Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 403.82K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 252

2022-10-10 16:22:01
"…ስንቅ ከራስህ ተብሎ ዳቦቆሎውን ቋጥሮ ከህወሓት ጎሮምሶች ጋር ከፊት መስመር ተሰልፎ ይዋጋ ዘንድ በግርማ የሺጥላ ወደ ግንባር እንዲገቡ የተገደዱት አባቶች አዛውንቶቹ የዐማራ ሚኒሻዎች።

"…ደግሞ የሚዋጉት በቆመህ ጠብቀኝ ነው። አንዴ ተኩሰው 30 ደቂቃ ንፋስ በሚያስመቱት መሳሪያ። ተመልከት መትረየስ፣ ዲሽቃና ስናይፐር ታንክ፣ ዲሽቃና መድፍ ከታጠቀ ኃይል ጋር ያለ ስንቅ በቆመህ ጠብቀኝ ጭዳ ይሆናሉ። ብዙ ሴቶችም ያለባል፣ ያለ አባወራም ይቀራሉ። ከዚያ 4ሴት ማግባት ሃይማኖቱ የሚፈቅድለት መጥቶ ያገባቸዋል። ያ ሃይል አሁን ስለውጊያው አያገባውም። አይመለከተውምም። ዳር ቆሞ ይስቃል።

"…ዝርዝር ዘገባ ይዤ እመለሳለሁ…!!
68.0K views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 14:19:49
እንደምን ዋላችሁ…?

"…ሌላው ሌላው ወሬ እንዳለ ሆኖ በወለጋ ግን ዐማራው ተቆጪ፣ ገልማጭ፣ ከሳሽ በሌለበት መልኩ በዚህ መልኩ ከሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ በከፋ መልኩ እየጸዳ ነው። ቪድዮው ደግሞ አናት ያዞራል።

"…ዐቢይ አሕመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ደመቀ መኮንን እና ጀሌዎቹ ሥራ ላይ ናቸው። ትንኝ የሞተ የተገደለ እንኳን አይመስላቸውም። ክላስተር፣ የበጋ ስንዴ፣ ኤክስፖርት ብቻ ነው ወሬው። ዐብን እንኳ መሪዎቹ በእንግሊዛዊው አንዳርጋቸው ጽጌ ደላላነት ከብልፅግና የሥልጣን ፍርፋሪ ካገኙ በኋላ ስለ ዐማራው ሞት ትንፍሽ ማለት አቁመዋል። ዋ አንቺ ኦሮሚያ…!!

"…እንደተለመደው ነፍስ ይማር እንበል…!!
12.9K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 23:12:36
"…ቀሲስ ልዑልሰገድ በዘመዴ ነጭነጯን ስቱድዮ ከራየን ወንዝ ማዶ ተገኝተዋል…!! ስቱዲዮ አልኳችሁ አይደል? አፉ በሉኝ። ካሜራው ስልክ ነው። መብራቱ የትራስጌ መብራት ነው። አበቃ። ሌላው ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው።

• ይፍቱኝ ይባርኩኝ…!!
16.8K views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 19:31:09
"… ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር …!!

• https://rumble.com/v1n8sj0--zemede-october-2-2022.html

"…ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ሳምንታዊው መደበኛ መርሀ ግብራችን ይጀምራል።በ https://mereja.tv ዌብሳይታችን ላይም ተከታተሉን።

• የዛሬው መርሀ ግብራችን ትንሽ ጫን ያለ ነው። "ህጻናትን፣ ነፍሰጡሮችን፣ የልብ ድካም ያለባቸውን ሰዎች ከቴሌቭዥኑ አካባቢ አርቁ። የወለጋ ጭፍጨፋን ከሞት የተረፉ በቪድዮ አድርሰውኛል። እናም የግድ ማየት አለባችሁ። የግድ፣ በግዳችሁ ማየት አለባችሁ። የራያንም ጉዳይ ዛሬ ነው የሚቀርበው። ጠብቁኝ።

• ጌዜ ሰዓት ከተረፈን ደግሞ ትደውላላችሁ… በጨዋ ደንብ እንወያያለን…!!

• በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ፦
https://donorbox.org/zemedemedia
https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ተመስግናችኋል።

"… ሰብሰብ ብላችሁ እየተወያያችሁ ጠብቁኝማ። ኣ

"… ሻሎም !  ሰላም !
44.9K viewsedited  16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 15:47:27
"…የምታየው ሶሪያ አይምሰልህ። እዚሁ ኢትዮጵያ ነው። ያውም ኦሮሚያ…!! …ወዳጄ አንተን ከዐማራና ከትግሬ ጋር አናክሰው ስትጠዛጠዝ፣ በክላስተር ስንዴ ዜና ሆድህን ነፋፍተው ቀብትተው በወሬ ቁንጣን እያዛጉህ እነሱ ግን በጓዳቸው መቋዲሾ ወሶሪያ ሆነውልሃል። ይሄ ይሄ በሚዲያ አይዘገብም። ማንም እንዲያየው እንዲሰማውም አይፈለገም። የሰሊጥ አክቲቪስቶችም አይደፍሩትም። እነሱ ወያኔ ብለው በምላሳቸው ላይ የተነቀሱትን ቃል ሲደሰኩሩት ነው የሚውሉት።

"…አቢቹ አራዳው ለሌላው ህዝብ ወያኔ፣ ክላስተር፣ የበጋ ስንዴ፣ ሳይንስ ሙዚየም፣ ፓርክ፣ ኢ መደበኛ ታጣቂ… ወዘተርፈ እያለ ያዝገዋል። ኦሮሚያ ግን ቅልጥ ያለ የከተማ ውስጥ ጦርነት ላይ ናት። ቀውጢ ነው።

"…ነገርየው የከፋ ነው። ከምትሰሙትም ከምታነቡትም በላይ ነው። በወለጋ የወሎ ዐማሮች የሚኖሩበት የነበረ ሙሉ ለሙሉ የፈረሰ፣ የነደደም የከተማ ፎቶም ደርሶኛል። አሁን እነሱ ዐማራውን ሙሉ ለሙሉ ሙልጭ ጥርግም አድርገው ኮሽታም፣ ተቃውሞም ሳይሰማ ከወለጋ እያጸዱት ነው። ለማንኛውም በምሽቱ የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ አብረን እናያለን፣ እንፈርዳለንም።

"…የሚመጡት ወሴዎቹ ግን የሚምሩት ሰው የለም። የዐማራው መከራ እንዳለ ሆኖ ብልፅግናን ሙሉ በሙሉ ነው የሚያጸዱት። ዐቢይም ጎንደር ዐማቾቹ ጋር፣ ጎጃም የቢዝነስ አጋሮቹ ጋር፣ አርሲ፣ ጅማ፣ ሸዋ ብቻ የክላስተር እርሻ ከመጎብኘት በቀር ብዙ ነገር ከእጁ እየወጣ ነው። ሽመልስ አብዲሳ ወለጋ ከእጁ ወጥቶም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት ነው። ። ወይ ፕሬዘዳንት እቴ። ትግራይ ከራያ ጋር እጁ ላይ የለም። ምዕራብ ሸዋም ለኦነግ እንጂ ለብልጽግና እንደወለጋ ኢሉአባቦርም ግብር አቁሟል። ሆያሆዬው ሸገር ብቻ ነው። ሶሪያን በኦሮሚያ ተመልከቷት…!!

