Get Mystery Box with random crypto!

'…ተጠባቂዋ ድርድር መጥታለች…!! '…አስቀድመን እንደተናገርነው በመጨረሻም በጉጉት የምትጠበቀዋ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ተጠባቂዋ ድርድር መጥታለች…!!

"…አስቀድመን እንደተናገርነው በመጨረሻም በጉጉት የምትጠበቀዋ የድርድር ዜና አሁን መጥታለች። ድርድር ሁልጊዜ ደግሞም የሚጠበቅ ነው። ሁለት ጉልበት ያላቸው ኃይላት መጀመሪያ ነገር ተፈላልገው በግልፅ ይፈሳፈሳሉ። ይፈሳፈሱ ይፈሳፈሱና ከዚያ መጨረሻ ላይ ድርድር የሚባል ጊዜ መግዣ የማምለጫ የወንድ በር ከች ያደርጉና ለማምለጥ ይሞክራሉ። ድርድር ለጤናማ ኃይላት ግሩም ነገር ነው። ድርድር ለወያኔ የማምለጫ፣ የጊዜ መግዣ ካርታዋ ነው። እንጂ ድርድርማ አስፈላጊና ቅዱስ ሃሳብ ነው።

"…ከወያኔ ጋር ድርድር በቦክስ ስፖርት ላይ ለእረፍት እንደሚደወለው ደወል ያለ ማለት ነው። ትፈሳፈስና እረፍት እንድትወስድ ይደወላል። ተደራድረህ ግን አይደለም። እረፍት ነው። በቦክስ ዘርረኸው ቀበቶህን ካላጠለቅ እንዲሁ እያረፍክ ስትቀጣቀጥ መዋልህ ነው። ህወሓትም እንደዚያው። ህወሓት ካልተወገደች ትግሬም፣ ዐማራም እረፍት አይኖራቸውም። ለ4ተኛ ዙር ይቀጣቀጣሉ። እናም የድርድር ሃሳቡ የመጣው ከማነው። ድርድሩ የሚጠቅመውስ ማንን ነው? ከዚህም ከዚያም የትየለሌ ነፍሳት ከጠፉ፣ ወደ ኋላ መቶ ዓመት የሚያሽቀነጥር የኢኮኖሚ ድቀት ከተፈጠመ በኋላ፣ የገበሬው ቤት ከፈረሰ፣ ከብት እና አዝመራው ከወደመ፣ የልጆቹን፣ የሚስቱን፣ የራሱንም ሞራል እንኩትኩቱን ካወጡት በኋላ፣ መሰረተ ልማቶች በሙሉ ከወደሙ በኋላ፣ አሸናፊው ሳይታወቅ ድርድር ደስ ባይልም ከተሳከ ለህዝቡም ሰላም ካስገኘ ጥሩ ነው። በሁለቱ ህዝብ ማለትም በትግሬና በዐማራው፣ በትግሬውና በአፋሩ መካከል ቋሚ የማይሻር የቂም በቀል ሃውልት ከተከተሉ በኋላ ነው እንግዲህ መጨረሻ ላይ ትንፋሽ መሰብሰቢያዋ ድርድር ተብዬዋ ካርታ ተስባ የማረፊያ፣ የጊዜ መግዣ ሆና ከች ብላ የምትመጣው።

