Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 403.82K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 255

2022-10-06 14:05:48
"…በሃገር ውስጥ ስደት… መሄጃ፣ መድረሻውን ያጣ ምስኪን ህዝብ፣ አሁን ይሄን ሁሉ አራሽ ገበሬ፣ ሃገር አጥግቦ የሚያኖር ምስኪን አፈናቅለህ ስታበቃ ወደፊት እህል ሲወደድ ድንጋይ ትበላ እንደሁ እናያለን።

"…ይሄ ስደት በወለጋ ብቻ ተወስኖ የሚቀር የመሰለህ አዲስ አበቤም አይቀርልህም። እንዲያውም ከወዲሁ ደብረብርሃን እና ደብረ ማርቆስ ላይ ድንኳንና ዳስ ብታዘጋጅ መልካም ነው። አዲስ አበባ አላስገባም አሉን ብለህ ስታለቃቅስ የነበርክ ጎንደሬ፣ ጎጃሜና ወሎዬ፣ ሸዋዬም አይደለም አዲስ አበባ ባለህበትም በማሩህ።

"…የሚገርመው በፀጥታ፣ ያለምንም ተቃውሞ እና ጠያቂ ኮሽታ ሳይሰማ በራሱ በዐማራው መልካም ትብብር ከምድረ ኢትዮጵያ ገፅ እየጠፋ ያለ ነገድ ዐማራ ብቻ ነው። ሲያርዱት እንኳ ጎረቤቱ እንዳይደነግጥ የማይንፈራገጥ አስገራሚ ፍጡር ነው ዐማራ። ልጆቹ ለሆዳቸው ሲሉ የከደቱ፣ አሳልፈው የሰጡት፣ ምቾታቸው እንዳይጓደል የሚባክኑ መሪዎች ያሉት ዐማራ። ለምን ብሎ የሚጠይቅን የነቃን ዐማራ የሚያስር፣ የሚገድል የሚረሽን ዐማራ ፖሊስ፣ የሚገድል ዐማራ ሚኒሻ ያለው ብቸኛው ፍጡር ዐማራ ነው። ወይ ብአዴን?

"…በጊዜ ለምፍትሄው ካልታገልክና አደጋውን ከወዲሁ ካልቀለበስክ ለኦህዴድኦነግ ስላቃጠርክ፣ ስለተገረድክለትም፣ አሽቃባጭ ስለሆንክለትም፣ እግሩ ስር ተደፍተህ የጫማውን ሶል ስለላስክለት ብቻ ለጊዜው ፍርፋሪውን እየወረወረልህ አስብቶ ያርድሃል እንጂ አዝኖልህ አይምርህም። ይህን ዕወቅ። ከወዲሁ ካላስቆምከው ትፈናቀላለህ፣ ትታረዳለህ፣ እንዲህ እንደምታየው በጀማ ትሰደዳለህ። ይኸው ነው።

"…እየተሰደዳችሁ…!!
13.2K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 12:37:15
"…ከ4 ዓመት ወዲህ ሱሪ የታጠቀ ወንድ ያላጋጠማቸው፣ እንዲገጥማቸውም ያልተደረጉት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባሮች በትግል ሜዳ ላይ… ወይ ትግል…ትግል ብሎ ዝም እኮ ነው።
28.2K viewsedited  09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 11:47:26
"…ሳፋሪኮሞች እንደምን አደራችሁ…?

"…ስለ ህወሓት ብቻ እንጂ ስለ ዐማራ በኦሮሚያ በኦሮሞዎች መታረድ፣ መቃጠል፣ መሰደድ፣ መውደም መስማትም ማየትም የማትፈልጉ ገተቶች እንደምን አደራችሁ? …እኔን የሚገርመኝ ዐማራ ሆኖ አጎት አክስቱ በኦሮሚያ እየፀዳ እሱ ከኦነግም፣ ከኦህዴድም በላይ ሆኖ ሲያሽቃብጥና ሲገረድ ያዙኝ ልቀቁኝም ሲል ማየቱ ነው። ኧረ ኤዲያ…!!