"…አሻማ አለ አልነጃሺ…!!
59.5K views12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 13:04:14
"…ሃገር ቀጥ አድርጎ የሚመግብ ገበሬ ዛሬ እንዲህ ተስገብግቦ ውኃ በስስት ለምኖ ሲጠጣ ከማየት በላይ ምን የሚያስደነግጥ ነገር አለ። መጋቢህ የሆድህ ጌታ እንዲህ ተሰዶ ከተማ ከገባልህ ከተሜ ሜካፑን ትበላው እንደሁ ይታያል። ጤፍንና የጤፍን ዘር አጥፍቶ ኩታገጠም ማሳ ላይ ዐቢይ ዘራሁት የሚለው የበጋ ስንዴም የሚሸጥ ነው ተብሏል። ባይሸጥም እንኳ ከአንድ መንደር ቀለብነት አያልፍም። በየሰፈራችሁ የምታዩዋቸው እንደነዚህ ያሉ ስደተኛ ገበሬዎችን ቁራሽ በመስጠት ጽደቁባቸው። ቢያንስ በወተት አምገው ይበሉ የነበሩ፣ ቅቤ በአናታቸው፣ አንጀታቸውንም ያርሱበት የነበሩ ሰዎች ናቸውና ውኃ እንኳ አጠጣቸው።
63.5K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 12:07:36
"…የሰንበት መርዶ ነው።

"…ይሄ በወለጋ የሲቡ ስሬ ወረዳ ተጨፍጫፊዎች ናቸው። ኔትወርክ ጠፍቷል። ጭፍጨፋውም ቀጥሏል። የሃጂ ኢብራሂም ቱፋው መጅሊስም ዝም ጭጭ ብሏል። የተጨፈጨፉትም።

1. ሸህ ጂብሪል ኢብራሂም
2. ሸህ ሰኢድ መሀመድ
3. ሸህ አብዱረህማን
4. ሸህ ሰይድ ሽፋ ከ1ልጅና የልጅ ልጃቸው።
5. ሸህ ዩሱፍ በልበል
6. ሼህ አሊ (የጀማል አሊ አባት)
7. መብሬ የ79 ዓመት አዛውንት
8. አህመድ መብሬ
9. ከድጃ ይፍሩ (ከነ2 ዓመት ህጻን ልጇ)
10. የሱፍ ሁሴን
11. ጠይባ አሊ ዳምጠው
12. መሀመድ ሞላ
13. ዘይነባ ሁሴን
14. ሁሴን ጀግኔ
15. የሙራድ አበባው ሚስት ከነ2 ልጆቿ
16. ሀሰን ሰይድ (ሞተረኛ)
17. ፋጡማ ይብሬ (ከሁለት ልጆቿ ጋር)
18. ለጢፉ ሁሴን (ከ1 ዓመት ልጅዋ ጋር)
19. ይፍሩ ገረመው
20. መሬም ገረመው (ከ2ና 3 ዓመት ልጆቿ)
21. ሙራድ ሰዒድ
22. ላቀች አባቡ (ከሁለት ልጆችዋ ጋር)
23. እንድሪስ ኡስማን ሞተረኛ
24. ምሳዬ መሀመድ ከልጇና ከልጅ ልጇ ጋር
25. መሃመድ የኑስ
26. ጀንበሩ አስናቀ
27. ቶሚ ውበቱ
28. የሱፍ ደንጎሮ
29. አብዱ አደም 
30. ሰኢድ አደም
31. መሃመድ የኑስ
32. ዳውድ ታደሰ
33. የሱፍ ሲራጅ
34. ጉዝጉዝ አደም ከሁለት ልጆቿ ጋር
35. ሰኢድ ሰውነት የሸህ ኡመር ማደሎ ልጅ
36. ደምሴ ሀይሉ
37. የሱፍ ይማም
38. መሀመድ ሰኢድ
39. አብዱራማን ኢብራሂም
40. የሱፍኢብራሂም
41. ኑሩ ጫኔ
42. ሁሴን ኢብራሂም 
43. ኡመር ሀሰን (የሼህ መዳሎ ልጆች ከነአባታቸው)
44. አባ አስቻለው (ከ3 ወንድሞቻቸው ጋር)
45. ይሄይስ ፍሬው  ከወንድሞቹ ጋር አብሮ ተገድሏል
46. ባምሌ ተዋበና ቦሰና ባልና ሚስት ከ2 ልጆቻቸው ጋር።