"…ባለፈው ኢትዮጵያና ኤርትራ ተፈሳፈሱ። ብዙ መቶ ሺ ወጣቶችም ጭዳ ሆነው ከዚህም ከዚያም እንደቅጠል ረገፉ፣ መሰረተ ልማቱም ከወደመ፣ የቂም በቀል ሃውልትም በትግሬና በኤርትራ መካከል ከተተከለ በኋላ አሸናፊው የኢትዮጵያ ኃይል ተንኳሽ የተባለውን የሻአቢያ ኃይል ለማጥፋት በፈንጂ ላይ ተረማምዶ አስመራ ሊገባ ሲል በኢትዮጵያ የኤርትራ ተወካዮቹ እነ መለስ ዜናዊ እና አቦይ ስብሃት ነጋ ሠራዊቱን ባሬንቱ ላይ ታክል ገብተው አስቆሙት። ከአስመራ ፈርጥጦ ምጽዋ ገብቶ ለነበረው ለኢሳያስም በነፍስ ደረሱለት። አልጄሪያ ድረስ ሩጠው ተሯሩጠው እያለከለኩም ተደራደሩ፣ ከኢሳያስ ጋር ፎቶ ተነሥቶ ተጨባበጡም። ነገርየው በዚያው ያበቃም መሠለ። በዚህ የተነሣ ህወሓት ለሁለት ተሰነጠቀች። ሻአቢያም 20 ዓመት የሆዱን በሆዱ ይዞ፣ ቂም ቋጥሮ፣ ታግሶ ምቹ ጊዜ ሲጠብቅ፣ እንደ ነፍሰ ጡር ቀን ሲቆጥር ከርሞ፣ ዐቢይ የሚባል አድራሽ ፈረስ፣ ታዛዥ፣ እንደልቡ የሆነ ሰው ሲያገኝ ይኸው ትግራይን ተበቀላት። በሰማይ በምድርም አረሳት። አሁንም እየተበቀላት ነው። በቀሉም ይቀጥላል። ጥፋቱ የማነው ካልከኝ ግን መልሴ የራሷ የህወሓት ነው። አለቀ።

"…አሁንም እንደዚያ ነው። ህወሓት ዐማራ ክልል ገብታ ስትገድልም፣ ስትሞትም ፀጥ ይባልና፣ ሂዊ ሲደክማት፣ ስንቅ ሲያጥራት፣ ተተኳሽ ሲያልቅባት፣ ወደ ጎሬዋ መሸሽ ስትጀምር አጅሪት አማሪካ ከጎሬዋ ትወጣለች። ነጠላዋንም ዘቅዝቃ የስለት ልጇን ለማዳን ዋይ፣ ዋይ እያለች በአፍሪካ ምድር ትኳትናለች። ለሞተው ትግሬ ሳይሆን የሚሞት ለሚመስላት ህወሓት በነፍስ ለመድረስ ትባክናለች። ድርድር፣ ድርድር አሁኑኑ ትላለች። እምቢ ካልሽ ኢትዮጵያ ሆይ እንደ ሩሲያ፣ እንደ ኢራን በማዕቀብ ሽባ አደርግሻለሁ ትላለች። ከዚያ የኢትዮጵያ ጦር ባለበት እንዲቆም ዐቢይ አህመድ ያዛል። ከዚያም ህወሓት ትተርፋለች። መልሳም ከጎሬዋ ሆና ታቅዳለች።  የጎደላትን ሁሉ ታሟላለች። ነዳጅ፣ መሣሪያ፣ ምግብ፣ ተሽከርካሪ፣ መድኃኒት ሁሉ በአየር፣ በምድር ይገባላታል። አዲስ ተዋጊም ትመለምላለች። ታሰለጥናለች፣ ታስታጥቅና ለ4ተኛ ዘሩ የደቀቀውን የዋግ እና የራያ ዐማራን እንኩትኩቱን ለማውጣት ትመጣለች። የልቧን ፈጽማ ስንቅ ሲያልቅባት እንደገና ድርድር ትላለች። ተጎጂዎቹ ግን ዐማራና ትግሬዎቹ ናቸው። ኦሮሙማ ምን ቸገረው?

"…ከሁለቱም ከወያኔም፣ ከብልፅግናም አመራሮች እስከአሁን የሚጎዳ፣ የተጎዳም ሰው የለም። ሁለቱም እንዳማረባቸው አሉ። ይኖራሉም። ድሮስ አባትና ልጅ ምን ይሆናሉ? እንዳማረባቸውም ይኖራሉ። እምሽቅ የሚለው ህዝቡ ነው። ካድሬ ምን አለበት? ህወሓት ሻአቢያን ያላጠፋችው መለስና እነ ስብሃት በግማሽ ጎን ኤርትራውያን ስለነበሩ ነበር። ዐቢይ አሕመድም ህወሓትን የማያጠፋት የትግሬና የዐማራ ሰላም ለታላቋ ኦሮሚያ ግንባታ እንቅፋት ስለሚሆን መፈሳፈስ አለባቸው። ማረፍ የለባቸውም። በቂም በቀል እስከወዲያኛው መነካከስ አለባቸው ብሎ ስለሚያምን ነው የሚሉም አሉ። ህወሓት እያለች አይሆንም እንጂ ሂኢ እና ታዲያ ትግሬና ዐማራ ታርቀውና ተስማምተው በአፍጢሙ ይድፉት እንዴ? ሞኝህን ፈልግ።

