Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 403.82K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 256

2022-10-05 14:17:48 "…ተጠባቂዋ ድርድር መጥታለች…!!

"…አስቀድመን እንደተናገርነው በመጨረሻም በጉጉት የምትጠበቀዋ የድርድር ዜና አሁን መጥታለች። ድርድር ሁልጊዜ ደግሞም የሚጠበቅ ነው። ሁለት ጉልበት ያላቸው ኃይላት መጀመሪያ ነገር ተፈላልገው በግልፅ ይፈሳፈሳሉ። ይፈሳፈሱ ይፈሳፈሱና ከዚያ መጨረሻ ላይ ድርድር የሚባል ጊዜ መግዣ የማምለጫ የወንድ በር ከች ያደርጉና ለማምለጥ ይሞክራሉ። ድርድር ለጤናማ ኃይላት ግሩም ነገር ነው። ድርድር ለወያኔ የማምለጫ፣ የጊዜ መግዣ ካርታዋ ነው። እንጂ ድርድርማ አስፈላጊና ቅዱስ ሃሳብ ነው።

"…ከወያኔ ጋር ድርድር በቦክስ ስፖርት ላይ ለእረፍት እንደሚደወለው ደወል ያለ ማለት ነው። ትፈሳፈስና እረፍት እንድትወስድ ይደወላል። ተደራድረህ ግን አይደለም። እረፍት ነው። በቦክስ ዘርረኸው ቀበቶህን ካላጠለቅ እንዲሁ እያረፍክ ስትቀጣቀጥ መዋልህ ነው። ህወሓትም እንደዚያው። ህወሓት ካልተወገደች ትግሬም፣ ዐማራም እረፍት አይኖራቸውም። ለ4ተኛ ዙር ይቀጣቀጣሉ። እናም የድርድር ሃሳቡ የመጣው ከማነው። ድርድሩ የሚጠቅመውስ ማንን ነው? ከዚህም ከዚያም የትየለሌ ነፍሳት ከጠፉ፣ ወደ ኋላ መቶ ዓመት የሚያሽቀነጥር የኢኮኖሚ ድቀት ከተፈጠመ በኋላ፣ የገበሬው ቤት ከፈረሰ፣ ከብት እና አዝመራው ከወደመ፣ የልጆቹን፣ የሚስቱን፣ የራሱንም ሞራል እንኩትኩቱን ካወጡት በኋላ፣ መሰረተ ልማቶች በሙሉ ከወደሙ በኋላ፣ አሸናፊው ሳይታወቅ ድርድር ደስ ባይልም ከተሳከ ለህዝቡም ሰላም ካስገኘ ጥሩ ነው። በሁለቱ ህዝብ ማለትም በትግሬና በዐማራው፣ በትግሬውና በአፋሩ መካከል ቋሚ የማይሻር የቂም በቀል ሃውልት ከተከተሉ በኋላ ነው እንግዲህ መጨረሻ ላይ ትንፋሽ መሰብሰቢያዋ ድርድር ተብዬዋ ካርታ ተስባ የማረፊያ፣ የጊዜ መግዣ ሆና ከች ብላ የምትመጣው።

"…ባለፈው ኢትዮጵያና ኤርትራ ተፈሳፈሱ። ብዙ መቶ ሺ ወጣቶችም ጭዳ ሆነው ከዚህም ከዚያም እንደቅጠል ረገፉ፣ መሰረተ ልማቱም ከወደመ፣ የቂም በቀል ሃውልትም በትግሬና በኤርትራ መካከል ከተተከለ በኋላ አሸናፊው የኢትዮጵያ ኃይል ተንኳሽ የተባለውን የሻአቢያ ኃይል ለማጥፋት በፈንጂ ላይ ተረማምዶ አስመራ ሊገባ ሲል በኢትዮጵያ የኤርትራ ተወካዮቹ እነ መለስ ዜናዊ እና አቦይ ስብሃት ነጋ ሠራዊቱን ባሬንቱ ላይ ታክል ገብተው አስቆሙት። ከአስመራ ፈርጥጦ ምጽዋ ገብቶ ለነበረው ለኢሳያስም በነፍስ ደረሱለት። አልጄሪያ ድረስ ሩጠው ተሯሩጠው እያለከለኩም ተደራደሩ፣ ከኢሳያስ ጋር ፎቶ ተነሥቶ ተጨባበጡም። ነገርየው በዚያው ያበቃም መሠለ። በዚህ የተነሣ ህወሓት ለሁለት ተሰነጠቀች። ሻአቢያም 20 ዓመት የሆዱን በሆዱ ይዞ፣ ቂም ቋጥሮ፣ ታግሶ ምቹ ጊዜ ሲጠብቅ፣ እንደ ነፍሰ ጡር ቀን ሲቆጥር ከርሞ፣ ዐቢይ የሚባል አድራሽ ፈረስ፣ ታዛዥ፣ እንደልቡ የሆነ ሰው ሲያገኝ ይኸው ትግራይን ተበቀላት። በሰማይ በምድርም አረሳት። አሁንም እየተበቀላት ነው። በቀሉም ይቀጥላል። ጥፋቱ የማነው ካልከኝ ግን መልሴ የራሷ የህወሓት ነው። አለቀ።

