Get Mystery Box with random crypto!

ወለጋ ነው። '…ባለፈው ሰኔ ወር ከመከላከያ አንድ ሻለቃ ኃይል ወደ ወለጋ ሂዶ በሴራ ይበላል። ከ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ወለጋ ነው።

"…ባለፈው ሰኔ ወር ከመከላከያ አንድ ሻለቃ ኃይል ወደ ወለጋ ሂዶ በሴራ ይበላል። ከዚያ ሌላ ተጨማሪ ኃይል በድጋሚ ወደ ወለጋ እንዲሄድ ሲጠየቅ የመኮንኑ መልስ "መቀሌ ግባ በሉኝ ዛሬ እነሳለሁ። ወለጋ ግን ሄጄ ቁማር አልበላም።" ብሎ እርፍ። ይሞታል እንዴ?

"…ነውጡ መጣ ተብሎ የኦነጉ ዐቢይ አሕመድ የፌደራል ፖሊስ አባላትን በሪፎርም ሰበብ ማባረር ፈለገ። ነገር ግን እሱ ነገር አደጋ ይኖረዋል በማለት ሌላ ዘዴ ተጠቀመ። የፌደራል ፖሊስ ውስጥ ያሉ ነፍስ ያላቸው በተለይ ዐማራና ኦርቶዶክሱን ለምን አናጸዳውም ብለው ይመክራሉ አሉ። መከሩናም ኦሮሞው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ደመላሽ ኃላፊነቱን ወስዶ በቀጥታ ወደ ሥራ ይገባል። ከዚያም 20 ሺ ነፍስ ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ተለይተው ይመረጣሉ። ይመረጡናም ወደ ወለጋ ለእርድ ይሄዱ ዘንድ ትእዛዝ ይቀበላሉ።

"…ሟቾቹ የፌደራል ፖሊሶች ዝም ብለው ብቻ አይደለም የሚሞቱት። ዘመናዊ መሣሪያ ታጥቀው፣ ስንቅና ትጥቅም አሟልተው ነው ወደ ወለጋ የተላኩት። ወለጋ ሲደርሱ ኦነግሽሜ ደፈጣ ይዞ እንዲጠብቅ፣ የኦሮሚያ ብልፅግና መረጃ እንዲያሳስት፣ ፍርዬ ቴሌን፣ መብራት ኃይልም ባልቦላውን እንዲያጠፋ አደረጉ። አደረጉናም 20ሺ የፌደራል ፖሊስ እምሽቅ አድርገው ከቢሮም፣ ከሰፈርም አጸዱት። ኦነግ ሸኔም በሰበቡ 20ሺ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ቀረበለት። ዐማራም ከፌደራል ፖሊስ ፀዳ። ቢባረር፣ ከሥራ ቢቀነስ ስጋት ይሆን የነበረው ፌደራል ፖሊስ በዘዴ አስወገዱት። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ይሄም አይደል? ሙሉ ረጅሙን ቪድዮው በመረጃ ቲቪ አቀርብላችኋለሁ። እስከዚያው ይህቺን ቀምሳችሁ ተኙ።

"…ዐማራ አሁንም መከላከያን በገፍ እየተቀላቀለ ነው። መልካም ነው ሱማሌ ሄዶ ከአልሸባብ ጋር ተዋግቶ መሞት ግን እንዴት ያለ ጽድቅ ነው መሰላችሁ።

•ነፍስ ይማር…!