"…ጭፍጨፋው ይቀጥላል…!!
65.7K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 23:14:08
የዛሬ ድብደባ ነው።

"…ኦሮሚያ ቡሌሆራ ያቤሎ አካባቢ ነው። መውሊድ ለምን ታከብራላችሁ? ለምንስ ሱፍይ ሆንናችሁ? እኛ በምናምነው በወሃቢያ መንገድ ኢስልምናን ለምን አትከተሉም? በሚል ጽንፈኛ አመለካከት የተነሣ ዛሬ በመስጊድ ውስጥ ተሰብስበው የመውሊድን በአል በዚህ መልኩ ይፈጽሙ የነበሩ ሲፊዎችን ድብደባ ፈፅመውባቸዋል። ብዙ ሰዎችም መጎዳታቸው ተነግሯል። ወሃቢስቶቹ የሃጂ ኢብራሂም ቱፋ እስላሞች ሱፊዎችን ደማቸውን በመስጊድ ውስጥ አፍሰውታል። ይሄ ትክክል አይደለም። ነውር ነው።

"…95% ሱፊ ባለበት ሀገር በ17 መርፌ አፈላላጊ ኮሚቴ የሚመራ ፅንፈኛ ቡድን ዘመኑ የኦሮሞ ዘመን ነው በማለት እንዲህ አይነት ጋጠወጥ ተግባር መፈጸማቸው በእውነቱ አግባብ አይደለም። አሁን ወሃቢያ መጅሊሱንም ስለተቆጣጠረ፣ ዐቢይም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፕሮጀክቱ ስለሚረዱት ባንክና ታንክም ፈቅዶላቸው የሌለ ሄጵ እንዲሉ አድርጓቸዋል ነው የሚሉት ሱፊዎቹ።

"…ወሀቢያ ማለት አይደለም ለክርስቲያኑ ለእስላሙ አይመለስም። ሃገራችንን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ የመሳሰሉ ሀገራትን እንዳያወደመው ከወዲሁ ሁሉም ሰው በተጠንቀቅ ሃገሩን ከነዚህ ፀረ ሃይማኖት ስብስቦች ሊጠብቅ ይገባል ነው የሚሉት ሱፊዎቹ።

"…አሁን የሽማግሌ እና የህጻናትን ደም ለምን መውሊድ አከበራችሁ ብሎ በዚህ መልክ ደማቸውን በመስጊድ ውስጥ ማፍሰስ ወንጀል ነው። ቁርዓኑም፣ ሀዲሱም የሚፈቅድ አይመስለኝም። በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከበርን በአል ለምን ይከበራል ብሎ ደም ማፍሰስ ምን የሚሉት ነገር ነው።

"…አያገባህም አትበለኝ ያገባኛል። አይመለከትህም አትበለኝ ይመለከተኛል። ደም እያፈሰስክ እንዴት ዝም እልሃለሁ። ገተት።

"…ደኅና እደሩልኝ።
72.6K views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 22:31:41
"…የመርሀ ግብር ማስታወቂያ…

"…ነገ እሑድ ረፋድ ላይ በወለጋ የተጨፈጨፉ ንፁሐን ዐማሮች መርዶ ይኖረኛል። ህጻናት ዐማሮችን ሳይቀር እንዴት አርደው ደማቸውን በኦሮሞ ምድር እንዳፈሰሱ አብረን እንመለከታለን። ቤተሰብ እንዴት ለዘር ሳያስቀሩ እንዳረዱ አብረን እናያለን። በስሙ የሚነግዱት ነፃ አውጪ ልጆቹ እንዴት ኦሮሞ ቀና ብሎ እንዳይሄድ አንገቱን እንዳስደፉት አብረን እናያለን። ትግሬ ትናንት ህወሓት ስታጠፋ ዝም ጭጭ እንዳለው ሁሉ ኦሮሞም ዛሬ በምድሩ ይሄ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም አይቶ ዝም በማለቱ ዋጋውን ከፈጣሪ ዘንድ ይቀበላል።