"…አሁንም እንደዚያ ነው። ህወሓት ዐማራ ክልል ገብታ ስትገድልም፣ ስትሞትም ፀጥ ይባልና፣ ሂዊ ሲደክማት፣ ስንቅ ሲያጥራት፣ ተተኳሽ ሲያልቅባት፣ ወደ ጎሬዋ መሸሽ ስትጀምር አጅሪት አማሪካ ከጎሬዋ ትወጣለች። ነጠላዋንም ዘቅዝቃ የስለት ልጇን ለማዳን ዋይ፣ ዋይ እያለች በአፍሪካ ምድር ትኳትናለች። ለሞተው ትግሬ ሳይሆን የሚሞት ለሚመስላት ህወሓት በነፍስ ለመድረስ ትባክናለች። ድርድር፣ ድርድር አሁኑኑ ትላለች። እምቢ ካልሽ ኢትዮጵያ ሆይ እንደ ሩሲያ፣ እንደ ኢራን በማዕቀብ ሽባ አደርግሻለሁ ትላለች። ከዚያ የኢትዮጵያ ጦር ባለበት እንዲቆም ዐቢይ አህመድ ያዛል። ከዚያም ህወሓት ትተርፋለች። መልሳም ከጎሬዋ ሆና ታቅዳለች።  የጎደላትን ሁሉ ታሟላለች። ነዳጅ፣ መሣሪያ፣ ምግብ፣ ተሽከርካሪ፣ መድኃኒት ሁሉ በአየር፣ በምድር ይገባላታል። አዲስ ተዋጊም ትመለምላለች። ታሰለጥናለች፣ ታስታጥቅና ለ4ተኛ ዘሩ የደቀቀውን የዋግ እና የራያ ዐማራን እንኩትኩቱን ለማውጣት ትመጣለች። የልቧን ፈጽማ ስንቅ ሲያልቅባት እንደገና ድርድር ትላለች። ተጎጂዎቹ ግን ዐማራና ትግሬዎቹ ናቸው። ኦሮሙማ ምን ቸገረው?

"…ከሁለቱም ከወያኔም፣ ከብልፅግናም አመራሮች እስከአሁን የሚጎዳ፣ የተጎዳም ሰው የለም። ሁለቱም እንዳማረባቸው አሉ። ይኖራሉም። ድሮስ አባትና ልጅ ምን ይሆናሉ? እንዳማረባቸውም ይኖራሉ። እምሽቅ የሚለው ህዝቡ ነው። ካድሬ ምን አለበት? ህወሓት ሻአቢያን ያላጠፋችው መለስና እነ ስብሃት በግማሽ ጎን ኤርትራውያን ስለነበሩ ነበር። ዐቢይ አሕመድም ህወሓትን የማያጠፋት የትግሬና የዐማራ ሰላም ለታላቋ ኦሮሚያ ግንባታ እንቅፋት ስለሚሆን መፈሳፈስ አለባቸው። ማረፍ የለባቸውም። በቂም በቀል እስከወዲያኛው መነካከስ አለባቸው ብሎ ስለሚያምን ነው የሚሉም አሉ። ህወሓት እያለች አይሆንም እንጂ ሂኢ እና ታዲያ ትግሬና ዐማራ ታርቀውና ተስማምተው በአፍጢሙ ይድፉት እንዴ? ሞኝህን ፈልግ።

