Get Mystery Box with random crypto!

'…ተመልከት ወያኔ ታንክ አላት። መትረየስ፣ ዲሽቃ፣ ዙ 23፣ ቢኤም ሁላ አላት። አንድም ክልል ወያ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ተመልከት ወያኔ ታንክ አላት። መትረየስ፣ ዲሽቃ፣ ዙ 23፣ ቢኤም ሁላ አላት። አንድም ክልል ወያኔ ያላትን የለውም። ወያኔ ሽፍታም፣ መንግሥትም በነበረች ጊዜ የዘረፈችውንም፣ የቀበረችውንም መሣሪያ ቆፍራ አውጥታ ትጠቀማለች። በምርኮ ሰበብ የሚሄድላት፣ በአየር በእርዳታ ሰበብ በመኪና የሚሄድላት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። መሳሪያ ዘጭ ናት። ቢያልቅባት ተዋጊና ተተኳሽ እንጂ የመተኮሻ መሳሪያው ነፍ ነው ያላት። የሌሎቹ ክልል ልዩ ኃይሎች ከክላሽ በቀር፣ ከፍ ካለ ብሬን ከመተኮስ በቀር ሌላ ችሎታ የላቸውም። እንዲኖራቸውም አልተደረገም። ህወሓት የሃገሪቱን መከላከያ ትመራ በነበረ ጊዜ ዐማራውን ከክላሽ በቀር ከባድ መሣሪያ እንዲሰለጥን አላደረገችውም። ትግሬ ትግሬውን መርጣ ነው በኢትዮጵያ ሀብት ከባድ መሣሪያ አተኳኮስ ስታሠለጥን የኖረችው። ለዚህ ነው ትግሬዎቹ በውጊያ ወቅት አንድ ታንክ ከኢትዮጵያ ቢማርኩ ወዲያው ጥቅም ላይ የሚያውሉት። ፋኖም ሆነ የዐማራ ልዩኃይል ከህወሓት ታንክ ቢማርክ የታንኩን አይን አይኑን ከማየት በቀር ምንም ሊያደርጉት አይችልም። አየህ ለመደራደር እንኳ እንዲህ አቅም ሊኖርህ ይገባል። ዓለም አቅም ላለው ነው የምታጎበድደው። ምላስ ብቻውን አቅም አይሆንም። ሆኖም አያውቅም።

አቤት እስከአሁን ስንትና ስንት ወጣት ከዚህም፣ ከዚያም አልቆ ይሆን? …ብአዴን ያው እንደተለመደው ሰሞኑን የተደፈሩ የዐማራ ሴቶች፣ እናቶችና ወንዶችን በአሚኮ በኩል ሲያዥጎደጉድልን ይከርማል። የፈረሱ፣ የተቃጠሉ፣ የወደሙ ጤና ጣቢያዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ድልድዮች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ወዘተረፈ ሲያዥጎደጉድልን ይከርማል። መጀመሪያ እንዳይፈጸም ማድረግ ሲገባው ከሆነ በኋላ የበለጠ ህዝቡን ሲያቆስልበት ይኖራል።

"…ጦርነቱ መቆሙ አልተሰማም። ሦስተኛ ዙር ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። እስከአሁን የተኩስ አቁም ስምምነት አልተፈረመም። ሆኖም ግን በጦርነት ውስጥ ያሉት  የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር፣ (ትህነግ) በደቡብ አፍሪካ ሊደራደሩ መሆኑ በዛሬው ዕለት ተነግሯል። እናም አሁን ድርድሩ ይቀጥላል። መንግሥታችንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እደራደራለሁ ማለቱን ገልጿል። አደራዳሪዎቹና የመደራደሪያ አዳራሹም ተወልውሎ፣ ወይራ ጢሶበት፣ ጡንጂትና አሪቲ ቄጤማም ተጎዝግዞበት፣ ሺቶም ተርከፍክፎበት እየጠበቃቸው ነው። ድርድሩን ህወሓቶች በሚጠሉት የቀድሞው የናይጄርያው ፕሬዘዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እና ህወሓቶች በሚወዱት በቀድሞው የኬኒያ ፕሬዘዳንት በኡሁሩ ኬኒያታና ፋምዚሌ ምላምቦ ይመራል ተብሏል፡፡ ከኢትዮጵያ ወገን በዚህ ድርድር ላይ የህወሓት የበኩር ልጆች አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙ የሚጠበቅ ሲሆን የደመቀና የሬድዋን የቀድሞ አለቆችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ህወሓት ድርድሩን በተመለከተ እስከአሁን ያለችው ነገር የለም። ከህወሓት በኩል ከተንቤን በረሃ ወጥቶ ደቡብ አፍሪካ ለድርድር የሚሄድ ይኑር አይኑር የታወቀም ነገር የለም። ኦነግ ግን ለድርድር አልተጋበዘም። በምሥራቅ ወለጋ ሰባት ወረዳዎችን መቆጣጠሩ የተሰማው የኦነግ ሽሜን ንቀውት ይሁን አይሁን ለድርድር ያልጠሩት የታወቀ ነገር የለም። ህወሓት እንደሁ የገበረችውን የትግሬ ወጣት ደም ገብራ፣ ከዐማራ የዘረፈችውን በአህያም፣ በግመልም፣ በኮንኮላታም ጭና እየተወገረችም በለው እያፈገፈገች ወደ ጎሬዋ እየተመለሰች መሆኑ እውን ሆኗል። አሚኮም በቡድን የተደፈሩ የዐማራ ሴቶችን፣ የተገደሉ ዐማሮችን፣ የተዘረፉ፣ የተቃጠሉ፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እያሳየ እዬዬውን ይጀምራል። የደቡብ አፍሪቃው ድርድር ካልተሳካ ግን ያው እንደተለመደው ለማይቀረው ለአራተኛው ዙር ፍስፍስ ደግሞ ከወዲሁ መዘጋጀት ነው።

"…እየተደራደርን እንፈሳፈሳለን…!!