Get Mystery Box with random crypto!

ደግሞ ጀመረሽ…? ለእህቴ ዘማሪት ምርትነሽ።           (ክፍል ፪) '…ከላይ የጀመርኩትን | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ደግሞ ጀመረሽ…?
ለእህቴ ዘማሪት ምርትነሽ።
          (ክፍል ፪)

"…ከላይ የጀመርኩትን ነው ለመቋጨት የምቀጥለው። ሌላ የሚያናግር አስገዳጅ አናጋሪ አጀንዳ ካልተገኘ በቀር በዚህ ጉዳይ ይሄ የመጨረሻዬ ነው። አልመለስበትም። ከላይ በቪድዮ በምስል የሰማችሁት "ለማርያም" የሚለው መዝሙር የዜማ ደራሲው ዘማሪ አረጋይ ነው። ዘማሪዋ ደግሞ እህቴ ዘማሪ ስንታየሁ ናት። ሲሰሙት ልብ ወከክ የሚያደርገው የዋሽንት፣ መሰንቆና ክራር ከበሮውም ጭምር ኢንትሮው በእነ ዘውዱ ጌታቸው ክራር፣ ዋሽንቱ በኤልያስ፣ እና ከበሮው አካሉ ዮሴፍ ይመስለኛል የተቀመመው። መግቢያው ራሱ ሲሰማ ልብ ይመስጣል። ይሄን የወጣትነቴን መዝሙር "እመቤታችንን" እያሰብኩ ስዘምረውም ሆነ ስሰማው ጭምር ለነፍሴ እረፍት፣ መረጋጋትን ይሰጠኛል። ጥቂት ከምሰጥባቸው መዝሙራት መካከልም አንዱ ይሄ መዝሙር ነው። ዜማውም፣ ግጥሙም ፍፁም የተዋበ የተሳካ መዝሙር ነው። ደግሞስ ልጆቹ የጎላ ቅዱስ ሚካኤል ልጆች አይደሉ? ዘማሪዋን ዘማሪት ስንታየሁን ከማኅበረ ሥላሴ ማኅበር ጀምሮ ነው የማውቃት። እህቷ እና ጓደኛዋ አብራት የምተዘምረው ሸዋዬም አሁን የት እንዳለች ባላውቅም ከአረብ ሃገር ወደ አውሮጳ ተሻግራ በዚያ ትኖር እንደነበር እሰማ ነበር። አረጋይ እዚያው ኢትዮጵያ ነው። ስንትሽ በትዳር ሆና ከዝማሬው ከራቀች ቆየች።

"…ይሄን መዝሙር ነው እንግዲህ እህታችን ምርትነሽ "ሪሚክስ" አድርጋ እንዲህ ቅጣንባሩን አጥፍታ ባንኮክ ታይላንድ ሄዶ በስፕራይት ጠርሙስ ቢራ ጨምሮ ጠጥቶ ሰክሮ እንደሚረብሽ ሰካራም ጴንጤ እና ወሃቢይ አወለጋግዳ ያቀረበችው። ይሄ በፍጹም ትክክል አይደለም። ምርትነሽ በስንት ድካም ከነበጋሻው፣ ከነዘርፌ፣ ከነትዝታው መንገድ ተለይታ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን የተመለሰች እህቴ ናት። መመለሷን በሰማሁ ጊዜም ካለሁበት ከራየን ወንዝ ማዶ ሆኜ ደውዬ ደስታዬን የገለፅኩላት እህቴም ናት። በመዝሙር ሥራ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍሬ ተዋሕዶ ብዬ በዘመነ VHS የቪሲዲ ሥራን ሟቹ ተስፋዬ ኢዶን ጨምሮ የ12 ዘማርያንን የመዝምር ሥራ " ፍሬ ተዋሕዶ" በሚል በቪድዮ ቀርጬ በመዝሙር መልክ የጀመርኩት እኔ ነኝ። ምርትነሽንም ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ቪድዮ ላይ አካትቼ ሠርቼ ህዝብ ፊት ያቀርብኳትም እኔ ዘመዴ ነኝ። ይሰመርበት…