"…በጦርነቱ የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ይገብራል። የዐማራም እንደዚያው። ዐማራው ግን ልጆቹን ብቻ አይደለም የሚገብረው። ሰራዊቱን ቀላቢም እሱ ነው። በሬ፣ ፍየል፣ በግ፣ ዳቦ፣ እንጀራ፣ ቂጣ፣ ቆሎ፣ ዶሮ፣ እርጎ፣ ወተት፣ ጠላ እና ጠጅ ሳይቀር ነው ለጥምር ጦሩ የሚያቀርበው። ምክንያቱም ህወሓት ስትመጣም ለምትበላው፣ ለምትዘርፈው ቢያንስ መከላከያዎቼ ይብሉት፣ በልተውም ያድኑኝ፣ ያትርፉኝ ከሚል ፍላጎት ነው። ተገቢም ነው።

"…መቼም ይሁን መቼም ህወሓት የምትባለዋ ካንሰር በዚያ ምድር በህይወት እያለች ትግሬም እረፍት አያገኝም። ዐማራም እረፍት አያገኝም። ህወሓት፣ ብአዴንና ኦህዴድኦነግ በዚያች ምድር እስካሉ ድረስ እረፍትና ሰላምን እንዳታስቧት። መጀመሪያ እነዚህ ሦስቱ ሰንኮፎች ተራበተራም ቢሆን መውለቅ፣ ጋንግሪኖቹም መቆረጥ አለባቸው። አለበለዚያ ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ እያልክ ስትማቅቅ ትኖራለህ እንጂ ሦስቱ ኢቦላዎች እያሉ ስለጤንነትህ እንዳታስባት።

"…ህወሓት መድኃኒት፣ ቀለብ፣ መሣሪያ እንዲገባላት እረፍት እንደምትፈልገው ሁሉ ዐቢይ አሕመድም ተንኮል ሴራው እንዳለ ሆኖ ቁጢ ስለጠረረበት ጥቂት ማረፍ ይፈልጋል። ትናንት እንኳ ያን የመሰለ ግዙፍ የሳይንስ ሙዚየም ካስመረቀ በኋላ እንደተለመደው ሻይ ቡና እንኳን አላዘጋጀም። በ4ዓመት ጉዞው ውስጥ ያልታየ አስደናቂ ክስተት ሆኖ ተመዝግቦ አልፏል። የሆነች ትንሽዬ ድልድይ መርቆ ድል ያለ ግብዣ ያደርግ የነበረው ሶዬ ትናንት ግን አልቻለም። "ማዕድ ማጋራት" የሚል ቅፅል የሚሰጠው የብልፅግናን ድል ያለ የተለመደ ግብዣም አላደረገም። መቼም ግብዣ የለመደ ካድሬ ትናንት ሳያብድ አይቀርም። የዐቢይ ያለመደገስ ግን ምክንያቱ ሌላ ነው። ቁጢ፣ ፈረንካ የሚባል በባንኩ ካዝና ውስጥ ስለሌለ ነው። ያለውንም ለኢሬቻ አውጥቶ ኢሬቻውን አብልቶታል። እናም እሱም ትንሽ ዶላር መሸቀል አለበት። ለምኖም ዕቃ ሽጦም ቢሆን ዶላር ፈረንካ መያዝ አለበት። አየህ ድርድሩ ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለእሱም በጣም አስፈላጊው ነው። ለዐቢይ አሕመድ።
13.5K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 14:03:13
"…የማትቀረዋ፣ ተጠባቂዋ ድርድሯ ደግሞ መጣች። ከተፍ አለች። … ከትግሬም፣ ከዐማራም፣ ከአፋርም፣ ከጥምር ጦሩም መቶ ሺዎች እንደቅጠል ከረገፉ በኋላ አጅሪት "ድርድር" አበጥራ ዳግም ተከስታለች። ነገር ግን ከእረፍት መልስ 4ተኛ ዙር ፍስፍሱ ይቀጥል ይሆን…? የተሰማኝን ከታች ጽፌያለሁ። ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንኬ ገብታችሁ አንብቡልኝ።



http://t.me/ZemedkunBekeleZ
19.2K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 22:36:19
የ40 ቀን ዕድሉ ወይስ…?

