Get Mystery Box with random crypto!

'…በሃገር ውስጥ ስደት… መሄጃ፣ መድረሻውን ያጣ ምስኪን ህዝብ፣ አሁን ይሄን ሁሉ አራሽ ገበሬ፣ ሃ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በሃገር ውስጥ ስደት… መሄጃ፣ መድረሻውን ያጣ ምስኪን ህዝብ፣ አሁን ይሄን ሁሉ አራሽ ገበሬ፣ ሃገር አጥግቦ የሚያኖር ምስኪን አፈናቅለህ ስታበቃ ወደፊት እህል ሲወደድ ድንጋይ ትበላ እንደሁ እናያለን።

"…ይሄ ስደት በወለጋ ብቻ ተወስኖ የሚቀር የመሰለህ አዲስ አበቤም አይቀርልህም። እንዲያውም ከወዲሁ ደብረብርሃን እና ደብረ ማርቆስ ላይ ድንኳንና ዳስ ብታዘጋጅ መልካም ነው። አዲስ አበባ አላስገባም አሉን ብለህ ስታለቃቅስ የነበርክ ጎንደሬ፣ ጎጃሜና ወሎዬ፣ ሸዋዬም አይደለም አዲስ አበባ ባለህበትም በማሩህ።

"…የሚገርመው በፀጥታ፣ ያለምንም ተቃውሞ እና ጠያቂ ኮሽታ ሳይሰማ በራሱ በዐማራው መልካም ትብብር ከምድረ ኢትዮጵያ ገፅ እየጠፋ ያለ ነገድ ዐማራ ብቻ ነው። ሲያርዱት እንኳ ጎረቤቱ እንዳይደነግጥ የማይንፈራገጥ አስገራሚ ፍጡር ነው ዐማራ። ልጆቹ ለሆዳቸው ሲሉ የከደቱ፣ አሳልፈው የሰጡት፣ ምቾታቸው እንዳይጓደል የሚባክኑ መሪዎች ያሉት ዐማራ። ለምን ብሎ የሚጠይቅን የነቃን ዐማራ የሚያስር፣ የሚገድል የሚረሽን ዐማራ ፖሊስ፣ የሚገድል ዐማራ ሚኒሻ ያለው ብቸኛው ፍጡር ዐማራ ነው። ወይ ብአዴን?

"…በጊዜ ለምፍትሄው ካልታገልክና አደጋውን ከወዲሁ ካልቀለበስክ ለኦህዴድኦነግ ስላቃጠርክ፣ ስለተገረድክለትም፣ አሽቃባጭ ስለሆንክለትም፣ እግሩ ስር ተደፍተህ የጫማውን ሶል ስለላስክለት ብቻ ለጊዜው ፍርፋሪውን እየወረወረልህ አስብቶ ያርድሃል እንጂ አዝኖልህ አይምርህም። ይህን ዕወቅ። ከወዲሁ ካላስቆምከው ትፈናቀላለህ፣ ትታረዳለህ፣ እንዲህ እንደምታየው በጀማ ትሰደዳለህ። ይኸው ነው።

"…እየተሰደዳችሁ…!!