Get Mystery Box with random crypto!

ደግሞ ጀመረሽ…? ለእህቴ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን።               (ክፍል ፩) • እን | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ደግሞ ጀመረሽ…?
ለእህቴ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን።
              (ክፍል ፩)

• እንደ መግቢያ…!!

"…በወለጋ እና በራያ ስላለው የህዝብ መከራ አውጥቼ የምጽፍበትን፣ ስለ ምስኪኖች የምጮህበትን ውድ ሰዓቴን ነው ውትወታው ስለበዛብኝ ብቻ ነው ለጊዜው እነሱን ቆም አድርጌ የሰሞኑን የአዳራሽ ግርግር በተመለከተ አጠር ብላ ረዘም ያለች ሃሳብ ሰጥቼ ለማለፍ ስል በዚህ ጦማር የተከሰትኩት። ሆኖም ግን (ጽድቅን ፅድቅ) ብሎ በመጻፍ ቤተ ክርስቲያኒቱን ስለማያውቃት የተሃድሶ ማኅበር ስብስብ ዝርዝር ሃተታ ልጽፍ አይደለም የመጣሁት። ስለ አዳራሽ ጉባኤም ሰፊ ሃሳብ አልሰጥም። የእኔኑ ወንድም ዘማሪ ሉልሰገድ ጌታቸው (ቋንቋዬነሽን) ጨምሮ በዚያ አዳራሽ ስለተገኙት ዘማርያንም ከአንዷ ዘማሪት በቀር ምንም አይነት አስተያየት መስጠት አልፈልግም። ምክንያቱም በአዳራሽ ተገኝቶ መዘመርን፣ ጉባኤ በአዳራሽ መሥራትን፣ ለይተን ለአንድ ስብስብ ማጥቂያ አድርገው የሚኳትኑ አስመሳይ የሃይማኖት ዘረኞችን መቀላቀል ስለማልፈልግ ነው። አሁን ዋይ ዋይ ስትል እኮ ለሃይማኖትህ የተቆረቆርክ ትመስላለህ። ለማያውቅህ ታጠን።

"…የአዳራሽ እና የሆቴል ጉባኤ ልክ አይደለም ብለን ተሟግተን በስንት መከራ በስንት ተጋድሎ ካስቀረን በኋላ እኮ ነው ትልቁ ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ ሚጢጢዎቹ ማኅበራት ሁላ ሳይቀሩ ታላላቅ ጉባኤዎችን በየሆቴሉና በየአዳራሹ ሲያደረጉ የከረሙት። እና ያኔ ዝም ጮጋ ብለህ ትከርምና አሁን ድንገት ተነሥተህ ትወበራለህ። ቀፋላ ሁላ…!! በፖስተር ላይ ከቅዱሳን ሥዕላት ጋር ጭምር የዘማሪ፣ የሰባኪ ምሥል እንዳይታተም ተሟግተን፣ ለፍተን፣ ለፍተን ያስቀረነውን ዛሬ ዛሬ በስመ ኦርቶዶክስ ሰባኪነት ስም ሰባኪውም፣ ዘማሪውም በየፖስተሩ ላይ ሥዕለ አድኅኖውን ሚጢጢ፣ ነጥብ አሳክሎ፣ የራሱን ፎቶ ደግሞ ከኪሊማንጃሮ ተራራ የገዘፈ አሳክሎ እያሠራ በየአደባባዩ ሲለጥፍ ባላየ ባልሰማ ዝም፣ ጭጭ ብለህ ትከርምና አሁን ድንገት ብድግ ብለህ ልክ እንደአዲስ ትወበራለህ። አስመሳይ ነህ። ፈሪሳዊን የምታስንቅ አስመሳይ። የምትፈራው ስታገኝ ጭጭ፣ የምትንቀው ስታገኝ መወብራት ደስስ አይልም። ክርስቲያን ማለት በዓላማው የማይወላውል፣ ቀጥ ያለ፣ ፊት አይቶ የማያደላ ማለት ነው። አንተ ግን ጎጤ ነገር ነህ።

