Get Mystery Box with random crypto!

'…ሳፋሪኮሞች እንደምን አደራችሁ…? '…ስለ ህወሓት ብቻ እንጂ ስለ ዐማራ በኦሮሚያ በኦሮሞዎች | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሳፋሪኮሞች እንደምን አደራችሁ…?

"…ስለ ህወሓት ብቻ እንጂ ስለ ዐማራ በኦሮሚያ በኦሮሞዎች መታረድ፣ መቃጠል፣ መሰደድ፣ መውደም መስማትም ማየትም የማትፈልጉ ገተቶች እንደምን አደራችሁ? …እኔን የሚገርመኝ ዐማራ ሆኖ አጎት አክስቱ በኦሮሚያ እየፀዳ እሱ ከኦነግም፣ ከኦህዴድም በላይ ሆኖ ሲያሽቃብጥና ሲገረድ ያዙኝ ልቀቁኝም ሲል ማየቱ ነው። ኧረ ኤዲያ…!!

"…እውነት ነው። ሃቅም ነው። የህወሓት መወገድ፣ መጽዳትም እጅግ ወሳኝና አስፈላጊ፣ ጠቃሚም ነው። የህወሓት መወገድ ለራሱ ለትግሬውም ለዐማራውም፣ ለአፋሩም በአጠቃላይ ለኢትዮጵያም ለምሥራቅ አፍሪካም ትልቅ እረፍት ነው። የህወሓት ሰንኮፏ ሳይቀር ተቆርጦ መጣል አለበት። በዚህ በወያኔ ቫይረስ ከተጠቁ ጥቂቶች በቀር ሁላችንም እንስማማለን። ምክንያቱም አሁን የምናየው የዘር ፖለቲካ ጦስ የዚህ ሁሉ ችግር ፈጣሪ መርዟ እርሷ ስለሆነች ማለት ነው። ነገር ግን ህወሓትን መዋጋቱ እንዳለ ሆኖ ከእግርህ ጀምሮ እየቆረጠ አንገትህ ጋር የደረሰውን የኦሮሞ አራጅ ቡድን በስሱ እንኳ ላለመቃወም ምንድነው አፍህን የለጎመህ? ምን እስክትሆን ነው ግን የምትጠብቀው?

"…በነገራችን ላይ በወለጋ የሚኖር የወሎ እስላም ዐማራ ለነጋሪ፣ ለዘር ሳይቀር ነው እንዲህ እያረዱት ያሉት። ስምዝርዝራቸውን ጭምር እለጥፍላችኋለሁ። የእስልምናው መጅሊስ ግን ዝም፣ ጭጭ፣ ትንፍሽ አይላትም። ጎንደር ቢሆን ግን ሁለት ግለሰቦች ቢጣሉ ቱርክን ሳይቀር መግለጫ ያስወጧት ነበር። በወለጋ ግን ምንም። ትንፍሽ የለም።

"…ወዳጄ አንተ አዲስ አበባ ላይ በሚያሳዩህ የማትበላው ፕሮጀክት ጨፍር። እልልል ብለህ አሽቃብጥ። ከኋላ ግን ዜናው እንኳ እንዳይወጣ አድርገው አፍነው ይዘው እንዲህ እያረዱህ ነው። እየቀረቀሩልህም ነው። እያፀዱህም ነው። ሰምተሃል…!!

"…ቆይቼ ከቪድዮ ጋር እመለሳለሁ…!!