"…መቼም ስለ ወለጋ ሲነሣ "ኧረ ዝምበል ዘመዴ የሚል ሰው ብዛቱ። በሳቅ እኮ ነው ፍርፍር ሊያበሉኝ የሚሞክሩት። ዝምማ አልልም። ይመዘገባል። ኦሮሞ ዐማራን ማዳን አቅቶት እንዴት እንደጨፈጨፈው፣ እንዳስጨፈጨፈው ተመዝግቦ ለታሪክ ይቀመጣል። በራያም፣ በትግራይም የንፁሐን ጭፍጨፋ ተመዝግቦ ይቀመጣል። ማየት ባትፈልጉም በግድህ ታያታለህ። በግድ አልኩህ።

"…አሻማ…!!
5.7K viewsedited  19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 21:28:53
ትዝብቴን ላካፍላችሁ…!!

"…ዛሬ መውሊድ ነው። የመውሊድ በአል በእስላም ጓደኞቼ ዘንድ በድምቀት የሚያከብሩት በአል ነው። በአሉ እስከዛሬ ድረስ በመላዋ ኢትዮጵያ ሲከበርም ኖሯል።

"…የሆነ ጊዜ ግን 17 የመርፌ አፈላላጊ ኮሚቴ ብለው ራሳቸውን የሰየሙ ወሃቢስቶች ይከሰታሉ። እነሱ ከመጡ በኋላ ግን የመውሊድ በዓል መከበር የለበትም። ሙናፊቅነት ነው ብለው አጥብቀው መሞገት ያዙ። ከክርስቲያን አትግዙ ለክርስቲያን ግን ሽጡ ብለውም ዐወጁ። መንዙማም አስፈላጊ አይደለም የምን ድቤ መቀጥቀጥ ነው ብለውም ዐወጁ። ብዙዎችንም በየመስጊዱ እየገቡ ወገሩ። ገደሉም። 

"…ቆይቶ በበሻሻ ክርስቲያን ኦርቶዶክሶች ሲታረዱ በቦታው ሹመኛ የነበረው የበሻሻው ዐቢይ አሕመድ የሃገሪቱ መሪ ሆነ። ወሃቢስቶቹም የዐቢይ አማካሪ፣ የቤተ መንግሥቱ ቤተኛ ሆኑ። ባንክ ከፈተላቸው። መስቀል ላይ እንዲሰግዱም ፈቀደላቸው። ዐማራ መጅሊሱን መምራት የለበትም ሲሉትም የወሎ ዐማራውን ሃጂ ሙፍቲን አንስቶ ጫላን ሾመላቸው። ኦሮሞው ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የመጅሊሱ ፕሬዘዳንት ሆኑ።

"…ዛሬ ግን የገረመኝ ግን ሁሉም ወሃቢስቶች ስለመውሊድ ትንፍሽ አላሉም። አህመዲን ጀበል እና ሙጂብ አሚኖ ኢሬቻንም መውሊድንም ምንም ላለማለት አልተነፈሱም። ዐቢይ አሕመድ ቀረ ላለመባል አስር መስመር ስለ መውሊድ ጣፍ ጣፍ አድርጓል። ሃሩን ሚዲያ የምን መውሊድ ብሎ ተሸብልሏል። የዐማራ ሚዲያ ስለ መውሊድ ደጋግሞ ሲጽፍ የሃጂ ቱፋ መጅሊስ በየ ምክንያቱ መግለጫ የሚሰጠው ግሩፕ ትንፍሽ አላለም። ያም ሆነ ይህ ግን እነ ሃጂ ሙፍቲ በአሉን በድምቀት አክብረዋል። ወሃቢ ግን ተናዷል። ምን ሆኖ ነው ግን?

"…ሃጂ ሙፍቲ ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች እንኳን ለመውሊዳችሁ አደረሳችሁ። እነ ወሃቢያ ቢጠሉትም ዛሬ ግን የዛሬውን መንዙማ ተጋበዙልኝ ሙስሊም ጓደኞቼ።

"…አሻማ…!
22.3K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