"…ኧረ ወይኔ… እያሉ ሴቶቹ እያለቀሱ የዐማራ ወንድ ወንዱ እየተመረጠ እንዲህ በጅምላ መረሸኑ፣ በጅምላም መቀበሩ የዐማራው ዕጣ ፈንታው ከሆነ ሰንብቷል። በጦርነት ላይ የሚያልቀው እኮ እሺ እሱ አንድፊቱን ስም አለው። ጦርነት ነው። የሚያጨሰው እኮ በቤቱ የተቀመጠን ሰላማዊ ዜጋ ያለከልካይ በጠራራ ፀሐይ መረሸኑ ነው።

"…ይሄን ግፍ ለመናገር እንኳ ዐማራው ይፈራል። ቢያንስ ሌላው ይቅር አትግደሉኝ ብሎ መጠየቅ ምን ያስፈራል…? ይሄ በኦሮሚያ በምሥራቅ ሸዋ የሚጸዳው የዐማራና የሀዲያ ነገድ ነው። ኦሮሞ ዐማራን ብቻ ገድሎ፣ አርዶ የሚያቆም መስሎት ነበር አዳሜ። በየተራ ይመጡልሃል ጠብቅ።

"…በሰሜንም በራያ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። ከዐማራ፣ ከሚኒሻው፣ ከልዩ ኃይሉ፣ ከመከላከያውም ሙትና ቁስለኛው እንደቀጠለ ነው። የትግራይ ወጣቶችም የሬሳ ክምር በራያ ምድር በሚዘገንን መልኩ እንደቀጠለ ነው። ፎቶም፣ ቪድዮውንም ማየት ያጥወለውላል።

• ይህ በእንዲህ እንዳለ የሳይንስ ሙዚየም በአዲስ አበባ ተመርቋል። የገበታ ማጋራት ግን አልነበረውም። ኦህዴድ ለመጀመሪያ ጊዜ የምሳ ግብዣ ረሳ። ቁጢው ጠረረ ወይስ ረሱት?

"…ብቻ የሟቾቹን ነፍስ ይማር…!!
25.5K viewsedited  19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 21:31:19
ወለጋ ነው።

"…ባለፈው ሰኔ ወር ከመከላከያ አንድ ሻለቃ ኃይል ወደ ወለጋ ሂዶ በሴራ ይበላል። ከዚያ ሌላ ተጨማሪ ኃይል በድጋሚ ወደ ወለጋ እንዲሄድ ሲጠየቅ የመኮንኑ መልስ "መቀሌ ግባ በሉኝ ዛሬ እነሳለሁ። ወለጋ ግን ሄጄ ቁማር አልበላም።" ብሎ እርፍ። ይሞታል እንዴ?

"…ነውጡ መጣ ተብሎ የኦነጉ ዐቢይ አሕመድ የፌደራል ፖሊስ አባላትን በሪፎርም ሰበብ ማባረር ፈለገ። ነገር ግን እሱ ነገር አደጋ ይኖረዋል በማለት ሌላ ዘዴ ተጠቀመ። የፌደራል ፖሊስ ውስጥ ያሉ ነፍስ ያላቸው በተለይ ዐማራና ኦርቶዶክሱን ለምን አናጸዳውም ብለው ይመክራሉ አሉ። መከሩናም ኦሮሞው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ደመላሽ ኃላፊነቱን ወስዶ በቀጥታ ወደ ሥራ ይገባል። ከዚያም 20 ሺ ነፍስ ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ተለይተው ይመረጣሉ። ይመረጡናም ወደ ወለጋ ለእርድ ይሄዱ ዘንድ ትእዛዝ ይቀበላሉ።

"…ሟቾቹ የፌደራል ፖሊሶች ዝም ብለው ብቻ አይደለም የሚሞቱት። ዘመናዊ መሣሪያ ታጥቀው፣ ስንቅና ትጥቅም አሟልተው ነው ወደ ወለጋ የተላኩት። ወለጋ ሲደርሱ ኦነግሽሜ ደፈጣ ይዞ እንዲጠብቅ፣ የኦሮሚያ ብልፅግና መረጃ እንዲያሳስት፣ ፍርዬ ቴሌን፣ መብራት ኃይልም ባልቦላውን እንዲያጠፋ አደረጉ። አደረጉናም 20ሺ የፌደራል ፖሊስ እምሽቅ አድርገው ከቢሮም፣ ከሰፈርም አጸዱት። ኦነግ ሸኔም በሰበቡ 20ሺ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ቀረበለት። ዐማራም ከፌደራል ፖሊስ ፀዳ። ቢባረር፣ ከሥራ ቢቀነስ ስጋት ይሆን የነበረው ፌደራል ፖሊስ በዘዴ አስወገዱት። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ይሄም አይደል? ሙሉ ረጅሙን ቪድዮው በመረጃ ቲቪ አቀርብላችኋለሁ። እስከዚያው ይህቺን ቀምሳችሁ ተኙ።