"…እውነት ነው። ሃቅም ነው። የህወሓት መወገድ፣ መጽዳትም እጅግ ወሳኝና አስፈላጊ፣ ጠቃሚም ነው። የህወሓት መወገድ ለራሱ ለትግሬውም ለዐማራውም፣ ለአፋሩም በአጠቃላይ ለኢትዮጵያም ለምሥራቅ አፍሪካም ትልቅ እረፍት ነው። የህወሓት ሰንኮፏ ሳይቀር ተቆርጦ መጣል አለበት። በዚህ በወያኔ ቫይረስ ከተጠቁ ጥቂቶች በቀር ሁላችንም እንስማማለን። ምክንያቱም አሁን የምናየው የዘር ፖለቲካ ጦስ የዚህ ሁሉ ችግር ፈጣሪ መርዟ እርሷ ስለሆነች ማለት ነው። ነገር ግን ህወሓትን መዋጋቱ እንዳለ ሆኖ ከእግርህ ጀምሮ እየቆረጠ አንገትህ ጋር የደረሰውን የኦሮሞ አራጅ ቡድን በስሱ እንኳ ላለመቃወም ምንድነው አፍህን የለጎመህ? ምን እስክትሆን ነው ግን የምትጠብቀው?

"…በነገራችን ላይ በወለጋ የሚኖር የወሎ እስላም ዐማራ ለነጋሪ፣ ለዘር ሳይቀር ነው እንዲህ እያረዱት ያሉት። ስምዝርዝራቸውን ጭምር እለጥፍላችኋለሁ። የእስልምናው መጅሊስ ግን ዝም፣ ጭጭ፣ ትንፍሽ አይላትም። ጎንደር ቢሆን ግን ሁለት ግለሰቦች ቢጣሉ ቱርክን ሳይቀር መግለጫ ያስወጧት ነበር። በወለጋ ግን ምንም። ትንፍሽ የለም።

"…ወዳጄ አንተ አዲስ አበባ ላይ በሚያሳዩህ የማትበላው ፕሮጀክት ጨፍር። እልልል ብለህ አሽቃብጥ። ከኋላ ግን ዜናው እንኳ እንዳይወጣ አድርገው አፍነው ይዘው እንዲህ እያረዱህ ነው። እየቀረቀሩልህም ነው። እያፀዱህም ነው። ሰምተሃል…!!

"…ቆይቼ ከቪድዮ ጋር እመለሳለሁ…!!
35.6K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 21:32:05
"…አዳዲስ አራጆች ተመርቀዋል…!!

• ማነህ ኢ-መደበኛ ሰምተሃል…!!

• በነገራችን ላይ የምሥራቅ ሸዋን ዐማራ የሚያጸዳው የኦነግ ሽሜ ሠራዊት በብሳት ምሥራቅ ሸዋ ሰፍሯል። ከአውራ ጎዳና ጀምሮ እስከ ምንጃር የጽዳት ሥራውን እንዲሠሩ መመሪያ እንደወረደላቸውም ተሰምቷል። እንዲያውም ዛሬ የት እንደሚሄድ ትእዛዝ አልወረደለትም እንጂ ስፍር ቁጥር የሌለው የኦሮሚያ ልዩ ሓይል ናዝሬት ከተማ ተከማችቶ በተጠንቀቅ ቆሟል። የሰሜን ሸዋ ነፍጠኛ እንደባለፈው ጊዜ ከጠነከረ ልዩኃይሉ፣ ፌደራል ፖሊሱና መከላከያው ድጋፍ እንዲሰጥ እንደተዘጋጀ ነው የሚሰማው።

"…ሰሜን ሸዋ ሰምተሃል…!!
66.5K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 18:57:51
ባለ ቀይ ቆቦ አባ ገዳ ፦

"…ቀሲስ በላይ መኮንን ይባላል። አባ ገዳም ነው። ምድቡ የምዕራብ ሸዋው የኦህዴድ ቡድን አባል ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ነው።

ባለ ነጭ እና በላ ቡናማው ቆቡ

"…ቄስ በዳሳ ቶሎሳ ይባላል። የወለጋው ኦነግ
የቤተክህነቱ ክንፍ ነው። በጠቅላይ ቤተክህነት የሊቃውንት ጉባኤ ክፍል ሹመኛም ነው። የሊቃውንት ጉባኤ።

• በላይንም በዳሳንም ለዚህ ሹመት ያበቃቸው የኦሮሚያ ቤተ ክህነት መሥራቾችና ሓላፊዎችም መሆናቸው ነው። በድርድሩ ወቅት ቤተ ክርስቲያኒቱን መከፋፈሉን ተዉት እናም ሥልጣንም፣ ገንዘብም ውሰዱ ተብለው የተሰጣቸው ቦታ ነው።

"…እነዚህን አሁን ለማውገዝ አይሞከርም። ኢንዴዢያ ነው።
75.4K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 18:21:51
አትዋሽ…!!