"…እነ በጋሻው ደሳለኝን በአዳራሽ፣ በሆቴል ተገኝተው፣ ጉባኤ እንዳይሠሩ፣ ገንዘብ እንዳይለምኑ፣ ምእመናንን እንዳይሰበስቡ ሞገትን። እነበጋሻውን፣ እነ ከፍያለው ቱፋን አዳራሽ ለአዳራሽ፣ ሆቴል ለሆቴል አሯሯጥን። እነሱም እጅ ሰጡ፣ ድራሽ አባታቸውም ጠፋ። በዚያው በአዳራሽ ልክፍት ተለክፈው አዳራሽ ከፍተው ወጥተው ቀሩ። ከዚያ በኋላስ ምንድነው የሆነው? የእነ በጋሻውን የአዳራሽ ጉባኤ፣ የሆቴል ጉባኤ ካስቆምን በኋላ በምትኩ እኮ ወደ አዳራሽ ጉባኤ የተመሙት ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ማኅበራት ናቸው። ሰባኪያን፣ ዘማርያን ናቸው። ለእነ ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ የሚፈቀድ የሆቴል አዳራሽ ለሌሎች የሚከለከልበት ምክንያት ምንድነው? የገባው ያስረዳኝ። ያውም  እኮ ክትፎ የሚያዘጋጁ፣ ወይንና ውስኪ በሚያወርዱ አዳራሾች ነው ጉባኤው የሚሠራው። በእነ በጋሻው ላይ ዱላ ሲያወርድ የከረመው ሰባኪ ነኝ፣ ዘማሪ ነኝ፣ ወላ ቀናኢ ምእመን ነኝ ባይ ሁላ ለካስ ይቀና የነበረው ለቀኖናው መጣስ ሳይሆን በእነ በጋሻው ሃብት፣ ሰው መሰብሰብ፣ መኪና መቀያየር እንጂ ለሃይማኖቱ አልነበረም። እነ በጋሻውን ከመድረክ አውርዶ አዳሜ እሱ መድረክ ላይ ወጥቶ እንደነበጋሻው በተዋሕዶ ስም ሲነግድ ማን ተናገረው? በየአዳራሹ ሲነግድ፣ በቤተ ክርስቲያን ስም ሚሊዮኖችን ሲዘርፍ፣ የመጽሐፍ ምረቃ፣ የሲዲ ምረቃ እያለ በየሆቴሎቹ አዳራሾች ሲንገዋለል ማን ተናገረ? መጋቤ ሃዲስ እሸቱ እና ዶር ቀሲስ ዘበነ በየ ብሔራዊ ቲያትሩ፣ በየ ክትፎ ቤት አዳራሹ የስታንዳፕ ኮሜዲ ምሽት አዘጋጅተው በሳቅ ህዝቡን ሲያፈርሱት ማን ተናገረ። የውም ከፓስተር ከኡስታዝ ጋር እየተጎራረሱ፣ እየተመራረቁ። አሁንም እንደዚያው ነው። ምድረ ምቀኛ። ሃይማኖት፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጣስ ሳይሆን የሚያንገበግብህ ቅናት ነው። ተበለጥን፣ ተወዳዳሪ መጣብን፣ የፈረንጅ ላም፣ ላሜ ቦራ ምእመናኖቻችንን የሚቀማን የተደራጀ ዘመናዊ ኃይል መጣብን የሚሉ የቀናተኞች ድምጽ ነው።

"…"ፍኖተ ጽድቅ ማኅበር" በተሃድሶዎቹ እንደተቋቋመ ዛሬ ነው እንዴ የታያችሁ? የማኅበሩ መሥራች፣ በገንዘብ ኢንቨስት የሚያደርገው ባለሃብት በቀጥተኛው መንገድ ሳይሆን በጓሮ በር መጥቶ በመምህር ምህረተአብ አሰፋ የሲዲ ምርቃት፣ የቴሌቭዥን የአየር ሰዓት ክፍያ ላይ ተገኝቶ በነበረ ሰዓት ምህረተአብ በቃ ይኸው ፀጋዬ ሮቶ ተመልሷል፣ ተሃድሶነቱን ትቷል፣ አቡነ መቃርዮስ ይጸልዩለት፣ ፋንታሁን ሙጨ አልቅስለት ብሎ ካባ አልብሶ፣ መድረክ ላይ በግንባሩ እንዲደፋ አድርጎ፣ ቀኖና ሰጥቶት፣ ገንዘብ ለራሳቸው ሲቀባበሉት ቆይተው ዛሬ የእዚሁ ባለሀብት ማኅበር ደርጅቶ መፋፋት ሲጀምር የምን መንጫጫት ነው? "አሀ ከዚህ ሰውዬ ጋር የተጠጉ ግለሰቦች መጡብን እኮ፣ ዝናችንን፣ የሀብት ምንጫችን የሆኑትን ምእመናኖቻችንን ሊቀሙን መጡብን ብሎ መወብራት አስመሳይ ቀጣፊነት ነው። ምድረ ሌባ ሞላጫ ሁላ። ፐ ለሃይማኖትህ ተቆርቁረህ ሞተሃል?

