዳዩ ነው። ቅርም የሚለው ይኖራል እሱም ጉዳዩ ነው። ኬሬዳሽ።

"…ቤተ ክርስቲያኒቱን አይደለም ለጽድቅ "ፅ" እና "ጽ" ን ለይቶ መጻፍ መጠቀም ከማይችል ሀ ገደሉ ድልብ መንጋ የተሃድሶ ቅሪት ጋርም አፍ ለመካፈት ብዬ አይደለም የመጣሁት። አንዲት ተቃውሞዬን ለምርትነሽ ብቻ ለመስጠት ነው የመጣሁት።

• ወዳጄም ወንድሜም መምህር ጳውሎስ መልክአሥላሴን በዚያ አይቼዋለሁ።
• ወንድሜን ቴዎድሮስ ዮሴፍንም አይቼዋለሁ።
• እህቴን ራሴው አምጥቼ ግጥምና ዜማ ሰጥቼ ዘማሪ ያደረግኳትን አዜብ ከበደበንም አይቻታለሁ።
• እንደ ወንድሜም ከልጆቼ እንደ እንዱ ልጄም የምቆጥረውን ዘማሪ ሉሌንም አይቼዋለሁ። ሌሎችንም አይቻለሁ። ለምን እዚያ ቦታ እንደተገኙ አላውቅም። ሉሌም እስከአሁን ደውሎም አልነገረኝም። መረዋም አልነገረኝም። ብቻ እኔ ስለዚህ ልጽፍ አይደለም የመጣሁት። እኔ የመጣሁት ምርትነሽን ልማጸናት ነው። እንጂ ስለ ወለጋና ስለ ራያ የምጮህላቸው ምስኪኖች ጉዳይ ነበረኝ። ይሄን ዛሬውኑ በቶሎ ጨርሼ እመለስበታለሁ።

"…ለዛሬ ግን በ፪ ክፍል አሰናድቼ ያቀረብኩትን ሃሳቤን አንብቡልኝ። አንብቡልኝ እና ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እናንተም በነፃነት ትተነፍሳላችሁ።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ
18.1K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 20:26:07
"…እነ ወሴም ስንቁም፣ ትጥቁም በሰዓቱ ደርሶና እያሉ ነው። ገለቶማም ብለዋል።

• በሰሜን ትግራይ ጦርነቱ ቀልጧል። በራያ የቆቦ ሰው ወደ ወልድያ እቃውን ሸክፎ መሰደድ ጀምሯል። ህወሓት በዋጃ በኩል ሰራዊቷን እያስጠጋች ነው። መከላከያ አንዲት ጥይት በራያ በኩል ወደ ትግራይ ኃይል እንዳይተኮስ አዟል። ከአስፓልቱ በቀር ገጠሩ የራያ ህዝብ አሁንም በህወሓት እጅ ነው።

• ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ተብለው በብአዴን እንደ ከፍት ተነድተው ዘብጥያ የተወረወሩት ከ12ሺ በላይ የዐማራ ፋኖዎች እስከአሁን የት እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም። አሳሪዎቹ ዘጭ ብለው ፈታ ብለው ይኖራሉ። ደርግ።

• ኦነግ እዚህ ምዕራብ ሸዋ መንግሥትን ተክቶ ግብር ማስገበር ጀምሯል።

• አሻማ… አለ አልነጃሺ…!!
59.2K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 18:01:34
ይድረስ ለዶር ብርሃኑ ነጋ

"…እነ ሌቦ ጀዋር መሀመድ ሌብነትን እንደ ትግል ስልት አድርገው ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ጎትተው ካመጡ ወዲህ ጨዋ፣ እንደ ቤተ መቅደስም ይፈራ የነበረውን የኢትዮጵያን የፈተና ሥርዓት ብልሽትሽቱን ማውጣታቸው ይታወቃል። ውሻ በቀደደው ጅቦቹ ገብተው ይባስ ብለው የክልል ሓላፊዎች፣ መምህራንና ባለሥልጣናት ሁሉ ተሳታፊ ሆነው በችርቻሮ ሳይሆን በጅምላ በተሰረቀ ፈተና ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲያግዙም ከርመዋል።

"…እናም ዶክተሩ ሆይ፣ ይሄን የገረረ፣ የከረረ፣ የገነገነ፣ የደነደነ ሌብነት ለመቀነስ፣ ከተቻለም ለማጥፋት የወሰዱት እርምጃ በእኔ እይታ የሚደገፍ ነው። 1 ቢልዮን ብር ኪሳራም ቢኖረውም ሙከራው የሚበረታታ ነው። በሂደቱ የተፈጠሩት ያረገዙ ተማሪዎች መውለዳቸው፣ የመኪና አደጋ፣ የድልድይ መሰበር፣ የሞትና መቁሰሉ ሁኔታም የፈጣሪ ሥራ እንጂ የእርስዎ ሴራ ነው ብዬም አላምንም። የሞቱትን ነፍስ ይማር። የቆሰሉትን ምህረት ፈውሱን ይላክላቸው።

"…የሆነው ሆኖ ዶፍተር ሆይ ሙከራዎ በአንዴ ባይጠራም በሂደት መቀነሱ ግን አይቀሬ። ነገር ግን ዘንድሮም ቢሆን እዛው ኦሮሚያ ውስጥ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ተሰርቆ የወጣ ነው የተባለ የእንግሊዝኛና የሂሳብ የፈተና ወረቀት በኢንተርኔት ሲዟዟር ታይቷል። ከፈተና በኋላ የተነሣ ይሁን ከፈተና በፊት ብቻ እንደ ድሮው በቴሌግራም በኅብረት ይሠሩታል ባልልም የተወሰኑ የሌባ ልጆች ስልክ አጭበርብረው ይዘው ገብተው ፎቶ አንሥተው መበተናቸው አልቀርም። ለዚህ ደግሞ ፍቱን መድኃኒቱ አለ። እሱም ለፍርዬ መንገር ነው። ኦነግ ዐማራን ሊያርድ ሆሮጉዱሩ ሲገባ ብቻ አይደለም ኢንተርኔት መዝጋት ፈተናው እስኪያልቅ ቢያንስ ከባልቦላው ምናለ አጥፍታ ብታግዝዎት። ደፍረው እንደ ዐቢይ አሕመድ ይጠይቋት። ወይ እሺ፣ ወይ እምቢ ነው የምትልዎት።

• ፈጣሪ ይርዳዎት።
70.1K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