"…የጦርነት ዘገባውን እንኳ እሺ ለምደነዋል። እንዲህ አይነቱን ቀደዳ ግን ተወው ወንድሜ። ደግሞ በሱማሌም ባህል፣ በኢስላምም ውሸት ሃራም ነው የሚባለው። አንተ ደግሞ ከሱማሌም፣ ከኢስላምም በላይ የዩኒቨርሲቲ መምህር ነህ። ሌላው ቢቀር ተማሪዎቼ ይታዘቡኛልስ አትልም? መስፍን ፈይሳ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ቶማስ ጃጃው እንኳን እሺ እንጀራቸው ነው። ሀ ገደሉ ይበዛቸዋል የሚሉ መተርጉማንም አሉ። በዚያ ላይ ሌለው ይቅር ትልቅ ሰው አይደለህ እንዴ? ተው እንጂ…! የምን ዝም ብሎ መበጥረቅ ነው?

• ለማንኛውም አረጋዊው ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ፍርድ ቤትም አልቀረቡም። ከእስርም አልተፈቱም። ይኸው ነው። (ደግሞ ዝም ብዬ አይደለም አልተፈቱም የምልህ እኔው ራሴ ክብርት ባለቤታቸው ወ/ሮ ፀጋ ጋር ደውዬ ያረጋገጥኩትን ነው።) እኔ ከጀርመን ያረጋገጥኩትን አንተ ከሸገር እዚያው ማረጋገጥ ለምን አቃተህ። የሀሰት ዜናስ ምን ይጠቅማል?
75.1K viewsedited  15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 17:32:31
ጨቋኟ ዐማራ…!!

"…መልካም የትምህርት ዘመን …!!
70.3K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 15:57:01
"…ሹርቤዎቹ ኦነግ ሽሜዎች ደሞዝም ቢሆን በወቅቱ ጊዜውን ጠብቆ ነው የሚከፈላቸው። ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፈረንካው ሰንዱቅ ቁልፍ ያዥ ሶዬ ምስጋና ይግባውና አፍታም አያቆይ፣ ሰኮንድም አያሳልፍባቸውም በጊዜ ነው ደሞዝ በሰዓቱ የሚከፍላቸው። ሂኢ…

"…ማነህ አንተ ኢ-መደበኛ እያየህ ነው አይደል…?
73.7K viewsedited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 14:18:13 Zemedkun Bekele (ዘመዴ) pinned «"…ተመልከት ወያኔ ታንክ አላት። መትረየስ፣ ዲሽቃ፣ ዙ 23፣ ቢኤም ሁላ አላት። አንድም ክልል ወያኔ ያላትን የለውም። ወያኔ ሽፍታም፣ መንግሥትም በነበረች ጊዜ የዘረፈችውንም፣ የቀበረችውንም መሣሪያ ቆፍራ አውጥታ ትጠቀማለች። በምርኮ ሰበብ የሚሄድላት፣ በአየር በእርዳታ ሰበብ በመኪና የሚሄድላት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። መሳሪያ ዘጭ ናት። ቢያልቅባት ተዋጊና ተተኳሽ እንጂ የመተኮሻ መሳሪያው ነፍ ነው ያላት።…»
11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 14:17:48 "…ተመልከት ወያኔ ታንክ አላት። መትረየስ፣ ዲሽቃ፣ ዙ 23፣ ቢኤም ሁላ አላት። አንድም ክልል ወያኔ ያላትን የለውም። ወያኔ ሽፍታም፣ መንግሥትም በነበረች ጊዜ የዘረፈችውንም፣ የቀበረችውንም መሣሪያ ቆፍራ አውጥታ ትጠቀማለች። በምርኮ ሰበብ የሚሄድላት፣ በአየር በእርዳታ ሰበብ በመኪና የሚሄድላት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። መሳሪያ ዘጭ ናት። ቢያልቅባት ተዋጊና ተተኳሽ እንጂ የመተኮሻ መሳሪያው ነፍ ነው ያላት። የሌሎቹ ክልል ልዩ ኃይሎች ከክላሽ በቀር፣ ከፍ ካለ ብሬን ከመተኮስ በቀር ሌላ ችሎታ የላቸውም። እንዲኖራቸውም አልተደረገም። ህወሓት የሃገሪቱን መከላከያ ትመራ በነበረ ጊዜ ዐማራውን ከክላሽ በቀር ከባድ መሣሪያ እንዲሰለጥን አላደረገችውም። ትግሬ ትግሬውን መርጣ ነው በኢትዮጵያ ሀብት ከባድ መሣሪያ አተኳኮስ ስታሠለጥን የኖረችው። ለዚህ ነው ትግሬዎቹ በውጊያ ወቅት አንድ ታንክ ከኢትዮጵያ ቢማርኩ ወዲያው ጥቅም ላይ የሚያውሉት። ፋኖም ሆነ የዐማራ ልዩኃይል ከህወሓት ታንክ ቢማርክ የታንኩን አይን አይኑን ከማየት በቀር ምንም ሊያደርጉት አይችልም። አየህ ለመደራደር እንኳ እንዲህ አቅም ሊኖርህ ይገባል። ዓለም አቅም ላለው ነው የምታጎበድደው። ምላስ ብቻውን አቅም አይሆንም። ሆኖም አያውቅም።