"…አሁን ግን ይህን ግሩም መዝሙር እህቴ ምርትነሽ እንዲህ ቅጥአምባሩን አጥፍታ አበላሽታ ዘምራው አየሁ። ክራሩን፣ ዋሽንቱን፣ መሰንቆውን አጥፍታ፣ ቤዝ ጊታሩን እንደ ፒያኖ ተጠቅማ አበላሽታ፣ ለዛውን አሳጥታ ስተዘምረው አየሁኝ። መታገስም አቃተኝ። ይሄ እኮ ጌዲኦኛ አይደለም። ጉራጊኛ፣ ጎጃም ጎንደርኛ፣ ወላይትኛም አይደለም። እጅግ የተደከመበት መዝሙር ነው። ልጆቹ አምጠው የወለዱት መዝሙር ነው። የመዝሙሩን ጥንተ ተፈጥሮ ማበላሸት ለምን አስፈለገ? አማካሪዎችሽ እነ ሰለሞን አቡበከር እንደሆን ታጥበው የማይጠሩ ሽንፍላዎች ናቸው። ግማሽ ክርስቲያን እኮ መሆን ጣጣ ነው። የእነሱን ምክር ሰምተሽ ያን የምወደውን መዝሙር በማይሆን፣ እጅግ በሚያስጠላ፣ ቋቅም በሚል አቀራረብ በማቅረብሽ ነው ተቃውሞዬን በግልፅ ለማቅረብ የተገደድኩት። ስለ አዳራሽ መገኘቱ አያገባኝም።

"…መጀመሪያ ባለቤቶቹን አስፈቅደሻልን? አንቺ ከጌዲኦ ሳትወጪ፣ ከይርጋለም ሳትነሺ ነው ይሄ መዝሙር የወጣው። ምንአልባት ዘማሪ አረጋይን ልታውቂው ትቺዪ እንደሁ እንጂ እርግጠኛ ነኝ ዘማሪዎቹን ስንቴንና ሸዋዬን አታውቂያቸውም። ዝም ብሎ የሰው ልጅ በመሳም ሰበብ ንፍጥ እና ለሃጭ መለቅለቅ ይደብራል። "ጎጆዬ፣ ጓዳዬ፣ ይናዳል ተራራው፣ ይሞላል ሸለቆው ብለሽ ስትዘምሪ ስለከረምሽ" አሁን ስለ እመቤታችን መዘመር ብትፈልጊ እንኳን አዲስ መዝሙር ማውጣት ቢያቅትሽ ቀደም ብሎ የወጣውንና በግሩም ሁኔታ የተዘመረውን መዝሙር አወለጋግዶ መዘመር ደግ አይደለም። ይቀፋልም። እኔ በአንቺ አዲስ ዜማ ስሰማው ከምር ቋቅ ነው ያለኝ።

"…እናም እህቴ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ሆይ መጪው ትውልድ የቀደመውን መዝሙር እውነተኛ ቀለም ትቶ በአንቺ የቤዝ ጊታር ሙዚቃ ተመስጦ በዚያው ዶግማ አድርጎት እንዳይቀር አስወግጂልኝ። እባክሽ ይሄን መዝሙር ከተጫነበት ሁሉ አውርጂልኝ። እኔም ለማነጻጸሪያነት ያመጣሁትን ቆይቼ መላ እፈልግለታለሁ ስል በትህትና እጠይቅሻለሁ። አክባሪ ወንድምሽ ዘመድኩን በቀለ ነኝ። ከራየን ወንዝ ማዶ።

"…ይሄን እዚህ ጋር ዘጋሁ። አሁን ወደ ወለጋ፣ ራያ እና ትግራይ ልብረር።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