"…ዐማራ አሁንም መከላከያን በገፍ እየተቀላቀለ ነው። መልካም ነው ሱማሌ ሄዶ ከአልሸባብ ጋር ተዋግቶ መሞት ግን እንዴት ያለ ጽድቅ ነው መሰላችሁ።

•ነፍስ ይማር…!
13.8K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 20:38:08
"…ጠዋት ፌደራል ፎሊስ… ከሰአት በኋላ ደግሞ መከላከያ ለኦነግ ሽሜዎቹ ኮንኮላታ አስረክበዋቸዋል። የፌደራል ፎሊሱ አዛዥ ኦቦ ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ሲሆኑ የመከላከያው ኢታማዦር ሹሙ ደግሞ ማረሻል ብርሃኑ ጁላ ናቸው።

"…ቪቫ እናት ሃገር ኦሮጵያ… !!
29.5K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 20:04:24
"…ጦርነት
37.0K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 17:29:58
"…ኦነግሽሜዎቹ ከ500 በላይ ንፁሐን የዐማራ ተወላጆችን ከረሸኑ በኋላ አሁን የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤቱን በሰላም ተቆጣጥረውታል። ወረዳው ኦነግሽሜዎቹ ከመምጣታቸው በፊት ዐማሮቹን መሣሪያቸውን ገፍፎ፣ ገሚሱን ጀግና ወንድ ዘብጥያ ከትቶ ነበር የጠበቃቸው። ኦነግ ሸኔዎቹም በመጡ ጊዜ የገጠማቸው መከላከል አልነበረም። የወረዳዎቹ አመራሮችም ወደ ነቀምት የሸሹ ሲሆን፣ በእስር ቤት ከቆለፉባቸው 100 ያህሉ ዐማሮች በእዚያው በወኅኒ ቤት ሳሉ በተቆለፈው እስርቤት ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ አቃጥለው ዐመድ እንዳደረጉአቸውም ተሰምቷል።

"…ጥምር ጡሩ ግን በራያ ግንባር፣ በድሮን፣ በታንክ፣ በመድፍ፣ በዲሽቃ፣ በሞርታርና በጀት የታገዘ ጦርነት እያካሄደ ነው። በትግሬና በዐማራ መካከል ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው።

"…ማነህ ባለሳምንት…?
52.8K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 17:02:49
"…ኧረ ጎበዝ ይሄ ነገር ያ የተባለው ጥቁሩ ክላሽ አይመስለኝም። የተለየ ይመስላል። መከላከያው ራሱ ይሄ መሣሪያ ያለው አይመስለኝም። በጭራሽ ከምር ጥቁሩ ወሴው የያዘው ጥቁሩን ክላሽማ አይመስለኝም።

• ችግሩ ከወንድ ጋር አይገጥሙበትም። ሴት፣ ህጻን፣ ሽማግሌ፣ ገበሬ ለመረሸን ነው የሚጠቀሙበት። ዐማራን ለማጽዳት ብቻ። ለእሱ ደግሞ አርጩሜስ መች አነሰ። ህጻን ለመግደል ጥፊስ አይበቃም…? አይ ኦሮሞ …አቤት ዘመን ሲለወጥ፣ ቀን ሲመጣ በእነዚህ አረመኔዎች ጦስ የምትከፍለው ዕዳ ይተኛል።

"…መሣሪያው ግን ጥቁር ክላሽ አይመስለኝም።
53.5K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 16:35:35
"…ወይ ዕዳችን ምንጉድ ነው ግን በማርያም…? ወሴው በቃ አይተንሃል ውረድ ከሶላሩ ነው ከጣሪያው ላይ… የመድኃኔዓለም ያለህ… አይዪዪእ…!! ኧረኤዲያ…
54.8K viewsedited  13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 15:52:52
"…እኔምለው ይሄ መከላከያ ብቻ እጅ የሚገኘው "ጥቁሩ ክላሽ" እንዴት እነ ኦነግሽሜ እጅ ገባ ግን…? ጥቁሩ ክላሽ ኦሮሚያ ላይ ነጭ ተብሎ ይሆን እንዴ የሚጠራው? ኦነግሸኔስ ከቆሰለ መከላከያ ነጥቆ ነው የታጠቀው ወይስ…

"…ሃይገርሚላችሁም…?
58.3K views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