አቤት እስከአሁን ስንትና ስንት ወጣት ከዚህም፣ ከዚያም አልቆ ይሆን? …ብአዴን ያው እንደተለመደው ሰሞኑን የተደፈሩ የዐማራ ሴቶች፣ እናቶችና ወንዶችን በአሚኮ በኩል ሲያዥጎደጉድልን ይከርማል። የፈረሱ፣ የተቃጠሉ፣ የወደሙ ጤና ጣቢያዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ድልድዮች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ወዘተረፈ ሲያዥጎደጉድልን ይከርማል። መጀመሪያ እንዳይፈጸም ማድረግ ሲገባው ከሆነ በኋላ የበለጠ ህዝቡን ሲያቆስልበት ይኖራል።

"…ጦርነቱ መቆሙ አልተሰማም። ሦስተኛ ዙር ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። እስከአሁን የተኩስ አቁም ስምምነት አልተፈረመም። ሆኖም ግን በጦርነት ውስጥ ያሉት  የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር፣ (ትህነግ) በደቡብ አፍሪካ ሊደራደሩ መሆኑ በዛሬው ዕለት ተነግሯል። እናም አሁን ድርድሩ ይቀጥላል። መንግሥታችንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እደራደራለሁ ማለቱን ገልጿል። አደራዳሪዎቹና የመደራደሪያ አዳራሹም ተወልውሎ፣ ወይራ ጢሶበት፣ ጡንጂትና አሪቲ ቄጤማም ተጎዝግዞበት፣ ሺቶም ተርከፍክፎበት እየጠበቃቸው ነው። ድርድሩን ህወሓቶች በሚጠሉት የቀድሞው የናይጄርያው ፕሬዘዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እና ህወሓቶች በሚወዱት በቀድሞው የኬኒያ ፕሬዘዳንት በኡሁሩ ኬኒያታና ፋምዚሌ ምላምቦ ይመራል ተብሏል፡፡ ከኢትዮጵያ ወገን በዚህ ድርድር ላይ የህወሓት የበኩር ልጆች አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙ የሚጠበቅ ሲሆን የደመቀና የሬድዋን የቀድሞ አለቆችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ህወሓት ድርድሩን በተመለከተ እስከአሁን ያለችው ነገር የለም። ከህወሓት በኩል ከተንቤን በረሃ ወጥቶ ደቡብ አፍሪካ ለድርድር የሚሄድ ይኑር አይኑር የታወቀም ነገር የለም። ኦነግ ግን ለድርድር አልተጋበዘም። በምሥራቅ ወለጋ ሰባት ወረዳዎችን መቆጣጠሩ የተሰማው የኦነግ ሽሜን ንቀውት ይሁን አይሁን ለድርድር ያልጠሩት የታወቀ ነገር የለም። ህወሓት እንደሁ የገበረችውን የትግሬ ወጣት ደም ገብራ፣ ከዐማራ የዘረፈችውን በአህያም፣ በግመልም፣ በኮንኮላታም ጭና እየተወገረችም በለው እያፈገፈገች ወደ ጎሬዋ እየተመለሰች መሆኑ እውን ሆኗል። አሚኮም በቡድን የተደፈሩ የዐማራ ሴቶችን፣ የተገደሉ ዐማሮችን፣ የተዘረፉ፣ የተቃጠሉ፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እያሳየ እዬዬውን ይጀምራል። የደቡብ አፍሪቃው ድርድር ካልተሳካ ግን ያው እንደተለመደው ለማይቀረው ለአራተኛው ዙር ፍስፍስ ደግሞ ከወዲሁ መዘጋጀት ነው።

"…እየተደራደርን እንፈሳፈሳለን…!!
14.1K viewsedited  11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