Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ነው። ሁላችሁ ስለጨፈጨፋችኋት፣ ለይታችሁ ስለወገራችኋት ስለዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ግን እጽ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዘማሪ ነው። ሁላችሁ ስለጨፈጨፋችኋት፣ ለይታችሁ ስለወገራችኋት ስለዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ግን እጽፋለሁ። ስለ ምርቴም የምጽፈው ለምን በአዳራሹ ተገኝተሽ ዘመርሽ ብዬ ሳይሆን በአዳራሹ ውስጥ ተገኝተሽ አጣመሽ፣ ሰባብረሽ የዘመርሽው መዝሙር ትክክል አይደለም ብዬ እንዳትደግመው ልማጸናት ነው። ስለራሷም መዝሙር አያገባኝም። ስትፈልግ በጉራጊኛ፣ ስትፈልግ በጎጃም በጎንደርኛ፣ ስትፈልግ በምንጃርኛ፣ ከቻለች ለምን በሬጌ ስልት አትጨፍረውም። አያገባኝም። እኔ ግን የቆየ ኦርቶዶክሳዊ የሰው መዝሙር ስትዘምሪ አስተካክለሽ ዘምሪ ብቻ ለማለት ነው የምጽፍባት እንጂ ለምን አዳራሽ ተገኘሽ ብዬ አይደለም። ከአዳራሽ ማን እንደቀረ ነው ምርትነሽ የምትቀረው? ምርቴ አይደለም አዳራሽ ለምን ስታዲዮም አትዘምርም። ማን እንደተነቀፈ፣ ማን እንደተከለከለ ነው የምነቅፋት? የእኔ የአሁኑ ተቃውም ምርቴ ላይ ብቻ ነው። ምርቴንም የምቃወመው ከላይ ጠቆም እንዳደረኳችሁ አበላሽታ ስለዘመረችው መዝሙር ብቻ ነው። ምርቴም ትረዳኛለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ባትረዳኝም የራሷ ጉዳይ… ኬሬዳሽ…!!

"…ክፍል ፪ ኢ ቃ ጢ ላ ሎ… ጠቢቁ…!!