Get Mystery Box with random crypto!

'…መልእክቱ ደርሶኛል። ሌላሌላው ጉዳይ ይዞኝ ነው እንጂ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ አስተያየት ሰጥቼ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልእክቱ ደርሶኛል። ሌላሌላው ጉዳይ ይዞኝ ነው እንጂ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ አስተያየት ሰጥቼ ለማለፍ ፈልጌ ሃሳቤን ጽፌ ካስቀመጥኩ ቆየሁ። አሁን ግን ውትወታው ሲበዛብኝ ብቻ ሳይሆን ያን የጻፍኩትን ሃሳቤን አስመዝግቤ፣ ለታሪክም አስቀምጬ ለማለፍ ስል መጥቻለሁ። ታዲያ ስናወራ፣ እኔም ለማውራት ለመደስኮር ስመጣ እንደተለመደው ነጭ ነጯን ነው የምንነጋገረው እንጂ ወርቅ ቅብ ብሎ ነገር የለም። የሚሰማኝን ዝርግፍ። የሚከፋው ይኖራል ጉዳዩ ነው። ቅርም የሚለው ይኖራል እሱም ጉዳዩ ነው። ኬሬዳሽ።

"…ቤተ ክርስቲያኒቱን አይደለም ለጽድቅ "ፅ" እና "ጽ" ን ለይቶ መጻፍ መጠቀም ከማይችል ሀ ገደሉ ድልብ መንጋ የተሃድሶ ቅሪት ጋርም አፍ ለመካፈት ብዬ አይደለም የመጣሁት። አንዲት ተቃውሞዬን ለምርትነሽ ብቻ ለመስጠት ነው የመጣሁት።

• ወዳጄም ወንድሜም መምህር ጳውሎስ መልክአሥላሴን በዚያ አይቼዋለሁ።
• ወንድሜን ቴዎድሮስ ዮሴፍንም አይቼዋለሁ።
• እህቴን ራሴው አምጥቼ ግጥምና ዜማ ሰጥቼ ዘማሪ ያደረግኳትን አዜብ ከበደበንም አይቻታለሁ።
• እንደ ወንድሜም ከልጆቼ እንደ እንዱ ልጄም የምቆጥረውን ዘማሪ ሉሌንም አይቼዋለሁ። ሌሎችንም አይቻለሁ። ለምን እዚያ ቦታ እንደተገኙ አላውቅም። ሉሌም እስከአሁን ደውሎም አልነገረኝም። መረዋም አልነገረኝም። ብቻ እኔ ስለዚህ ልጽፍ አይደለም የመጣሁት። እኔ የመጣሁት ምርትነሽን ልማጸናት ነው። እንጂ ስለ ወለጋና ስለ ራያ የምጮህላቸው ምስኪኖች ጉዳይ ነበረኝ። ይሄን ዛሬውኑ በቶሎ ጨርሼ እመለስበታለሁ።

"…ለዛሬ ግን በ፪ ክፍል አሰናድቼ ያቀረብኩትን ሃሳቤን አንብቡልኝ። አንብቡልኝ እና ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እናንተም በነፃነት ትተነፍሳላችሁ።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