Get Mystery Box with random crypto!

የ40 ቀን ዕድሉ ወይስ…? '…ኧረ ወይኔ… እያሉ ሴቶቹ እያለቀሱ የዐማራ ወንድ ወንዱ እየተመረጠ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የ40 ቀን ዕድሉ ወይስ…?

"…ኧረ ወይኔ… እያሉ ሴቶቹ እያለቀሱ የዐማራ ወንድ ወንዱ እየተመረጠ እንዲህ በጅምላ መረሸኑ፣ በጅምላም መቀበሩ የዐማራው ዕጣ ፈንታው ከሆነ ሰንብቷል። በጦርነት ላይ የሚያልቀው እኮ እሺ እሱ አንድፊቱን ስም አለው። ጦርነት ነው። የሚያጨሰው እኮ በቤቱ የተቀመጠን ሰላማዊ ዜጋ ያለከልካይ በጠራራ ፀሐይ መረሸኑ ነው።

"…ይሄን ግፍ ለመናገር እንኳ ዐማራው ይፈራል። ቢያንስ ሌላው ይቅር አትግደሉኝ ብሎ መጠየቅ ምን ያስፈራል…? ይሄ በኦሮሚያ በምሥራቅ ሸዋ የሚጸዳው የዐማራና የሀዲያ ነገድ ነው። ኦሮሞ ዐማራን ብቻ ገድሎ፣ አርዶ የሚያቆም መስሎት ነበር አዳሜ። በየተራ ይመጡልሃል ጠብቅ።

"…በሰሜንም በራያ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። ከዐማራ፣ ከሚኒሻው፣ ከልዩ ኃይሉ፣ ከመከላከያውም ሙትና ቁስለኛው እንደቀጠለ ነው። የትግራይ ወጣቶችም የሬሳ ክምር በራያ ምድር በሚዘገንን መልኩ እንደቀጠለ ነው። ፎቶም፣ ቪድዮውንም ማየት ያጥወለውላል።

• ይህ በእንዲህ እንዳለ የሳይንስ ሙዚየም በአዲስ አበባ ተመርቋል። የገበታ ማጋራት ግን አልነበረውም። ኦህዴድ ለመጀመሪያ ጊዜ የምሳ ግብዣ ረሳ። ቁጢው ጠረረ ወይስ ረሱት?

"…ብቻ የሟቾቹን ነፍስ ይማር…!!