"…እደግመዋለሁ ስለ አዳራሽ ጉባኤ ሃሳብ አልሰጥም። ስለ ፖስተር ሃሳብ አልሰጥም። ታግለን፣ ታግለን፣ ታስረንበት ሁላ ጭምር ዋጋ ከፍለንበት ቀርቶ ነበር። ከቀረ በኋላ ግን ሁልሽም ተነካክተሽ፣ መልሰሽ ተዘፍቀሽበት ስታብጂበት ከቆየሽ በኋለ ደርሰሽ አሁን ዋይ ዋይ ስትዪ ይደብራል። እነ በጋሻው ደሳለኝን በተቃወምክበት አፍህ እነ ምህረተአብንም መቃወም የግድ ይልህ ነበር። የጥላቻ ተቃውሞ እኮ አይደለም። በፍቅር ልክ አይደላችሁም ማለት ሳትደፍር አሁን ደርሰህ ፍኖተ ጽድቅ የሚባለውን የተሃድሶ ማኅበር ለመቃወም አትላላጥ። ከተቃወምክ ሁለቱንም። የመጽሐፍ፣ የሲዲ ምረቃ ላይ ባለሀብቱ ከሆቴል በቀር አይመጣልንም እያልክ ባለሀብቱን ፍለጋ ሆቴል ለሆቴል ስትልከሰከስ፣ ስትርመጠመጥ ከርመህ አሁን አንተ የምን የአዳራሽ ተቃውሞው ነው ይዘህ የምትዘበዝበው። ሌላው አዳራሽ ሲከሰት ግን ኡኡ ሃይማኖቴ ተደፈረ። ይሄ ኃጢአት ነው፣ ወንጀልም ነው። ከባድ ነው። ወዘተ ብሎ ማናፋት። ሌላው የአንተ የመሰለህ ግን ሲንቦጫረቅ እያየህ ዲዳና ደንቆሮ፣ ማየት የተሳነውም ሆነህ ቁጭ። ከተቃወምክ ሌላውን በተቃወምክበት አፍህ ማኅበረ ቅዱሳንም በሆቴል ጉባኤ ሲጣድ መቃወም፣ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌም፣ ምህረተአብም፣ ዳንኤል ክብረትም፣ ምንዳዬ ብርሃኑም በሆቴል ሲጣድ መቃወም አለብህ እንጂ የሆኑ ሰዎችን ለይተህ እየመረጥክ ስትንጫጫ ይደብራል። ደግሞስ በገጠር እየታረደ፣ እየተቃጠለ፣ እየወደመ ስላለው የሃይማኖት አባትህ፣ ወንድም እህቶችህ ምንም ሳትተነፍስ አሁን ደርሰህ አዳራሽ ውስጥ ተዘመረ ብለህ ፌስቡኩን ሙሉ በሙሉ ፍኖተ ጽድቅ፣ ፍኖተ ጽድቅ እያስባልክ ስታላዝንበት ማየት ሼም ነው። ኧረ እፈር።

"…እኔ አሁን በፍኖተ ጽድቅ ተብዬው አዳራሽ ውስጥ ስለተገኙት ዘማርያንና ሰባኪያን አልጽፍም። ስለ ሉሌም ጭምር አልጽፍም። ስለ ቸርነትም አልጽፍም። ቸርነት እንኳ ሃይማኖት የለውም። አይደለም አዳራሽ ቃልቻ ቤት ገንዘብ ይገኛል ከተባለ አይኑን የማያሽ ከልጅነቱ ጀምሮ የማውቀው ሰው ስለሆነ ስለ እሱ አልጽፍም። ስለ የትምወርቅ በገና አልጽፍም። እናንተም ለይታችሁ ስላልጻፋችሁበት ስለ ዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ እኔም አልጽፍም። ቴዲ ፀጋው ነው። ምን የተገለጠ ኃጢአት ቢሠራ ዱላ የማይበዛበት ሁሉ የሚከልለው