"…በጦርነቱ የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ይገብራል። የዐማራም እንደዚያው። ዐማራው ግን ልጆቹን ብቻ አይደለም የሚገብረው። ሰራዊቱን ቀላቢም እሱ ነው። በሬ፣ ፍየል፣ በግ፣ ዳቦ፣ እንጀራ፣ ቂጣ፣ ቆሎ፣ ዶሮ፣ እርጎ፣ ወተት፣ ጠላ እና ጠጅ ሳይቀር ነው ለጥምር ጦሩ የሚያቀርበው። ምክንያቱም ህወሓት ስትመጣም ለምትበላው፣ ለምትዘርፈው ቢያንስ መከላከያዎቼ ይብሉት፣ በልተውም ያድኑኝ፣ ያትርፉኝ ከሚል ፍላጎት ነው። ተገቢም ነው።

"…መቼም ይሁን መቼም ህወሓት የምትባለዋ ካንሰር በዚያ ምድር በህይወት እያለች ትግሬም እረፍት አያገኝም። ዐማራም እረፍት አያገኝም። ህወሓት፣ ብአዴንና ኦህዴድኦነግ በዚያች ምድር እስካሉ ድረስ እረፍትና ሰላምን እንዳታስቧት። መጀመሪያ እነዚህ ሦስቱ ሰንኮፎች ተራበተራም ቢሆን መውለቅ፣ ጋንግሪኖቹም መቆረጥ አለባቸው። አለበለዚያ ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ እያልክ ስትማቅቅ ትኖራለህ እንጂ ሦስቱ ኢቦላዎች እያሉ ስለጤንነትህ እንዳታስባት።

"…ህወሓት መድኃኒት፣ ቀለብ፣ መሣሪያ እንዲገባላት እረፍት እንደምትፈልገው ሁሉ ዐቢይ አሕመድም ተንኮል ሴራው እንዳለ ሆኖ ቁጢ ስለጠረረበት ጥቂት ማረፍ ይፈልጋል። ትናንት እንኳ ያን የመሰለ ግዙፍ የሳይንስ ሙዚየም ካስመረቀ በኋላ እንደተለመደው ሻይ ቡና እንኳን አላዘጋጀም። በ4ዓመት ጉዞው ውስጥ ያልታየ አስደናቂ ክስተት ሆኖ ተመዝግቦ አልፏል። የሆነች ትንሽዬ ድልድይ መርቆ ድል ያለ ግብዣ ያደርግ የነበረው ሶዬ ትናንት ግን አልቻለም። "ማዕድ ማጋራት" የሚል ቅፅል የሚሰጠው የብልፅግናን ድል ያለ የተለመደ ግብዣም አላደረገም። መቼም ግብዣ የለመደ ካድሬ ትናንት ሳያብድ አይቀርም። የዐቢይ ያለመደገስ ግን ምክንያቱ ሌላ ነው። ቁጢ፣ ፈረንካ የሚባል በባንኩ ካዝና ውስጥ ስለሌለ ነው። ያለውንም ለኢሬቻ አውጥቶ ኢሬቻውን አብልቶታል። እናም እሱም ትንሽ ዶላር መሸቀል አለበት። ለምኖም ዕቃ ሽጦም ቢሆን ዶላር ፈረንካ መያዝ አለበት። አየህ ድርድሩ ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለእሱም በጣም አስፈላጊው ነው። ለዐቢይ አሕመድ።