Get Mystery Box with random crypto!

'…ተቃውሞዬ እዚህ መዝሙር ላይ ነው። ምርትነሽን የምቃወማት እዚህ መዝሙር ላይ ነው። ምክንያቴን ከ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ተቃውሞዬ እዚህ መዝሙር ላይ ነው። ምርትነሽን የምቃወማት እዚህ መዝሙር ላይ ነው። ምክንያቴን ከታች በጽሑፍ ገልጬዋለሁ። ለማነጻጸር እንዲመቻችሁ ከታች ኦሪጅናሉን መዝሙር አስቀምጬላችኋለሁ።

• ምርትነሽ ወዝ አሳጣችው።
• ዜማውን ቆራረጠችው።
• እንደ ድሮ የፊሊፕስ ቴም ነካከሰችው።
~ቤዝ ጊታሩን እንደ ፔያኖ ተጠቀመችበት። ፍፁም የመናፍቃን መዝሙር አስመሰለችው። ጴንጤ ላለመባል የማርያምን መዝሙር የግድ መዘመር ካስፈለገም ኦሪጅናል ቀለሙን ሳይለቅ እንጂ የምን ማኪያቶ አስመስሎ አወላግዶ መዘመር ነው? ምርትነሽ የሚቀርጻት ሰው ነው እንጂ ያጣችው አሁንም የጴንጤን መንገድ፣ በእነ ትዝታው፣ ዘርፌ በጋሻው ጎዳና ትሄዳለች ብዬ ብዙም አላስብም። ከሰለሞን አቡበከር ጋር ገጥማ ግን፣ ከፀጋዬ ሮቶ ጋር ገጥማ ግን ጤነኛ ትሆናለች ብዬም ደግሞ አላስብም። ቫይረሱ ከባድ ነው።

ቁጥር አንዱ ምርትነሽ የዘመረችው ነው።
ሁለተኛ ኦሪጅናሉ እህቴ ዘማሪት ስንታየሁ የዘመረችው ነው።
ሦስተኛው ደግሞ ስማቸውን ያላወቅኩት ዘማርያን የዘመሩት ነው። ምርትነሽ አወላግዳ ስትዘምረው መዘምራኑ ግን ኦሪጅናሉን ዘምረውታል። እነ ሰለሞን አቡበከር ኦሪጅናሉን ማጥፋት ነው አላማቸው። ይሄንን ነው የምቃወመው።