Get Mystery Box with random crypto!

አትዋሽ…!! '…የጦርነት ዘገባውን እንኳ እሺ ለምደነዋል። እንዲህ አይነቱን ቀደዳ ግን ተወው ወን | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አትዋሽ…!!

"…የጦርነት ዘገባውን እንኳ እሺ ለምደነዋል። እንዲህ አይነቱን ቀደዳ ግን ተወው ወንድሜ። ደግሞ በሱማሌም ባህል፣ በኢስላምም ውሸት ሃራም ነው የሚባለው። አንተ ደግሞ ከሱማሌም፣ ከኢስላምም በላይ የዩኒቨርሲቲ መምህር ነህ። ሌላው ቢቀር ተማሪዎቼ ይታዘቡኛልስ አትልም? መስፍን ፈይሳ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ቶማስ ጃጃው እንኳን እሺ እንጀራቸው ነው። ሀ ገደሉ ይበዛቸዋል የሚሉ መተርጉማንም አሉ። በዚያ ላይ ሌለው ይቅር ትልቅ ሰው አይደለህ እንዴ? ተው እንጂ…! የምን ዝም ብሎ መበጥረቅ ነው?

• ለማንኛውም አረጋዊው ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ፍርድ ቤትም አልቀረቡም። ከእስርም አልተፈቱም። ይኸው ነው። (ደግሞ ዝም ብዬ አይደለም አልተፈቱም የምልህ እኔው ራሴ ክብርት ባለቤታቸው ወ/ሮ ፀጋ ጋር ደውዬ ያረጋገጥኩትን ነው።) እኔ ከጀርመን ያረጋገጥኩትን አንተ ከሸገር እዚያው ማረጋገጥ ለምን አቃተህ። የሀሰት ዜናስ ምን ይጠቅማል?