Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ታቦር የሆነው እንዲህ ነው። '…በደቡብ ጎንደር በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትናንት ለፈተና | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በደብረ ታቦር የሆነው እንዲህ ነው።

"…በደቡብ ጎንደር በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትናንት ለፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ፈተናው በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይም በኦሮሚያ ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል መባልን እንደሰሙና እንደራጋገጡም በመናገር አንዳንድ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይጀምራሉ። በዚህ የተነሣ ጥያቄውን አጥብቀው ይጠይቁ የነበሩ ተማሪዎችን ፖሊስ ወደ ዘብጥያ ማውረዱ ይነገራል። ይሄ በዚህ አለፈ።

"…መሸ… ነጋ… ሁለተኛም ቀን ሆነ። ዛሬ ማለት ነው። ጠዋት ላይ ተማሪዎች ትናንት የታሠሩት ተማሪዎች እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀርባሉ። በዚህም መካከል ፈተናው ሳይጀመር በ https://t.me/Qeeroo12 በሚባለው ቴሌግራም ቻናል ላይ እንደተለመደው የጂኦግራፊና የአቲትዩድ ፈተናዎች ናቸው የተባሉ መረጃዎች መለቀቅ ይጀምራሉ። ከውጭ ያለው ህዝብም ፈተናው መሰረቁን በጩኸት መናገር ጀመረ። ተማሪዎች ፈተና ሳይጀምሩ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናው ከመጀመሩም በላይ የቄሮ ሚዲያ ፈተናውን እያሰጣ መሆኑን በመስማት መረጋጋት ጠፋ። ተሜ ተበሳጨ። ተቃወመም።

"…ቆይቶም የጸጥታ ኃይል ወደ ዩኒቨርሲቲው ገባ። ድሮም ለዐማራ ትእግስት የሌለው የፀጥታ ኃይል እንደገባ ተማሪዎቹን መቀጥቀጥ ጀመረ። እጅና ጭንቅላቱን አፈረሱት፣ ቀጠቀጡት። ልክ እንደ ፖሊሱ እንዲደድብና እናዳያስተውል ወገሩት። በዱላ ብቻ አልቆመም ወደ ጥይት ተኩስ ተገባ። ብዙ ተማሪዎችም ወደቁ። ግርግሩ ጦዘ፣ ጦፈም። ከተኩሱ ለማምለጥ በተገኘው አቅጣጫ ሁሉ ተማሪው ሮጠ።

"…አሁን 4 እና 9 በሚል ያልተረጋገጠ ቁጥር ያለው የሞት ወሬ ተማሪዎች መሞታቸው እየተነገረ ነው። የቆሰሉም እንደዚያው። ተማሪዎች አሁን ከፈተና ጣቢያው ወጥተዋል። መነሃሪያው በተማሪዎች ተሞልቷል። መኪና ግን የለም። ትርፍ የጫኑ መኪኖችን ፖሊሶች እያስወረዱ ነው። ህዝቡ ጥቂት ተማሪዎችን ሊያስተናግድ፣ ሊያበላ እና ሊያጠጣ ብቻ ነው የሚችለው። ተማሪው ግን ብዙ ነው። በቀጣይ ምን እንደሚሆን አይታወቅም።

"…በተመሳሳይ ወሬ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ ውዝግብ ተነሥቶ ተማሪዎች ከፈተና ጣቢያው መውጣት ጀምረው የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ ግን በሽማግሌዎች ጣልቃ ገብነት ወደ ፈተና ጣቢያው መመለሳቸው ተነግሯል። ከደብረ ማርቆስ መረጃውን ያቀበለኝ ታማኙ የመረጃ ምንጬ አንዷን ተማሪ ያነጋገራት ሲሆን ተማሪዋም "የሌሎችን አላውቅም እኔ ግን ተማሪዎች ሲወጡ የወጣሁት እጅግ በጣም ስለከበደኝ ነው የወጣሁት" እንዳለችው ነው የነገረኝ። እናም አንዳንድ ፈተናው የከበዳቸው ሰነፍ ተማሪዎች በዚህ ግርግር ተጠቅመው እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አካሄድ ሊሄዱ እንደሚችሉና በቋፍ ላይ ያለን ተማሪ ተረጋግቶ እንዳይፈተን ሊያደርጉት እንደሚችሉ ይጠረጠራል። ሰነፎች እረፉ።

"…ትናንት ፈተናው እስኪያልቅ ድረስ ኢንተርኔት ተዘግቶ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግን ፍርዬ ቢያንስ ቴሌግራምን እንኳ ባለመዝጋቷ ትንሽ ውዝግብ መፈጠሩን አይቻለሁ። በተረፈ እንዲያም እንዲህም ተብሎ በሰላም ይለቅ። ከሞት ከግድያ ያድናችሁ። ይሰውራችሁ። ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ። ተማሪዎች ተረጋግታችሁ ተፈተኑ። እናንተ እንድትረበሹና ተረጋግታችሁ እንድትፈተኑ የሚፈልግ ኃይል እንዳለም ዕወቁ። እየቆየ የሚሆነውን ብናይም ዘንድሮ ግን ፈተናው እንደድሮው በጀማ የመሥራቱ ነገር በጣም የጠበበ መሆኑንም ለማረጋገጥ ችያለሁ። ስህተት ቢኖርም ስህተቱ ግን እንደ አምና ካቻምናው አይሆንም። ተረጋግታችሁ ተፈተኑ።

"…ሻሎም…!  ሰላም…!